Wednesday, February 28, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበአዲስ አበባ በእግረኞች ላይ የሚደርስ አደጋን የሚቀንስ ስትራቴጂ ይፋ ሆነ

በአዲስ አበባ በእግረኞች ላይ የሚደርስ አደጋን የሚቀንስ ስትራቴጂ ይፋ ሆነ

ቀን:

በአዲስ አበባ ከተማ በእግረኞች ላይ የሚደርሰውን የተሽከርካሪ አደጋ ለመቀነስ፣ የአስተዳደሩ ካቢኔ ያፀደቀው የ13 ዓመታት ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ይፋ ተደረገ፡፡

ስትራቴጂካዊ ዕቅዱን ለጋዜጠኞች ያስተዋወቁት በከንቲባ ድሪባ ኩማ መሪነት፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ይህደጐ ሥዩምና ሌሎች የሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ናቸው፡፡

ስትራቴጂውን ለማዘጋጀት የሚያስችሉ ጥናቶች በብሉምበርግ ፊለንትሮፒስ ኢንሼቲቭ ፎር ግሎባል ሮድ ሴፍቲና አጋር ድርጅቶች መዘጋጀታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ከተማዋ በተለይ ለእግረኞች ደኅንነት ምቹ እንድትሆን ያስችላት ዘንድ፣ የከተማዋ አመራሮች የ13 ዓመታት የመንገድ ደኅንነት ስትራቴጂን ይፋ አድርገዋል፡፡ ከተቀመጡት መፍትሔዎች መካከልም የእግረኞች ቁጥር በሚበዛባቸው አካባቢዎች የተሽከርካሪዎችን ሕጋዊ የፍጥነት መጠን መቀነስ፣ የተሻሻሉ የመንገድ ዲዛይኖች፣ የትራፊክ ሕጐችን በአግባቡ ማስፈጸም፣ ሕግ ለሚተላለፉ አሽከርካሪዎች ቅጣቱን መጨመር፣ ተደራሽ የሕዝብ መገናኛ ብዙኃን ዘመቻን ማካሄድና የመንጃ ፈቃድ አሰጣጥ ሥርዓቱን ማጥበቅ የሚሉት ይገኙበታል፡፡

ከጥናቶቹ ቁልፍ ግኝቶች መካከል በ2008 ዓ.ም. በከተማዋ 463 የሞት አደጋዎች በትራፊክ አደጋ ሳቢያ መከሰታቸው ተጠቃሽ ነው፡፡ በከተማዋ የሕዝብ ቁጥር መጨመርና ከፈጣኑ የከተማ ዕድገት ጋር ተያይዞ ይህ አኃዝ በአንፃራዊነት የተረጋጋ ሊባል እንደሚችል፣ ሆኖም ይህ አኃዝ የሚወክለው የተመዘገቡ አደጋዎችን ብቻ እንደሆነና ቀላል የማይባሉ አደጋዎችን በአግባቡ ያለማስመዝገብ ችግር እንደሚስተዋል ተጠቁሟል፡፡

በአጠቃላይ የሞት አደጋ ከሚደርስባቸው የመንገድ ተጠቃሚዎች መካከል 80 በመቶ እግረኞች ናቸው፡፡ በከተማዋ ካሉ መንገዶች ውስጥ ደግሞ 14 በመቶ ብቻ ለእግረኛ ተስማሚ መሆናቸው ተገልጿል፡፡ ከፍጥነት ልክ በላይ ማሽከርከርና ጠጥቶ ማሽከርከር የመሳሰሉ ለአደጋ አጋላጭ የአሽከርካሪ ባህሪያት የተንሰራፉባት ከተማ መሆኗን ጥናቶቹ ያመለክታሉ፡፡

ከ2008 ዓ.ም. አንስቶ አሽከርካሪዎች በሚያሽከረክሩበት ወቅት በሰውነታቸው ውስጥ የሚገኘውን የአልኮል መጠን ለማወቅ በተከናወነ ምርመራ 5.9 በመቶ ያህሉ በደማቸው ውስጥ ሊኖር ከሚገባው የአልኮል መጠን በላይ ተገኝቶባቸዋል፡፡ ከሦስት የሞተር ብስክሌት ጋላቢዎች አንዱ ብቻ የራስ ቅል መሸፈኛ (ሔልሜት) በአግባቡ እንደሚያደርግ ሲገለጽ፣ የተሽከርካሪ ተሳፋሪዎች የመቀመጫ ቀበቶ አጠቃቀም እጅግ በጣም ዝቅተኛ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ በተጨማሪም 40 በመቶ የሚሆኑ ተሽከርካሪዎች ከፍጥነት ልክ በላይ እንደሚንቀሳቀሱ መታወቁ ተገልጿል፡፡

ቁጥራቸው እጅግ የበዛ የትራፊክ አደጋዎች የሚደርሱት በወንዶች ላይ መሆኑንና 92.2 በመቶ እንደሚወክሉ ተጠቁሟል፡፡ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ታክሲዎች 23 በመቶ የሚሆነውን የትራፊክ ሞት አደጋ በማድረስ ከፍተኛ ድርሻውን እንደሚወስዱ፣ ከሁለት ዓመት በታች የማሽከርከር ልምድ ያላቸው አሽከርካሪዎች 26 በመቶ የሞት አደጋዎችን ማድረሳቸው በጥናቱ ተገልጿል፡፡            

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...