Sunday, March 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ሥነ ፍጥረትአንበጦችና የነርቭ ሴላቸው

አንበጦችና የነርቭ ሴላቸው

ቀን:

በራሪዎቹ አንበጦች እንቅስቃሴያቸውን የሚቆጣጠሩት በነርቭ ሴላቸው አማካይነት መሆኑ ይወሳል፡፡ ጄ ደብሊው ኦርግ በድረ ገጹ እንደጻፈው፣ በመንጋ የሚጓዙት አንበጦች ‹‹በአንድ ካሬ ኪሎ ሜትር ስፋት ውስጥ 80 ሚሊዮን›› አንበጦች አብረው ሊበርሩ ይችላሉ፡፡

ይህ ሁሉ ሆኖ እነዚህ በራሪዎች አንዳቸው ከሌላው ጋር የማይጋጩበት ምሥጢር ምንድን ነው? ለሚለው የሳይንስ ሊቃውንት የሚሰጡት ምላሽ አለ፡፡

እንደ ድረ ገጹ ማብራሪያ አንበጦች ከዓይኖቻቸው በስተጀርባ ‹‹ሎቡላ ጃይንት ሙቭመንት ዲቴክተር›› ተብሎ የሚጠራ እንቅስቃሴን የሚቆጣጠር የነርቭ ሴል አለ፡፡ አንበጦቹ ሊጋጩ ሲቃረቡ እነዚህ ሴሎች ለክንፎቻቸውና ለእግሮቻቸው መልእክት በማስተላለፍ ፈጣን ዕርምጃ እንዲወስዱ ያደርጋሉ፡፡ እንዲያውም ዕርምጃ የሚወስዱበት ፍጥነት ዓይን ከሚርገበገብበት በአምስት እጥፍ ይበልጣል፡፡

በብሪታኒያ የሊንከን ዩኒቨርሲቲ ባልደረባው ፕሮፌሰር ሺጋንግ ዩዌ ‹‹እንደ አንበጣ ካለች አነስተኛ ፍጡር እንኳ ብዙ መማር ይቻላል›› ላሉት ማረጋገጫ የሚጠቅሱት ሳይንቲስቶች የአንበጣን ዓይንና የነርቭ ሴል በመኮረጅ ራዳር ወይም ጨረር የሚጠቀም የተወሳሰበ መሣሪያ ሳያስፈልግ ከፊቱ የመጣበትን ነገር መለየትና መሸሽ የሚችል በኮምፒውተር የሚመራ ተንቀሳቃሽ ሮቦት ለመሥራት መቻላቸውን ነው፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...