Friday, September 22, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ብሔራዊ ባንክ ሁሉም የፋይናንስ ተቋማት የኮምፒዩተር የደኅንነት ሥርዓት እንዲዘረጉ አዘዘ

ተዛማጅ ፅሁፎች

  • ሥርዓቱን ለመዘርጋት ከ80 ሚሊዮን ዶላር በላይ ያስወጣል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሁሉም የአገር ውስጥ ባንኮችና ኩባንያዎች የኢንሹራንስ የኮምፒዩተር ደኅንነት ሥርዓት በተናጠል እንዲያበለፅጉ አዘዘ፡፡

የፋይናንስ ተቋማት ተቆጣጣሪ የሆነው ብሔራዊ ባንክ ሁሉንም የፋይናንስ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች ባለፈው ሳምንት ስብሰቦ በጉዳዩ ላይ በማነጋገር፣ የደኅንነት ሥርዓቱን ከሁለት እስከ አምስት ዓመት ድረስ ተግባራዊ እንዲያደርጉ መመርያ ሰጥቷል፡፡

ተቋማቱ መገንባት የሚጠበቅባቸው የደኅንነት ሥርዓት ቴክኒካዊ (Technical)፣ አካላዊ (Physical) እና አስተዳደራዊ (Administrative) መሆን እንደሚገባው ገለጻ መደረጉን ውይይቱን የተከታተሉ ምንጮች ገልጸዋል፡፡

ቴክኒካዊ የደኅንነት ሥርዓቱ በባንኮቹ የኮምፒዩተር ዳታ ላይ የሚሰነዘሩ የኢንተርኔት ጥቃቶችን ቀድሞ ማሳወቅና መተንተን የሚያስችል እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

አካላዊ የሚባለው የደኅንነት ሥርዓት በየተቋማቱ በሚተከሉ ካሜራዎች የሰዎች አካላዊ እንቅስቃሴን መከታተል የሚያስችል መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ እነዚህ ሁለቱ የደኅንነት ሥርዓቶች በአገር አቀፍ የሳይበር ደኅንነት ደረጃዎች ተግባራዊ መደረግ የሚገባቸው በመሆኑ፣ ኮንትራቱን መስጠት የሚገባቸው የአገር አቀፍ ስታንዳርዱ ባለቤትና ተቆጣጣሪ ለሆነው ለኢትዮጵያ የመረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (INSA) መሆን እንዳለበት ተነግሯቸዋል፡፡

ኮንትራቱን ለኤጀንሲው መስጠቱ ደኅንነትን ከማረጋገጥ ባለፈም በዋጋ ደረጃም የተሻለ እንደሚሆን ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል፡፡

በአጠቃላይ ለሁሉም ባንኮች 80.8 ሚሊዮን ዶላር አጠቃላይ ወጪ የሚጠይቅ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

የመረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተመሳሳይ የኮምፒዩተር ደኅንነት ሥርዓት (Security Operating System) በ30 ሚሊዮን ብር ገንብቶ ባለፈው ዓመት አስረክቧል፡፡    

 

 

 

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች