አስፈላጊ ግብዓቶች
- ኪሎ ዓሳ ተቀቅሎ የተፈጨ
- 3 እንቁላል አስኳሉና ዞፉ የተለየ
- 3 የሾርባ ማንኪያ የፉርኖ ዱቄት
- 1 የሾርባ ማንኪያ ፐርሰሜሎ
ትንሽ ነጭ ሽንኩርት የተከተፈ፣ ጨው፣ ቁንዶ በርበሬ
አሠራር
- ዓሳ፣ የእንቁላል አስኳል፣ ዱቄት፣ ቁንዶ በርበሬ፣ ነጭ ሽንኩርት፣ ፐርሰሜሎ በጎድጓዳ ሣህን ማደባለቅ፡፡
- የተመታ የእንቁላል ዞፍ ከላይ ከተዘጋጀው ድብልቅ ጋር ማዋሀድ፡፡
- በመጥበሻ ላይ በፈላ ዘይት የዓሳና የእንቁላል ድብልቁን በማንኪያ እያወጡ ጨምሮ እያገላበጡ መጥበስ፡፡
አራት ሰው ይመግባል፡፡
- ጽጌ ዕቁባሚካኤል ‹‹የእናት ጓዳ›› (1984)