Saturday, June 10, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትሻለቃ ባሻ ዋሚ ቢራቱ - ስድሳ አራት ዓመት በሩጫ

ሻለቃ ባሻ ዋሚ ቢራቱ – ስድሳ አራት ዓመት በሩጫ

ቀን:

ሩጫ፣ ውርወራና ዝላይን የያዘው ዘመናዊ አትሌቲክስ ኢትዮጵያ ውስጥ መዘውተር የጀመረው በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ጀምሮ በተለይ በትምህርት ቤቶችና በወታደራዊ ክፍሎች እንደሆነ ይነገራል፡፡

በወታደራዊ ክፍሎች ውስጥ ይወዳዳሩ ከነበሩትና ከ1940ዎቹ መገባደጃ ጀምሮ ታዋቂ የሆኑት ሻለቃ ባሻ ዋሚ ቢራቱ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ መነሻቸው ገጠር የሆነው ዋሚ በልጅነታቸው ከዕረኝነት እስከ እርሻ ሥራ ውስጥ በመሰማራት ከአዲስ አበባ ዳርቻ ላይ በሚገኘው ሱሉልታ ኑሮዋቸውን ከወላጆቻቸው ጋር ይመሩ ነበር፡፡ እናታቸው ወ/ሮ ወርቄ አያና በአንድ አጋጣሚ ከአዲስ አበባ ገበያ ቡና፣ ስኳርና ሌላ ፍጆታ ሸምተው ሲመለሱ ቁሳቁስ የተጠቀለለበት ጋዜጣ ላይ የሰፈረው የሚሮጥ ሰው የዋሚን ቀልብ ይይዛል፡፡

‹‹አትሌት ሻለቃ ባሻ ዋሚ ቢራቱ›› በተሰኘው ምጥን መጽሔት (ቡክሌት) እንደተጻፈው፣ ‹‹እኔ አውሬ እያባረርኩ ሚዳቋ፣ ጃርት፣ ጥሪኝና ቆቅ እየያዝኩ ከሰንጋ ፈረስ ጋር ተሽቀዳድሜ እያሸነፍኩ ይህ ሰውማ አያቅተኝም፤›› ብለው የሯጭነት ሐሳባቸውን ቀየሱ፡፡

አዲስ አበባ በመስከረም 1945 ዓ.ም. በመጡበት አጋጣሚ፣ በሁለተኛው ክፍለጦር በወታደርነት መቀጠራቸው ለአትሌቲክስ ሕይወታቸው በር ከፍቶላቸዋል፡፡

አስመራ በሚገኘው ሁለተኛ ክፍለ ጦር በምልምል ወታደሮችና ነባሮች መካከል በተደረገ የ10 ኪሎ ሜትር ሩጫ አሸናፊ መሆናቸው ትኩረታቸው አትሌቲክስ ላይ እንዲሆን አድርጎላቸዋል፡፡  

በ1909 ዓ.ም. በቀድሞ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት በመናገሻ አውራጃ፣ በሱሉልታ ወረዳ በአካኮና መናብቹ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር እንደተወለዱ የሚነገርላቸው ባሻ ዋሚ ቢራቱ መቶኛ ዓመታቸውን መሰንበቻውን አክብረዋል፡፡

64 ዓመታት በአትሌቲክስ ውስጥ ያሳለፉት ዋሚ ቢራቱ በተለያዩ ርቀቶች ካደረጓቸው ውድድሮች መካከል በተለይ በ1950 ዓ.ም. 50 የክፍለ ጦር ተወዳዳሪዎች የተሳተፉበት 42 ኪሎ ሜትር ሩጫ አሸንፈው የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡ በተከታታይ ዓመታትም በአምስት ሺሕ፣ በአሥር ሺሕና በማራቶን ከነአበበ ቢቂላ ጋር በመሮጥ ውጤታማ ነበሩ፡፡ በተለይ በማራቶን የአገሪቱ ቁጥር አንድ ሯጭ ስለነበሩ በሮም ኦሊምፒክ ከአበበ ቢቂላ ጋር እንደሚወዳደሩ ቢጠበቁም፣ ወደ ኦሊምፒክ ለመጓዝ ስድስት ቀናት ሲቀራቸው በደረሰባቸው የጤና መታወክ 19 ቦታ ብጉንጅ ስለወጣባቸው ሳይካፈሉ ቀርተዋል፡፡

ዋሚ በሮም ባይሳተፉም ለመጀመሪያ ጊዜ በኦሊምፒክ የተወዳደሩት አበበ ቢቂላና አበበ ዋቅጅራ አንደኛና ሰባተኛ በመሆን ለኢትዮጵያ አኩሪ ውጤት አስገኝተዋል፡፡ በባዶ እግሩ ሮጦ ባሸናፊነት ወርቁን ያጠለቀው አበበ ቢቂላ ‹‹እኔ የዓለም አንደኛ የኢትዮጵያ ግን ሁለተኛ ነኝ፡፡ አንደኛው [ዋሚ] በመታመሙ አልመጣም፤›› በማለት የዋሚ ቢራቱን ታላቅ ሯጭነት መመስከሩ በወቅቱ ተመዝግቧል፡፡   

የ11 ልጆች አባት የሆኑት፣ ዋሚ ቢራቱ በርካታ የልጅ ልጆች ያሏቸው ሲሆን፣ ቅድመ አያትም ሆነዋል፡፡ የረዥም ዕድሜ ቆይታቸው ምስጢር ሩጫን ቀዳሚ ምስክር ያደርጋሉ፡፡ 64 ዓመት በሩጫ መኖራቸው አንዱ ማሳያም እስከ ዓምና ድረስ በተካሄዱት የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ውድድሮች ሳያቋርጡ መወዳደራቸው ነው፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አያሌ የውኃ “ጠርሙሶች”ን በጫንቃ

መሰንበቻውን በአይቮሪ ኮስት መዲና አቢጃን የምትኖር አንዲት ሴት፣ በሚደንቅ...

ወልቃይትን ማዕከል ያደረገው የምዕራባዊያን ጫና

በትግራይ ክልል የተከሰተው የዕርዳታ እህል ዘረፋ የዓለም አቀፍ ተቋማት...

ከቀጣዩ ዓመት በጀት ውስጥ 281 ቢሊዮን ብሩ የበጀት ጉደለት ነው ተባለ

ለቀጣዩ በጀት ዓመት ከቀረበው 801.65 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ በጀት...