Monday, March 4, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅ‹‹የጭንቅ ጉዞ››

‹‹የጭንቅ ጉዞ››

ቀን:

በምሥራቅ ትግራይ፣ የገረዓልታ ተራሮች እቅፍ ውስጥ ከሚገኙት ውቅር አብያተ ክርስቲያናት አንዱ ወደ ሆነው አቡነ ይምዓታ ለመድረስ. . .

(ፎቶ ከፌስቡክ)

ስም ብቻ ስንብት

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የትናንት – አብሮ ውሎ

የአብሮነት – ገመድ ሰሎ

የደግመን አንገናኝ ይሆንን …? 

      ስጋት አክሎ

የስሜት እንባ ግድብ ሊገፈተር

ከዓይን ዙሪያ – ሲንጠረዘዝ

ሆድ በስስት – ሲማሰል

ክናድ – በአንገት ዙሪያ ተጋምዶ

በሐዘን ስልት እንጉርጉሮ – ልቅሶ

ክፉ – አይድረስብን የኔ – ዓለም

እኔም ያላንች አንችም ያለኔ – የለንም

በል ይቅናህ! ይቅናኝ – ተባብሎ

            ደፋር መስሎ

            አንጀት አስሮ

ሸኝም ሸኝ ሆኖ

ልቡን አስከትሎ

      ሒያጅም ተጓዥ – መስሎ

      ልቡን ጣል አድርጎ፡፡

  •  

… ያወጋሉ …

ሁለቱም በሁለቱ ውስጥ አሉ

      ይቀራሉም ይጓዛሉ

      ስም – ብቻ ስንብት፡፡

  • አገኘው አዳነ ድልነሳው ‹‹ጨለማን ሰበራ›› (1987)
  •  

500 ኪሎ የምትመዝነዋን ግብፃዊት ክብደት ለመቀነስ ቀዶ ሕክምና ተደረገላት

በዓለም በክብደቷ ቀዳሚ ናት ተብላ የምትገመተውን ግብፃዊት ኢማን አህመድ ክብደት ለመቀነስ በህንድ ቀዶ ሕክምና ተደርጎላታል፡፡

ቢቢሲ እንደዘገበው፣ የ36 ዓመቷ ኢማን 500 ኪሎ ግራም የምትመዝን ሲሆን፣ በህንድ ሙምባይ ሳፊ ሆስፒታል በተደረገላት ቀዶ ሕክምና 100 ኪሎ ቀንሳለች፡፡

ቤተሰቦቿ እንደሚሉት፣ ኢማን ለ25 ዓመታት ያህል ከቤቷ ወጥታ አትውቅም፡፡ ከሁለት ወራት በፊት ወደ ህንድ ለሕክምና ያመጧትም አውሮፕላን በግል ተከራይተው ነው፡፡

የሆስፒታሉ ቃል አቀባይ እንዳስታወቁት፣ በባሪአትሪክ (በጣም የወፈሩ ሰዎችን በቀዶ ሕክምና የሚያስተካክል ባለሙያ) ቀዶ ሐኪም በሚመራ ቡድን ቀዶ ሕክምና የተደረገላት ኢማን፣ በቀጣይ በሚደረግላት ሕክምና ተጨማሪ ኪሎዎችን እንድትቀንስ ይደረጋል፡፡

*********

የብርድ ልብስ ክፍያ ያስነሳው ውዝግብ የአውሮፕላን በረራ አስተጓጎለ

 የ66 ዓመቱ የህዋያን አየር መንገድ አውሮፕላን ተሳፋሪ፣ አውሮፕላኑ ከላስ ቬጋስ ወደ ኖሆሉሉ በመብረር ላይ እያለ ነበር ‹‹በርዶኛል ብርድ ልብስ ስጠኝ›› ብለው የበረራ አስተናጋጁን የጠየቁት፡፡

የበረራ አስተናጋጁም ብርድ ልብሱ 12 ዶላር እንደሚያስከፍል ይነግራቸዋል፡፡ ተሳፋሪውም የአየር መንገዱን ባለሥልጣናት ማናገር እንደሚፈልጉ በቁጣ ያሳውቃሉ፡፡ የበረራ ላይ ስልክ ተጠቅመው አቤቱታቸውን እንዲያሰሙ የተፈቀደላቸው አዛውንት፣ የጠየቁት ግን ብርድ ልብስ ሳይሆን አንድ ሰው ከእንጨት ማከማቻ ክፍል መውሰድ እንደሚፈልጉ መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

አዛውንቱ የጠየቁት ጥያቄ ጥርጣሬ ውስጥ ያስገባቸው የአየር መንገዱ ባለሥልጣናት ወደ ኖሆሉሉ ተጀምሮ የነበረው በረራ ተስተጓጉሎ አውሮፕላኑ ላስቬጋስ እንዲመለስ አድርገዋል፡፡ ተሳፋሪው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከአውሮፕላኑ እንዲወርዱ ተደርጎ በሌላ በረራ መጓዝ እንደሚችሉ እንደተነገራቸው ዩፒአይ ዘግቧል፡፡

************

ባለመኪኖችን ያስደነበሩ እንቁራሪቶች

በሰሜን ለንደን በሚገኝ ሱፐርማርኬት መኪና ማቆሚያ ስፍራ ውስጥ 50 እንቁራሪቶች ተጥለው መገኘታቸው መኪና አሽከርካሪዎችን አስደንብሯል፡፡ የሰሜን ለንደን ፖሊስ ዲፓርትመንት እንደሚለው፣ 20 እንቁራሪቶች ከነበሩበት የፕላስቲክ ቦርሳ ውስጥ መጥተው ነበር፡፡ ‹‹እንቁራሪቶቹ በየቦታው እየዘለሉ ነበር›› ያለው ፖሊስ፣ 50ውን እንቁራሪቶች በመያዝ ምርመራ አድርጓል፡፡

ኤክስፕረስ ዩኬ እንደሚለው፣ እንቁራሪቶቹ በፑትኒ የእንስሳት ሆስፒታል ተመርምረው ጤናማ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡ ለምንና በማን ወደመኪና ማቆሚያ ስፍራው እንደተጣሉ ግን ማወቅ አልተቻለም፡፡ እንቁራሪቶቹም ወደ ጫካ ተለቀዋል፡፡

**********

ፍሬ ልቡና

የሰውን ትውልድ እንደሚያጠፋ ቸነፈርና ብዙ መርዝ እንዳለው እባብ ከሰው አፍ የሚወጣ ሐሜትም እንዲሁ ነው፡፡ ከሐሜት ተጠበቅ፤ ቁጥር ስፍር የሌላቸው ብዙ ክፋቶችና መከራዎች ከሐሜት ይበቅላሉና፡፡ ቃሉ ለጆሮችህ ደስ የሚያሰኝ ቢሆንም ወንድሙን የሚያማን አትስማ፡፡ አንተ ራስህ ሰዎች እንዲያሙህ አትፈልግምና፡፡ ስለዚህ ከሐሜት ልትርቅ ይገባሃል፡፡ ሐሜትስ በእውነት ሌብነት ነው፡፡ የባልንጀራችንን ስም የምትሰርቅም አንደበታችን ናት፡፡ ሌባ የሌላውን ገንዘብ ስለሰረቀ ፍርድ እንደሚገባው እንዲሁም ሐሜተኛ የባልንጀራውን መልካም ስም ስለሰረቀና ስላጠፋ ጽኑ ፍርድ ይገባዋል፡፡

አንተም ከወዳጆችህ ጋር ስትነጋገር አፍህንና አንደበትህን ጠብቅ፡፡ አንደበትህ ከጠላት ሁሉ ይከፋልና፡፡ ቃልህ ከአፍህ ሲወጣ የሚያምር ይመስልሃል፡፡ በኋላ ግን በደረቀ አገዳ ውስጥ እንደሚነድ የእሳት ነበልባል ይነድዳል፡፡ በምንም ሥራ ልታጠፋው አትችልም፡፡ ነገርህ ሁሉ ከልብህ ሳይወጣ በጥበብህ ሚዛን ልትመዝነው ይገባል፡፡ ያለበለዚያ ግን ሳታስብ ካወጣኸው በኋላ በከንቱ ትጸጸታለህ፡፡ ከዝምታ የሚሻል መናገር እንደሌለ አስብ፡፡ ሁሉን ከመናገር ይልቅ ዝምታ ይሻላልና፡፡ ተናጋሪ ሰው ነገርን አያቃናም፡፡

አንድ ሰው ነበር፡፡ እርሱም ከቀደሙት ጠቢባን ወደ አንዱ ሂዶ፣ ‹‹ጠቢብ ሆይ ከሰው ሁሉ ጋር ሰላምን እንዳገኝ ምን ማድረግ ይገባኛል? ንገረኝ›› አለው፡፡ ያም ጠቢብ አንዱን እጁን በአፉ ላይ ሌላይቱ እጁንም በብልቱ ላይ አስቀመጠ እንጂ ምንም አልመለሰለትም፡፡ በዚህም አንዱ ከሌላው ጋር ሰዎችን የሚያጣሉ ሦስት ምክንያቶችን ያመለክታል፡፡ ከእነሱ አንደኛው ክፋትና ስንፍናን፣ ሐሜትና ስድብን የሚናገር፣ ስፍር ቁጥር የሌለው ጠብ የሚያመጣ አንደበት ነው፡፡ ሁለተኛው ምክንያት ሰዎችን ሁሉ የሚያጣላ፣ ዝሙትን የሚያበዛና ግድያንና ጠብን ያለልክ የሚያመጣ እስኪት (ብልት) ነው፡፡ ሦስተኛው ምክንያት እጆች ወደ ሌላው ገንዘብ በሚዘረጉበት ጊዜ ነው፡፡

አንተ ግን ብልሀተኛ ከሆንህ አፍህንና አንደበትህን በታላቅ ጥንቃቄ ጠብቅ፡፡ የማይጠቅምህን አትናገር፡፡ ነገርን አታብዛ፣ ለመናገርም አትቸኩል፡፡ ዳግመኛም እጆችህን ጠብቅ፡፡ የሌላ ገንዘብ ከሆነው ወደ ምንም ፈጥነው እንዳይዘረጉ ከልክላቸው፡፡ መስረቅ ታላቅ በደል ነውና፡፡ ይልቁንም ፊትን ያሳፍራል፡፡ ከገንዘብህ አንዳች ይጠፋ ዘንድ እንደማትወድ እንዲሁም የሌላውን ገንዘብ እንዳታጠፋ እወቅ፡፡ ስለ ሥራህም አዝኖ እንዳይረግምህ፣ ወደ እግዚአብሔር እንዳይጮህና እሱም እንዳይቀስፍህ የድካሙንም ፍሬ አታጥፋበት፡፡ በፈቃድህ ቢሆን፣ ያለፈቃድህ ከባልንጀራህ ገንዘብ አንዳች ካጠፋህ በምንም ምክንያት ቢሆን የባልንጀራህ ብድር በእጅህ ከተገኘ ከእርሱ ጋር ባለህ ብድር መጠን ፈጥነህ ክፈለው እንጂ አታዘግይ፡፡ ከቀማኞች ጋር እንዳትቀሰፍ፡፡ በሰው ዘንድ ያለውን ፍርድ ባትፈራም ከእግዚአብሔር ፍርድ በምንም መንገድ ልታመልጥ አትችልም፡፡

ብልትህን ለመጠበቅ በፍጹም ትጋት ተጋደል፡፡ ያለዚያ ግን ከአቅም በላይ የሆነ መከራ ያገኝሃል፡፡ ለዘማዊ ሰላም የለውምና፡፡ በእግዚአብሔርና በሰው ዘንድም ምሕረት የለውም፡፡ ዓይኖችህን ወደ ሰው ሚስት አታንሳ፤ እንዳትመኛት፡፡ የሐዘን፣ የትካዜ ወጥመድ አለባትና፡፡ ለወንድ ግን ሚስቱ ትበቃዋለች፡፡ ለሴትም ባልዋ ይበቃታል፡፡ አስቀድሞ የሚጥም ይመስላል፡፡ በኋላ ግን ከእባቦች መርዝ ይልቅ ይመራል፡፡ ወደ ሰው ሚስት የሚስብህ የሥጋህ ምኞት እሺ፣ በጀ አትበለው፡፡ ወይም ወደ ሴት ባል ለሚስብሽ የሥጋሽ ምኞት እሺ፣ በጀ አትበይው፡፡ ይህ ታላቅ ሌብነት ነውና፡፡ ለፍርድም የሚገባ ነውና፡፡

አለቃ ያሬድ ፈንታ ‹‹ሐተታ ዘርዐ ያዕቆብ ወሐተታ ወልደ ሕይወት የኢትዮጵያ ፍልስፍና›› (2007) 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...