የካቲት 30 ለመጋቢት 1 ቀን 2009 ዓ.ም. አጥቢያ ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት በአንድ ዲፕሎማት ስትሽከረከር የነበረች ቶዮታ ራቭ4 አውቶሞቢል ከአፍሪካ ጎዳና (መስቀል አደባባይ አቅጣጫ) ወደ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት በመጓዝ ላይ ሳለች፣ የቻይና አፍሪካ ወዳጅነት አደባባይን ዞራ መሄድ ሲገባት አደባባዩን ጥሳ የመገልበጥ አደጋ ደርሶባታል፡፡ በአውቶሞቢሏ ላይ መጠነኛ ጉዳት ከመድረሱ ውጪ፣ በአደጋው አሽከርካሪውም ሆነ በሌሎች ሰዎች ላይ የደረሰ ጉዳት የለም፡፡
ፎቶ በዳንኤል ጌታቸው