የአዋሽ ባንክ ባለአክሲዮኖች የባንኩን ካፒታል ከሦስት ቢሊዮን ብር ወደ ስድስት ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ዛሬ ኅዳር 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በተካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ወሰኑ፡፡ ይህም በአገሪቱ ካሉት 16 የግል ባንኮች ከፍተኛው ነው፡፡
በ2009 ዓ.ም. ባንኩ ከታክስ በፊት 1.4 ቢሊዮን ብር ያተረፈ ሲሆን፣ ጠቅላላ ሀብቱም 42 ቢሊዮን ብር እንደደረሰ ታውቋል፡፡ ይህም በኢትዮጵያ ከሚገኙ የግል ባንኮች ከፍተኛው ነው፡፡