Thursday, June 13, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርትየካፍና የኮሳፋው ፕሬዚዳንት ቺያንጋዋ ውዝግብ

የካፍና የኮሳፋው ፕሬዚዳንት ቺያንጋዋ ውዝግብ

ቀን:

  • ኢትዮጵያን ጨምሮ አምስት የአፍሪካ አገሮች በሐራሬው የኮሳፋ ስብሰባ መገኘት ካፍን አስቆጥቷል

  የአፍሪካ ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ከመጋቢት 5 እስከ 7 ቀን 2009 ዓ.ም. በአዲስ አበባ 39ኛውን መደበኛ ስብሰባና የቀጣዩን አራት ዓመት የካፍ አመራሮች ምርጫ ያከናውናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ይሁንና ካፍ ከሚያስተዳድራቸው አምስቱ ዞኖች ሰባት አገሮች በአባልነት የተካተቱበት የደቡባዊ አፍሪካ ዞን (ኮሳፋ) ባደረገው ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ አምስት የአፍሪካ አገሮች በተጋባዥነት መገኘታቸው ካፍን ማስቆጣቱ የቢቢሲ ዘገባ አመልክቷል፡፡ የኮሳፋው ስብሰባ በአዲስ አበባ የሚደረገውን የካፍ መደበኛ ስብሰባና ምርጫ ለማናጋት ያለመ ስለመሆኑ ጭምር ዘገባው ካፍን ጠቅሶ አትቷል፡፡

እንደ ዘገባው ከሆነ፣ የፊታችን ማክሰኞ፣ ረቡዕና ሐሙስ በአዲስ አበባ ከሚደረገው የካፍ መደበኛ ስበሰባ በተጨማሪ ተቋሙን ለቀጣዩ አራት ዓመት የሚያስተዳድሩት የፕሬዚዳንትና የሥራ አስፈጻሚ ምርጫ ይደረጋል፡፡ በምርጫው ካፍን ላለፉት ሦስት አሠርታት የመሩት ካሜሩናዊ ኢሳ ሐያቱና የማዳጋስካሩ አህመድ አህመድ ለፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተፎካካሪ እንደሚሆኑ ይጠበቃል፡፡

የደቡባዊ ዞን አገሮች (ኮሳፋ) ፕሬዚዳንት የዚምባቡዌ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ፊሊፕ ቺያንጋዋ ናቸው፡፡ ቺያንጋዋ ከዚህ ኃላፊነታቸው በተጨማሪ የኢሳ ሐያቱ ተፎካካሪ ሆነው ለሚቀርቡት የማዳጋስካሩ አህመድ የምርጫ ቅስቀሳ ማናጀር ስለመሆናቸው ጭምር ዘገባው ይጠቁማል፡፡

- Advertisement -

የደቡባዊ አፍሪካ አገሮች (ኮሳፋ) የካቲት 16 ቀን 2009 በሐራሬ በጠራው ስብሰባ ላይ በተጋባዥነት የተገኙት አገሮች ከምሥራቅ አፍሪካ ኢትዮጵያና ጂቡቲ ሲሆኑ፣ ከምዕራብ አፍሪካ ደግሞ ጋና፣ ላይቤሪያና ናይጄሪያ ናቸው፡፡

እንደ ዘገባው ከኮሳፋው ስብሰባ በተጨማሪ ቺያንጋዋ የልደት ቀናቸውን ምክንያት በማድረግ ተጋባዥ አገሮቹ እንዲገኙ ማድረጋቸው ተነግሯል፡፡ የካፍን ውንጀላ አስመልክቶም ጉዳዩን በሕግ እንደሚከታተሉት ጭምር ቺያንጋዋ ማስጠንቀቃቸው ተመልክቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...