Monday, December 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

‹‹ይድነቃቸው ተሰማ የወጣቶች እግር ኳስ አካዴሚ››

ትኩስ ፅሁፎች

በ70 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው ‹‹ይድነቃቸው ተሰማ የወጣቶች እግር ኳስ አካዴሚ›› መጋቢት 5 ቀን 2009 ዓ.ም. ሲመረቅ ከነበረው ሥነሥርዓት ከፊል ገጽታ፤ አካዴሚውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኰንንና የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ፕሬዚዳንት ኢሳ ሐያቱ መርቀውታል፡፡ (ፎቶ ዳንኤል ጌታቸው)

 

ብር ባይ

            ምኑንም ሳያየው ገና ከጅምሩ

                  ሊሮጥ ተቻኮለ፤

እንዳልገሩት ፈረስ ልጓም እንዳልነካው

ጥድፍ ጥድፍ አለ፡፡

ሐሳቡን ሳይገራ ልበ ድፍን ሆኖ

ከራሱ ተማክሮ፤

የዘንድሮ ጎበዝ ብር ብሎ ገደል

ገባ ተንደርድሮ፡፡

  • መላኩ ደምለው ‹‹ብልጭታ›› (2008)
  •  

ቺካጎ የወንዟን ቀለም አረንጓዴ አደረገች

የቅዱስ ፓትሪክ ክብረ በዓልን ምክንያት በማድረግ በከተማዋ የሚገኘው ወንዝ ውኃ ደማቅ አረንጓዴ እንዲሆን መደረጉን የሜትሮ ዘገባ ያመለክታል፡፡ የወንዞች ቀለም እንዲህ እንዲሆን የተደገው በፓውደር ሲሆን በየወንዞች ላይ የተሰማሩ ሁለት ጀልባዎች ወደ ወንዙ ውኃ ፓውደር የመጨመርና የመበጥበጥ ሥራ እንዲያከናውኑ በመደረጉ ነው፡፡ በዚህ መልኩ ዕለቱን አስቦ መዋል እ.ኤ.አ. ከ1952 የተጀመረ ሲሆን ክብረ በዓሉ ዓርብ የሚከበር ይሆናል፡፡

*********

የቀድሞዋ ፕሬዚዳንት ፓርክ ውሾችን አውላላ ሜዳ ላይ በመተው ተከሰሱ

ከሙስና ጋር በተያያዘ ባለፈው ሳምንት ከሥልጣን እንዲወርዱ የተደረጉት የደቡብ ኮሪያዋ ፕሬዚዳንት ፓርክ ቤተ መንግሥቱን ለቅቀው ሲወጡ ያሳድጓቸው የነበሩ ዘጠኝ ውሾችን እዚያው ጥለው በመውጣታቸው የአገሪቱ የእንስሳት መብት ተሟጋች ማኅበር ክስ እንዳቀረበባቸው የሮይተርስ ዘገባ አመለከተ፡፡ ውሾቹ ጂንዶ ተብለው የሚጠሩ የኮሪያ አዳኝና ታማኝ ናቸው፡፡ ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ ከሥልጣን የተነሱት ፓርክ እሑድ ዕለት በሶል ጋንጋም ግዛት ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ቢመለሱም ሥልጣን ተረክበው ወደ ሰማያዊው የኮሪያ ቤተ መንግሥት ሲገቡ ነዋሪዎች ከቀያቸው የተሰጧቸውንና ከዚያም የተዋለዱትን ጂንዶዎች ይዘዋቸው ሳይመለሱ ቀርተዋል፡፡ የመከሰሳቸው ምክንየት ይኼው ነው፡፡

********

በአዞ ፊቱ እንዳልሆነ የሆነው የሠርከስ ባለሙያ

በምሥራቃዊ ቬትናም ከአዞ ጋር በመሆን ትርዒት ያሳይ የነበረው ባለሙያ ድንገት አዞው ተቆጥቶ ጭንቅላቱን ውጦ ሲለቅቀው የፊት ገፅታው እንዳልሆነ መሆኑን የሜትሮ ዘገባ አመልክቷል፡፡ ትርዒተኛው ወዲያው ፊቱን በሁለት እጆቹ በመያዝ ራሱን ተቆጣጥሮ ጥቂት ዕርምጃዎችን ለማድረግ ቢሞክርም ይህ ፈጽሞ የሚቻል አልሆነም፡፡ ፊቱ በከፍተኛ ሁኔታ ይደማ ጀመረ፤ ከዚያም ከታዳሚዎች በተወረወረለት ፎጣ ፊቱን ይዞ ሲወርድ አዞው መድረኩ ላይ ብቻውን ቀረ፡፡ 

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች