Friday, March 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትከፌዴሬሽኑና ከአሠልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ የሚጠበቀው

ከፌዴሬሽኑና ከአሠልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ የሚጠበቀው

ቀን:

የአሠልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ መሰናበት ይፋ ከተደረገ በኋላ የሚተካቸው አሠልጣኝ ማን ይሆናል? የሚለው ሲያነጋግር ቆይቷል፡፡ በመጨረሻው ውጤት መሠረትም የደደቢቱ አሠልጣኝ ኢንስትራክተር ዮሐንስ ሳሕሌ ተሰማ አዲሱ የብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ሆነው መሰየማቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በያዝነው ሳምንት መጀመርያ ይፋ አድርጓል፡፡ ሆኖም አሠልጣኙ ከብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ጋር ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ያልጨረሷቸው ጉዳዮች እንዳሉ ተሰምቷል፡፡ ይኼውም ከደመወዝና ተዛማች ጥቅማ ጥቅሞች ጋር የተያያዙ ስለመሆኑም ታውቋል፡፡

ማተሚያ ቤት እስከገባንበት ሰዓት ድረስ ጉዳዩ እልባት ያላገኘ ሲሆን ይፋዊ መግለጫ ከመስጠት ተቆጥረዋል፡፡ ሆኖም የእሳቸው ብሔራዊ ቡድኑን መረከብ ሁሉንም ወገን አላስማማም፡፡ በተለይ የአገር ውስጥ አሠልጣኞችና ተያያዥነት ያላቸው ባለሙያዎች ቅሬታ እንዳደረባቸው ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡ በሌላው ወገን አሠልጣኙ ዕድሜያቸው ከ17 ዓመት በታች ወጣቶች ብሔራዊ ቡድንና በደደቢት ክለብ ያሳዩት ለውጥ ለብሔራዊ ቡድን እንዲታጩ ምክንያት መሆኑን የሚገልጹ ተንታኞችም በመገናኛ ብዙኃን ተደምጠዋል፡፡

ምንም እንኳ በአንዳንድ ወገኖች ዘንድ አሠልጣኙ ብሔራዊ ቡድን ለመያዝ የሚያስችል ልምድ የሌላቸው ስለመሆናቸው ሲገለጽ ቢደመጥም፣ በሌላ ወገን ደግሞ አቶ ዮሐንስ በተጨዋችነት ከክለብ እስከ ብሔራዊ ቡድን እንዲሁም ለአሠልጣኝነት የሚያበቃቸውን ሥልጠና በብራዚልና በአውሮፓ የተለያዩ አገሮች ሥልጠና እንደወስዱ፣ በአሜሪካ በተለያዩ አካዴሚዎች በዳይሬክተርነትና በአሠልጣኝነት ከመሥራታቸውም በላይ በአካዴሚክ ደረጃ ቢሆንም ሁለተኛ ዲግሪያቸው በስፖርት አመራርና ሥልጠና መሥራታቸውን በመጥቀስ ለብሔራዊ ቡድኑ የሚመጥን አቅም እንዳላቸው የሚከራከሩ አሉ፡፡

የተሰናባቹ አሠልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ ዕጣ ፈንታ አቶ ዮሐንስ እንዳይገጥማቸው የሰጉ አስተያየት ሰጪዎች ፌዴሬሽኑ ላይ አነጣጥረዋል፡፡ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ መሠረታዊ የሚባል የመዋቅር ለውጥ መደረግና መተግበርም እንዳለበት፣ የእግር ኳስ አደረጃጀትና አሠራር እንዲስተካከልና ዓለም አቀፋዊ መመዘኛዎች ላይ ተመርኩዞ  እንዲሠራም ያሳስባሉ፡፡

ከፖርቹጋላዊው አሠልጣኝ ስንብት ጋር ተያይዞ በተለይ የብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ብሔራዊ ቴክኒክ ኮሚቴና ቴክኒክ ዲፓርትመንት የሙያተኞች ስብስብ በአቅምና ችሎታ ላይ የተመሠረተ እንዳልሆነ፤ ይህንኑ ፌዴሬሽኑ እንዲያጠራና ትክክለኛውን መስመር መከተል እንዳለበት ጭምር ሲነገር ቆይቷል፡፡ እየተነገረም ይገኛል፡፡

የብሔራዊ ቴክኒክ ኮሚቴና ቴክኒክ ዲፓርትመንቱ ኃላፊነት ከብሔራዊ ቡድኑ አልፎ የክለቦችን መዋቅራዊ አደረጃጀት ምን መምሰል እንዳለበት አቅጣጫዎችን የማመልከት አቅምን ያማከለ ሊሆን እንደሚገባ፣ እስከዛሬም የብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ትልቁ ክፍተትና ድክመት እዚሁ ክፍል ላይ ሆኖ የቀጠለበት ሁኔታ ስላለ፣ ይኼ ባልጠራበት ደግሞ አሁን እየመጡ ያሉት አሠልጣኝም ሆነ ከሌሎች ውጤት መጠበቅ አስቸጋሪ እንደሚሆን ይነገራል፡፡ ፌዴሬሽኑን ካለፈው አሠራርና ትምህርት ወስዶ የቆየውን ኋላ ቀር አሠራር ማስተካከል እንደሚጠበቅበትም እምነት ተይዟል፡፡

ሚያዝያ 19 ቀን 2007 ዓ.ም. በኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል የስንብት ግብዣ የተደረገላቸው የቀድሞ አሠልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ፣ በአገሪቱ የሚገኙ የእግር ኳስ አሠልጣኞችና ባለሙያዎች እግር ኳሱን የኅብረተሰቡን ያህል የሚወዱት ከሆነ እርስ በርስ መጎነታተሉንና  መተቻቸቱን ወደ ጎን አስቀርተው ተመካክረውና ተጋግዘው እንዲሠሩ ጥሪ ማድረጋቸውም ተሰምቷል፡፡ ማሪያኖ በኃላፊነት በነበሩበት ወቅት ለብሔራዊ ቡድኑ ጥንካሬ በተለይም ከብሔራዊ ቴክኒክ ኮሚቴውም ሆነ ቴክኒክ ዲፓርትመንቱ ምንም ዓይነት ሙያዊ ድጋፍ እንደማይደረግላቸው፣ በዲፓርትመንቱ የነበሩ ብዙዎቹ ባለሙያዎች እሳቸውን በሚመለከቱበት ሰዓት ጀርባቸውን ሰጥተዋቸው ይሄዱ እንደነበርም መናገራቸው መዘገቡ ይታወሳል፡፡

ከአቶ ዮሐንስ ሳሕሌ ቅጥር ጋር ተያይዞ የብሔራዊ ፌዴሬሽኑ አመራሮች ላይ ወቀሳና ትችቶች ሲሰነዘሩ ተደምጧል፡፡ ይህንኑ አስመልከቶ የብሔራዊ ቡድኑ የቀድሞ አሠልጣኝ፣ አመራሩ የአሠልጣኞችን ቅጥር መፈጸም እንደሚችል ይህም በየትኛውም አገር የተለመደ አሠራር መሆኑን መናገራቸውም ተሰምቷል፡፡ ቁም ነገር ሁሉም ኢትዮጵያውያን አሠልጣኞችና ባለሙያዎች ሊያስጨነቃቸው የሚገባው ምን ሠራን? የሚለው ሊሆን እንደሚገባ ጭምር መጠቆማቸው ተደምጧል፡፡ የብሔራዊ ቡድኑ አዲሱ አሠልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ ቅጥር በመርሕ ደረጃ ቢጠናቀቅም ከንትራትና ተያያዥ ጉዳዮች ባለመጠናቀቃቸው ምክንያት ምንም ማለት እንደማይፈልጉ ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...