Sunday, April 14, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊአብዛኞቹ የዘላቂ ልማት ግቦች እንዲሳኩ የሥርዓተ ምግብ ችግሮች መፈታት እንዳለባቸው ተገለጸ

አብዛኞቹ የዘላቂ ልማት ግቦች እንዲሳኩ የሥርዓተ ምግብ ችግሮች መፈታት እንዳለባቸው ተገለጸ

ቀን:

ለሁለንተናዊ ዕድገት አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል ተብለው በመተግበር ላይ ከሚገኙት 17 ዘላቂ ልማት ግቦች መካከል 12ቱ የሚሳኩት የሥርዓተ ምግብ ችግሮች ሲፈቱ ብቻ መሆኑን በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የእናቶችና ሕፃናት ጤና ዳይሬክቶሬት፣ የሥርዓተ ምግብ ኬዝ ቲም የሥርዓተ ምግብ ባለሙያ አስታወቁ፡፡

በሕፃናት ወተት አያያዝና በአጠቃላይ በሥርዓተ ምግብ ዙሪያ የካቲት 21 ቀን 2009 ዓ.ም. በተካሄደው የግማሽ ቀን ዐውደ ጥናት ላይ ባለሙያዋ ወይዘሮ ፍሬዘር አበበ እንደገለጹት፣ የሥርዓተ ምግብ ችግሮች መፈታት በ12ቱ የልማት ግቦች ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ለቀሩት አምስት ዘላቂ የልማት ግቦች መሳካት አስተዋጽኦ ያበረክታሉ፡፡

አገሪቱ በምግብ እጥረትና ከመጠን በላይ በሚመጣው ውፍረት ተጠቂ መሆኗን ገልጸው፣ ይህም ከአመጋገብ መዛባት ጋር የመጣ ችግር መሆኑን አስረድተዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

መንግሥት ይህን ችግር ለመቅረፍ የአምስት ዓመት የብሔራዊ ሥርዓተ ምግብ ፕሮግራም የቀረፀ ሲሆን፣ ፕሮግራሙም ወደ ተግባር ከገባ አንድ ዓመት ሆኖታል፡፡

ሁለተኛውን ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ታሳቢ በማድረግ፣ በመጀመሪያው አምስት ዓመት ብሔራዊ ሥርዓተ ምግብ ፕሮግራም አፈጻጸም ላይ የተገኙትን መልካም ተሞክሮዎችና የታዩ ክፍተቶችን እንደ ግብዓት በመውሰድ የተቀረጸውን ሁለተኛውን ፕሮግራም የማስፈጸም ኃላፊነት የወደቀው በ13 ሴክተር መሥሪያ ቤቶች ላይ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

እንደ ባለሙያዋ፣ አገሪቱ የሕፃናትን የመቀንጨር ችግር በ2022 ዓ.ም. ለማስወገድም በሰቆጣው ስምምነት መሠረት እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ነች፡፡ 

አዳግ ኢንተርናሽናል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ባካሄደው በዚሁ ዐውደ ጥናት ላይ ከኢትዮጵያ የምግብ፣ የመድኃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን (ኤፍኤምሃካ)፣ ከኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅትና ከኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን የቀረቡና በምግብ ማስታወቂያዎች ዙሪያ ያጠነጠኑ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

ጽሑፎቹ እንደሚያሳዩት፣ የታዳጊ ሕፃናት ምግቦች የሚባሉት ከስድስት ወር እስከ ሦስት ዓመት ለሆኑ ሕፃናት ብቻ ታስበው የሚዘጋጁ ናቸው፡፡

አንዳንድ ማስታወቂያዎች ካለማወቅ ለሕፃኑ ይህ ምግብ ከተሰጠው ሌላ ምግብ አያስፈልገውም እያሉ እንደሚያስተዋውቁ፣ የኤፍኤምሃካ የማስታወቂያ ቁጥጥር መመሪያ ግን ይህ ዓይነቱን ማስታወቂያ አጥብቆ እንደሚከለክል ተገልጿል፡፡፡

በትክክለኛ ሰነድና ማስረጃ ያልተረጋገጠ፣ ‹‹እንደ ብቸኛ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ ከዚህ ቀደም ያልነበረ፣ የሁሉም ምርጫ፣ ለሁሉም ተስማሚ፣ ልዩ፣ አንደኛ፣ ተቀባይነትን ያገኘ›› ወዘተ የሚባሉ የተጋነኑና አበላላጭ ይዘት ያላቸው ቃላት ወይም ምስል መጠቀም መመሪያው ይከለክላል፡፡

የሕፃናት ምግብ ቸርቻሪዎችንና ሱፐርማርኬቶችን የመቆጣጠር ሥልጣንና ኃላፊነት በክልል ተቆጣጣሪዎች ላይ የተጣለ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ የምግብ፣ የመድኃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣንም ለዚሁ ተግባር የሚውሉ ሞዴል መመሪያዎችን አዘጋጅቶ አሠራጭቷል፡፡

ከዚህ አንፃር ማንኛውም የሕፃናትና ታዳጊ ምግብ መሸጥ ያለበት በተለየ ሱቅ ላይ እንደሆነ፣ በባለሙያም መያዝ እንዳለበት ተመልክቷል፡፡

ማንኛውም ተጠቃሚ ምርቶችን ከገበያ ሲገዛ የሚገዛበትን ቦታ ሕጋዊነት ማረጋገጥ፣ የሚገዛው ምርት በአግባቡ መከማቸቱን፣ መደርደሪያ ላይ መሆኑን፣ መደርደሪያውም ከመሬት ቢያንስ 50 ሳንቲ ሜትር ከፍ ማለቱንና ከጣሪያውም የዚህኑ ያህል መራቁን መተፋፈግ በማይፈጥር አግባብ መከማቸቱን ማረጋገጥ አለበት፡፡ ገላጭ ጽሑፉ የሚጻፍበት ቋንቋ አማርኛ ወይም እንግሊዝኛ መሆን እንዳለበት፣ በተጨማሪም የምርቱ ስም፣ አምራቹ የት እንደሚገኝ፣ የተመረተበትና የመጠቀሚያው ጊዜ የሚያልፍበት ቀን እንዲሁም የደረጃ ምልክት በጽሑፉ መኖሩን ማረጋገጥ አስፈላጊ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአብዮቱ ያልተዘጉ ዶሴዎች

‹ዳኛው ማነው› ሒሳዊ ንባብ - ሐሳብና ምክንያታዊነት በዚያ ትውልድ...

የ ሳ ም ን ቱ ገ ጠ መ ኝ

በዚያን ሰሞን የሹክሹክታ ወሬ ደርቶ ነው የሰነበተው፡፡ የአገራችን ልጆች...

በፓሪስ ኦሊምፒክ ዝግጅት ዙሪያ

‹‹ድንጋይ ላይ ሠርተን እንዴት ነው ውጤት እንድናመጣ የሚጠበቀው?›› የኦሊምፒክ አትሌቶች በደረጀ...