Friday, March 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትዳሸን ቢራ ለባህር ዳር ስታዲየም 50 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

ዳሸን ቢራ ለባህር ዳር ስታዲየም 50 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

ቀን:

በክልሎች ከተገነቡ ዘመናዊ ስታዲየሞች ፋና ወጊ የሆነው የባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የማጠናቀቂያ ግንባታውን ለማከናወን ይረዳው ዘንድ የ50 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ከዳሸን ቢራ አክሲዮን ማኅበር አገኘ፡፡ ፋብሪካው ለባህር ዳር ከተማ እግር ኳስ ቡድን ተጨማሪ የአንድ ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡

የዳሸን ቢራ አክሲዮን ማኅበር በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ ቅዳሜ የካቲት 18 ቀን 2009 ዓ.ም. በባህር ዳር በተዘጋጀው ሥነ ሥርዓት የዳሸን ቢራ ፋብሪካ አክሲዮን ማኅበር የተዘጋጀው የገንዘብ ድጋፍ ለክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሙሉዓለም ጌታሁን አስረክቧል፡፡

ምክትል ቢሮ ኃላፊው አቶ ሙሉዓለም የገንዘብ ርክክብር ሥነ ሥርዓቱ ከተከናወነ በኋላ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ዳሸን ቢራ አክሲዮን ማኅበር ለባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ከምሥረታው ጀምሮ ዕውን መሆን የተጫወተው ሚና ከፍተኛ መሆኑን መናገራቸው በመግለጫው ተካቷል፡፡ ገንዘቡም ለስታዲየሙ የግንባታ ሒደት ማለትም በቅርቡ ለሚጀመረው የስታዲየሙ ዘመናዊ መቀመጫ ወንበር የሚውል እንደሆነ መናገራቸው ታውቋል፡፡  

የዳሸን ቢራ ፋብሪካ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ ማሩ በበኩላቸው፣ ፋብሪካው ከተመሠረተ ጊዜ ጀምሮ በአገሪቱ ሁለንተናዊ የማኅበራዊ ልማቶች ላይ ቀጥተኛ ተሳታፊ በመሆን ባለፉት 16 ዓመታት ብቻ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ አድርጓል ማለታቸውም ተገልጿል፡፡ እንደ መግለጫው በተለይም በስፖርቱ ዘርፍ ክለቦችን በማቋቋምና በመደገፍ፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራ ግንባታዎችን በማገዝ፣ እንዲሁም ስፖርታዊ ሁነቶችን ስፖንሰር በማድረግ ያደረገው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑ ጭምር ተነግሯል፡፡

ፋብሪካው ለስታዲየሙ ግንባታ ማጠናቀቂያ ከሰጠው 50 ሚሊዮን ብር በተጨማሪ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ከፍተኛ ሊግ (ሱፐር ሊግ) በመወዳደር ላይ ለሚገኘው የባህር ዳር ከተማ እግር ኳስ ክለብ የአንድ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረግ መቻሉም በመግለጫው ተካቷል፡፡

  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...