Friday, June 9, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየወላይታ ልማት ማኅበር ከ4500 በላይ ረዳት የሌላቸውን ሕፃናት እያስተማረ መሆኑን ገለጸ

የወላይታ ልማት ማኅበር ከ4500 በላይ ረዳት የሌላቸውን ሕፃናት እያስተማረ መሆኑን ገለጸ

ቀን:

ከተመሠረተ 15 ዓመታት ያስቆጠረው የወላይታ ልማት ማኅበር (ወልማ) በዞኑ ሁሉም ወረዳዎች የሚገኙ ከ4500 በላይ ረዳትና ወላጅ የሌላቸውን ሕፃናት እያስተማረ መሆኑን ገለጸ፡፡

ወልማ ከተቋቋመ ጀምሮ ከ2170 በላይ ተማሪዎችን 12ኛ ክፍል እንዲያጠናቅቁ በማድረግና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ያገኙ ተማሪዎችን አስመርቆ ለቁም ነገር ማብቃቱን፣ የማኅበሩ ዋና ዳይሬክተር አቶ አልታዬ አየለ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

አቶ አልታየ እንደገለጹት፣ ማኅበሩ ከታኅሣሥ 1 ቀን 2009 ዓ.ም. እስከ መጋቢት 2 ቀን 2009 ዓ.ም. ለገቢ ማሰባሰቢያ የሚውል የቶምቦላ ቲኬት አዘጋጅቶ ነበር፡፡ በሦስት ወራት ውስጥ ባካሄደው ሽያጭም 1.5 ሚሊዮን ትኬቶችን መሸጥ ተችሏል፡፡ የአንዱ ትኬት ዋጋ አሥር ብር መሆኑንና በድምሩ 15 ሚሊዮን ብር መሸጥ መቻሉን አስረድተዋል፡፡

በወላይታ ዞን የሚገኙ ሶዶ፣ ቦዲቲና አረካ ከተሞችን ጨምሮ፣ በ12 የገጠር ወረዳዎች ለሚገኙ ችግረኛና ቤተሰብ ያጡ ተማሪዎችን ለመርዳት፣ ማኅበሩ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እያደረገ መሆኑን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ችግረኛ ተማሪዎችን የሚመለምሉትም ወላጅ ያጡትን፣ ወላጅ ቢኖራቸውም ምንም ዓይነት ገቢ እንደሌላቸው ማረጋገጫ ያቀረቡና አቅም ኖሯቸው በተለያየ ምክንያት ትምህርታቸውን መቀጠል ያልቻሉትን መሆኑን አክለዋል፡፡

ወላይታ ሉቄ አዳሪ ትምህርት ቤትን ጨምሮ፣ በርካታ ተማሪዎችን እየረዱ መሆኑን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ዩኒቨርሲቲ ለሚገቡ ተማሪዎች ስንቅ፣ ትራንስፖርትና የትምህርት መሣሪያዎችን በዓመት ሁለት ጊዜ እንደሚረዱ ገልጸዋል፡፡

የዕርዳታ ማሰባሰቢያው ቶምቦላ ዕጣ መጋቢት 3 ቀን 2009 ዓ.ም. በብሔራዊ ሎተሪ አዳራሽ የወጣ ሲሆን፣ በዕጣ አወጣጡ ሥነ ሥርዓት ላይ የመንግሥት ምክትል ተጠሪ ሚኒስትር አቶ አማኑኤል አብርሃ፣ የወላይታ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አስራት ጤራና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

ሁለት 35 ኩንታል የሚጭኑ አይሱዙዎች፣ የቤት አውቶሞቢል፣ ሁለት ባለሦስት እግር ባጃጅ፣ ሞተር ሳይክልና ሁለት ላፕቶፖች ዕጣ ወጥቶባቸዋል፡፡ ጋራድ 66 ሺሕ ብር ዋጋ ያለው ስጦታ ማበርከቱም ታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ