Tuesday, December 5, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

«ዋ! . . . ያቺ ዓድዋ»

ትኩስ ፅሁፎች

የፀጋዬ ገብረመድኅን «እሳት ወይ አበባ» (1966) ከተሰኘው የሥነ ግጥም መድበሉ ውስጥ የሚገኝ ስለ ዓድዋ የዘከረበት  ከፊሉ እነሆ፡፡ 

. . . . ዋ!

ዓድዋ የዘር ዐፅመ ርስትዋ 

የደም ትቢያ መቀነትዋ 

በሞት ከባርነት ሥርየት 

በደም ለነፃነት ስለት 

አበው የተሰውብሽ ለት፤ . . . 

ሲያስተጋባ ከበሮዋ 

ሲያስገመግም ዳኘው መድፍዋ

ያባ መቻል ያባ ዳኘው 

ያባ ነፍሶ ያባ ቃኘው 

ያባ በለው በለው ሲለው 

በለው – በለው – በለው!

       ዋ! . . . ዓድዋ . . . 

* * *

የመላጦች ውድድር

ባለፈው ሳምንት አጋማሽ ላይ በጃፓኗ ከተማ ሱሩታ የመላጦች ውድድር ተካሂዶ እንደነበር የሮይተርስ ዘገባ አመለከተ፡፡ ለውድድሩ ሰላሳ የሚሆኑ መላጦች ተገኝተው ነበር፡፡ በተለይም የከተማዋ መላጦች ማኅበር በርካታ አባላቶቹን አሳትፎ ነበር፡፡ ሰሳኪ የተባለ ተወዳዳሪ ‹‹መላጣ በመሆኔ እኮራለሁ መመለጥ የጀመርኩት የአርባ ዓመት ጎልማሳ ሳለሁ ነው፤›› በማለት የመሰል መላጦች ክበብ በከተማዋ መኖር ለሱ ትልቅ ነገር እንደሆነ ይናገራል፡፡ እ.ኤ.አ. በ1989 የተቋቋመው ማኅበሩ ከመላ አገሪቱ 65 አባላትን ማፍራት የቻለ ሲሆን መመለጥን ሰዎች በአዎንታዊ መንገድ እንዲያዩት ይሠራል፡፡

* * * *

ያመለጠው በሬ የኒዮርክ ፖሊሶችን በሥራ ወጠረ

ማክሰኞ ዕለት ከቄራ ያመለጠ አንድ በሬ በኒዮርክ ጎዳና ላይ ነፍሴ አውጪኝ በሚል ዓይነት በዚህ በዚያ እያለ ሲሯሯጥ ደቂቃዎችን ማሳለፍ በአካባቢው ፖሊስ ላይ ከፍተኛ ሥራ ሆኖ ነበር፡፡ ይህ የበሬውና የፖሊስ አባሮሽ በቪዲዮ የተቀረጸ ሲሆን ፖሊስ በሬውን በተደጋጋሚ ለመያዝ ያደረገው ጥረት እንዴት እንዳልተሳካ ያሳያል፡፡ ፖሊስ በመኪና የቱንም ያህል በሬውን ለማሳደድ ቢሞክር መያዝ ግን ቀላል አልሆነለትም ነበር፡፡ ይህ አባሮሽ ለሁለት ሰዓት ያህል ቀጥሎ በሬው በመጨረሻ ከአንድ ሰው መኖሪያ ግቢ መግባቱ የፖሊሶችን ሥራ ቀላል አድርጎላቸዋል፡፡ ይህ መኖሪያ በሬው ካመለጠበት ቄራ 2.4 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን በሬውን መጀመሪያ ማደንዘዣ በመውጋት ፖሊስ ሊይዘው መቻሉ ተዘግቧል፡፡ ኋላም በሬው መሞቱ ተገልጿል፡፡ በበሬው ምንም ዓይነት ሰዎች ላይ የደረሰ ጉዳትም አልነበረም፡፡

* * * * * * *

‹‹የግጭት አፈታትና አያያዝ ጥበብ›› እና ሌሎችም

በቅርቡ ለአንባቢ ከበቁ መጻሕፍት መካከል የዓለሙ አማረ ‹‹የግጭት አፈታትና አያያዝ ጥበብ›› ይገኝበታል፡፡ መጽሐፉ የፖለቲካዊ፣ የማኅበራዊ፣ የኢኮኖሚያዊና የሃይማኖታዊ ግጭቶች መንስኤና መፍትሔዎችን የሚዳስስ ሲሆን፣ በ81 ብር እየተሸጠ ነው፡፡ በተያያዥ ‹‹የእግዜር ድርሰት›› የተሰኘው የይባቤ አዳነ መጽሐፍ በ196 ገጽ የቀረበ ሲሆን፣ በ61 ብር ቀርቧል፡፡ ‹‹እኩያና ዕቡያን›› የተሰኘው የጥላሁን ገብረ ክርስቶስ መጽሐፍ ልዩ ልዩ ማኅበረሰባዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ሲሆን፣ በ50 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡

* * * * * * *

የኪነጥበብ ዝግጅት

ዝግጅት፡- ዜማ ብዕር ኢትዮጵያ የሴቶች የሥነ ጽሑፍ ማኅበር የተመሠረተበትን አሥረኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የኪነ ጥበብ ዝግጅቶች ይቀርባሉ፡፡

ቀን፡- የካቲት 25 ቀን 2009 ዓ.ም.

ሰዓት፡- 8፡00

ቦታ፡- ራስ ሆቴል

አዘጋጅ፡- ዜማ ብዕር ኢትዮጵያ የሴቶች የሥነ ጽሑፍ ማኅበር

******

የተማሪዎች ምርቃትና ሽልማት

ዝግጅት፡- ቶም የቪዲዮግራፊና ፎቶግራፊ ማሠልጠኛ ተቋም በ16ኛ ዙር 500 ተማሪዎችን ያስመርቃል፡፡ በተመራቂዎች የተሠሩ ፊልሞች በስምንት ዘርፍ ተወዳድረው ‹‹ቶም አዋርድ›› የተሰኘ ሽልማት ያገኛሉ፡፡

ቀን፡- የካቲት 25 ቀን 2009 ዓ.ም.

ሰዓት፡– 2፡30

ቦታ፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር

አዘጋጅ፡- ቶም የቪዲዮግራፊና ፎቶግራፊ ማሠልጠኛ

*****

የአልበም ምርቃት

ዝግጅት፡- ሜሮን ኩርፋ ‹‹ሜሪ›› የተሰኘ የመጀመሪያ አልበሟን ለቃለች፡፡ 13 ባህላዊና ዘመናዊ ሙዚቃዎች ያሉት አልበሙ፣ በግጥምና ዜማ ኢዮኤል ብርሃኔ፣ ጌትሽ ማሞ፣ አቤል ሙልጌታና ሌሎችም ባለሙያዎችን ያሳተፈ ሲሆን፣ ማስተሪንጉ በአበጋዝ ክብረወርቅ ሺኦታ ተሠርቷል፡፡

 

 

 

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች