Wednesday, March 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየታላቁ ሕዳሴ ግድብ የእግር ኳስ ውድድር ይካሄዳል

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የእግር ኳስ ውድድር ይካሄዳል

ቀን:

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የመሠረት ድንጋይ የተጣለበት ስድስተኛ ዓመት ክብረ በዓል በተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮች በመከበር ላይ ይገኛል፡፡ መጋቢት 14 እና 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በአራት የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች መካከል የሚደረገው የእግር ኳስ ውድድር ከስፖርታዊ ውድድሮቹ ተጠቃሽ ነው፡፡

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት በላከው እንዳስታወቀው፣ መጋቢት 14 እና 16 ቀን 2009 ዓ.ም. የሚደረገው የእግር ኳስ ውድድር መርሐ ግብር በኢትዮጵያ ቡና፣ በፋሲል ከነማ፣ በአዳማ ከነማና በአርባ ምንጭ ከነማ ክለቦች መካከል የሚደረገው የእግር ኳስ ጨዋታ ይጠበቃል፡፡ ስድስተኛ የምሥረታ ክብረ በዓሉን እያከበረ የሚገኘው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ከ90 ሺሕ በላይ ተሳታፊዎች የታደሙበት የሩጫ ውድድር አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም የአገሪቱ ክልል ከተሞች ከሁለት ሳምንታት በፊት መከናወኑ ይታወሳል፡፡

የክብረ በዓሉ አንድ አካል የሆነውና በአራቱ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች መካከል በሚደረገው የእግር ኳስ ጨዋታ በመርሐ ግብሩ መሠረት፣ ሐሙስ መጋቢት 14 ቀን 2009 ዓ.ም. ፋሲል ከነማ ከአዳማ ከነማ ጋር በ9 ሰዓት፣ ኢትዮጵያ ቡና ከአርባ ምንጭ ከነማ ደግሞ በ10 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም የመጀመርያ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

መጋቢት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. በመጀመርያው የጨዋታ መርሐ ግብር ያሸነፉት ቡድኖች ለዋንጫና ተሸናፊዎቹ ቡድኖች ደግሞ ለደረጃ በ9 እና በ10 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም እንደሚጫወቱ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት አስታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...

አወዛጋቢነቱ የቀጠለው የአዲስ አበባ የጤፍ ገበያ

ሰሞኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጤፍ የተከሰተውን የዋጋ ንረት...