Thursday, September 21, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

በግማሽ ዓመት ከውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት 1.2 ቢሊዮን ዶላር መገኘቱ ተገለጸ

ተዛማጅ ፅሁፎች

በተያዘው የበጀት ዓመት ስድስት ወራት ውስጥ ከውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት 1.2 ቢሊዮን ዶላር የተመዘገበው፣ ከአምናው መሻሉን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ባወጣው ሪፖርት የስድስት ወራቱ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ35 በመቶ አብላጫ ማሳየቱ ተገልጿል፡፡ ለቀጥተኛ ኢንቨስትመንቱ መሻሻል ምክንያት ከሆኑ ነገሮች ውስጥ በአገሪቱ ‹‹የታየው ሰላማዊ ሁኔታ አንዱ ሲሆን፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች መስፋፋትና ወደ ግንባታ መግባት ሌላኛው ምክንያት ነው ተብሏል፡፡

በተለይም የኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ የአሜሪካ፣ አውሮፓና የእስያ ታላላቅ ኩባንያዎችን ለመሳብ አስችሏል ሲል የኮሚሽኑ የግማሽ ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት አስረድቷል፡፡

‹‹ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ ታዋቂ ኩባንያዎች ወደ አገር ውስጥ መግባታቸውንና ይህም የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰቱን በማሳደግ የላቀ አስተዋጽኦ አድርጓል፤›› በማለት ሪፖርቱ ገልጿል፡፡

ለአብነትም በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የተሰማሩ ሦስት የቻይና፣ ሁለት የህንድና የሌሎች አገሮች ኩባንያዎች በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ መግባታቸውን፣ ከእነዚህም ውስጥ ኪያንግሱ ሰንሻይን ግሩፕ በኢትዮጵያ 945 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስት ለማድረግ መወሰኑን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡

በተያያዘም በዚሁ የሐዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ውስጥ የሚገኙና ቀደም ብለው ሥራ የጀመሩ ፋብሪካዎች ከመጋቢት ወር መጨረሻ በኋላ ምርታቸውን ወደ ውጭ ገበያ እንደሚያቀርቡ ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

በፓርኩ ሥራ የጀመሩ ፋብሪካዎች ፈጥነው ወደ ሥራ መግባታቸው ቀደም ብሎ የታቀደውን የአንድ ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ማሳካቱንና ይሳካል የሚል እምነት እንዳሳደረባቸውም የኮሚሽኑ ኃላፊዎች ገልጸዋል፡፡

በፓርኩ ሥራ ከጀመሩ ኩባንያዎች መካከል ታል ጨርቃ ጨርቅ ኩባንያ የሸሚዝ ምርት በመጋቢት ወር መጨረሻ ላይ ለውጭ ገበያ ማቅረብ ይጀምራል ብለው እንደሚጠብቁ ኃላፊዎቹ ገልጸዋል፡፡   

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች