Friday, April 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች ግጭት የተሳተፉ 103 ተጠርጣሪዎች ታሰሩ

በሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች ግጭት የተሳተፉ 103 ተጠርጣሪዎች ታሰሩ

ቀን:

በሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች በተከሰተው ግጭት የተሳተፉ 103 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር እንደዋሉ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትሩ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ዛሬ ኅዳር 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በጽሕፈት ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናገሩ፡፡

ከኦሮሚያ ክልል 98 ተጠርጣሪዎች የተያዙ ሲሆን፣ የክልሉ ፀጥታ ኃይሎች 54 ያህሉን በቁጥጥር ሥር ሲያውሏቸው የተቀሩት በፌዴራል ፖሊስ ነው የተያዙት፡፡

ከሶማሌ ክልል በግጭቱ የተሳተፉ 29 ተጠርጣሪዎች ቢኖሩም፣ እስካሁን የተያዙት ግን አምስት ብቻ እንደሆኑ ሚኒስትሩ በመግለጫቸው ተናግረዋል፡፡ አምስቱን ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው የፌዴራል ፖሊስ እንደሆነ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በ2010 ዓ.ም. በሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች የተከሰተው ግጭት ከሞላ ጎደል ተረጋግቷል ሲሉ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡ ሚኒስትሩ ግጭቱ የተረጋጋ ቢሆንም ግን መቶ በመቶ ቆሟል ለማለት ግን እንደማይቻልም አስረድተዋል፡፡

በባሌ፣ ቦረናና ጉጂ አካባቢዎች ግጭቶች ተከስተው እንደነበር የገለጹት ሚኒስትሩ፣ የሰው ሕይወት እንደጠፋና ንብረትም እንደወደመ ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...