Wednesday, May 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ሥነ ፍጥረት‹‹የጉንዳን አንገት››

‹‹የጉንዳን አንገት››

ቀን:

ጉንዳንን የአለቃ ደስታ ተክለወልድ ዐዲስ ያማርኛ መዝገበ ቃላት ‹‹ተናካሽ፣ ተቆናጣጭ ሥጋና ቅባት ወዳድ›› ብሎ ብቻ አይፈታውም፡፡ ሌላም ያክልበታል፡፡ ጥሬ እህል ለቀለቡ ባፉ እየያዘ ወደጉድጓድ የሚያገባ፣ የሚከት የሚጐደጉድ ጥቁር ተንቀሳቃሽ፤ እንዳይነቅዝበት እየከካ በውጭ በፀሓይ ላይ የሚያሰጣ፣ አግዝ (ገብረ ጉንዳን)፡፡ መልከ ቀይም አለው፤ ማረ በላ፣ ፈጣን ይሉታል፡፡

ጉንዳን በሴት አንቀጽ ከምሳሌያዊ አነጋገር አትጠፋም፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞን በመጽሐፉ ‹‹አንተ ታካች፣ ወደ ገብረ ጉንዳን ሂድ፤ መንገድዋንም ተመልክተህ ጠቢብ ሁን፤›› ያለውን ያስተውሉና የተጠበቡ በምድሪቱ ሞልተዋል፡፡ ‹‹ንቁ!›› የተሰኘ አንድ የባሕር ማዶ መጽሔት በድረ ገጹ የሜካኒካል ምሕንድስና ባለሙያዎች፣ ጉንዳኖች ባላቸው ከአካላቸው ብዙ እጥፍ የሚበልጥ ክብደት የመሸከም ችሎታ ይደነቃሉ ሲል ከትቧል።

በዩናይትድ ስቴትስ በሚገኘው የኦሃዮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ያሉ መሐንዲሶች፣ ጉንዳኖች ያላቸውን ይህን ችሎታ ለመረዳት ሲሉ የኮምፒዩተር ሞዴሎችን አዘጋጅተዋል፤ ሞዴሎቹ የጉንዳኖቹን አካል አወቃቀርና ባሕርይ እንዲሁም እንቅስቃሴ የሚያሳዩ ናቸው። ሞዴሎቹ የተሠሩት የጉንዳኖቹን ውስጣዊ የአካል ክፍል የሚያሳይ የራጅ ምስል (ረቂቅ ሲቲ ስካን) እና ጉንዳኖች ከባድ ሸክም ሲሸከሙ ኃይላቸውን የሚጠቀሙበትን መንገድ የሚያሳዩ ምስሎችን በመጠቀም ነው።

- Advertisement -

የጉንዳኖች አንገት ትልቅ ሚና አለው፤ ምክንያቱም አንድ ጉንዳን በአፉ የሚይዘው ከባድ ሸክም ሙሉ ክብደት የሚያርፈው አንገቱ ላይ ነው። በጉንዳኑ አንገት ውስጥ የሚገኙ ለስላሳ ሕብረ ሕዋሳት በደረቱ አካባቢ (አካላቱ) እና በጭንቅላቱ ላይ ካሉት ጠንካራ ድጋፍ ሰጪ አጥንቶች ጋር የተቆላለፉ ናቸው፤ ይህም በታጠፉ እጆች ላይ ጣቶች ከሚቆላለፉበት ሁኔታ ጋር የሚመሳሰል ነው።

‹‹ይህ መቆላለፍ ያለው ንድፍና አወቃቀር፣ የአንገቱ መገጣጠሚያ ለሚያከናውነው ተግባር ወሳኝ ነው፤›› በማለት ከተመራማሪዎቹ አንዱ ይናገራል። ‹‹የአንገቱ መገጣጠሚያ ይበልጥ ጥንካሬ እንዲኖረው ያደረገው ነገር ጠንካራና ለስላሳ የአካል ክፍሎቹ የተያያዙበት መንገድ ሳይሆን አይቀርም፤ ምናልባትም መገጣጠሚያው ከባድ ሸክም እንዲሸከም የሚያስችለው ይህ ንድፍ ሊሆን ይችላል።›› የጉንዳን አንገት እንዴት እንደሚሠራ በግልጽ መታወቁ ለሰው ሠራሽ ሮቦቶች ንድፍ መሻሻል አስተዋጽኦ ሊያበረክት እንደሚችል ተመራማሪዎች ተስፋ ያደርጋሉ።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የማዳበሪያ አቅርቦትና ውጣ ውረዱ

በቅፅል ስሙ “The Father of Chemical Warfare” እየተባለ የሚጠራው...

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የትርፍ ምጣኔውን ከ70 በመቶ በላይ አሳደገ

ከሁለቱ መንግሥታዊ ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ...