Monday, October 2, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

በኢትዮ ጂቡቲ ምድር ባቡር አክሲዮን ኩባንያ ምሥረታ ላይ የሚመክር የመሪዎች ጉባዔ ሊካሄድ ነው

ተዛማጅ ፅሁፎች

የኢትዮ ጂቡቲ ምድር ባቡር አክሲዮን ኩባንያን ለመመሥረትና በሌሎች የሁለቱ አገሮች ኢኮኖሚያዊ መስተጋብሮች ላይ የሚመክር የመሪዎች ጉባዔ በመጋቢት ወር ሊካሄድ ነው፡፡

ከውይይቱ ጎን ለጎንም የጂቡቲ ፕሬዚዳንት እስማኤል ዑመር ጌሌ በአዲስ አበባ ኦፌሴሊያዊ ጉብኝት እንደሚያደርጉም ታውቋል፡፡

ጉባዔው በመሪዎች ደረጃ እንዲከናወን የጠየቁት የጂቡቲ ፕሬዚዳንት ሲሆኑ፣ ጥያቄያቸውንም በገንዘብ ሚኒስትራቸው በኩል ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ባለፈው ሳምንት እንዳቀረቡ የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡

የሚቋቋመው የኢትዮ ጂቡቲ ምድር ባቡር የሁለቱ አገሮች አክሲዮን ኩባንያ መሆኑን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ የሁለቱ አገሮች ድርሻ የሚሆነው በይዞታቸው በሚገኝ መሠረተ ልማት ልክ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል፡፡

ኩባንያውን ለመመሥረት እንዲረዳ የውጭ አማካሪ ተቀጥሮ የባለአክሲዮኖች ስምምነት፣ የመተዳደሪያ ደንብና የሁለትዮሽ ስምምነት ሰነዶች ተዘጋጅተው ለጂቡቲ መንግሥት ባለሥልጣናት መላኩ ታውቋል፡፡

በእነዚህ ሰነዶች ላይ ከጂቡቲ መንግሥት ይሁንታ መገኘቱንና በመጪው የመሪዎች ጉባዔም ይፋዊ ስምምነት እንደሚፈረም ምንጮች አስረድተዋል፡፡

በአዲስ አበባ ጂቡቲ መስመር ላይ ትልልቅ መጋዘኖችና ሊበላሹ ለሚችሉ ገቢ ዕቃዎችና ወደ ውጭ ለሚላኩ የግብርና ምርቶች ማቀዝቀዣ ደረቅ ወደብ እንደሚኖርም ለማወቅ ተችሏል፡፡

በመሪዎቹ ጉባዔ ላይ ከድሬዳዋ ጂቡቲ እየተገነባ ያለውን የአስፋልት መንገድ በተመለከተ፣ እንዲሁም የሕዝብ ትራንስፖርት በሁለቱ አገሮች መካከል ለመጀመር ስምምነት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከአፋር ክልል ዳሎል እስከ ጂቡቲ አዲሱ ወደብ ታጁራ የሚገነባውን መንገድ አስመልክቶም ውይይት ይደረጋል ተብሏል፡፡

የጂቡቲ ወደብ የኢትዮጵያን ገቢና ወጪ ምርቶች የማስተናገድ አቅሙን ለመጨመር በሚችልበት ሁኔታ ላይ ምክክር እንደሚደረግ ምንጮች ገልጸዋል፡፡  

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች