ለ17ኛ ጊዜ ዛሬ ኅዳር 17 ቀን 2010 ዓ.ም. በተደረገው የታላቁ ሩጫ ላይ የተሳተፉ ሁለት ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉ ታወቀ፡፡ ለጊዜው ስማቸው ያልታወቁት ሟቾች አንደኛው ጎተራ አካባቢ ወድቆ በዚያው ሕይወቱ ሲያልፍ፣ ሁለተኛው ግን ሩጫውን ጨርሶ ከገባ በኋላ ወድቆ ወደ ዘውዲቱ ሆስፒታል ለሕክምና ቢወሰድም በዚያው ሕይወቱ ሊያልፍ ችሏል፡፡
የዘንድሮው ታላቁ ሩጫ ከ44 ሺሕ በላይ ተሳታፊዎችን ያሳተፈ ሲሆን፣ ሩጫው ከጊዜ ወደ ጊዜ የጎብኚዎችን ቀልብ እየሳበ የመጣ የጎዳና ላይ ሁነት መሆን ጀምሯል፡፡