Monday, April 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልየኢትዮጵያ ፊልሞች በፌስፓኰ ይሳተፋሉ

የኢትዮጵያ ፊልሞች በፌስፓኰ ይሳተፋሉ

ቀን:

ፌስፓኰ (ፓን አፍሪካን ፌስቲቫል ኦፍ ሲንማ ኤንድ ቴሌቪዥን) እ.ኤ.አ. ከ1969 ጀምሮ በቡርኪናፋሶ እየተካሄደ ያለ የፊልም ፌስቲቫል ሲሆን፣ አፍሪካዊ ፊልሞችን በማወዳደርና በማስተዋወቅ ስመ ጥር ከሆኑ ፓን አፍሪካን ፌስቲቫሎች አንዱ ነው፡፡ ፌስቲቫሉ በአፍሪካውያን ባለሙያዎች የተሠሩ ፊልሞችን አወዳድሮ በመሸለምና ለዕይታ በማብቃትም ተጠቃሽ ሲሆን፣ ዘንድሮ በዚህ ፌስቲቫል በሦስት ዘርፎች ሦስት የኢትዮጵያ ፊልሞች ይሳተፋሉ፡፡ እነዚም በፊቸር ፊልም ዘርፍ የክንፈ ባንቡ ‹‹ፍሬ››፣ በአጭር ፊልም የማንተጋፍቶት ስለሺ ‹‹ግርታ›› እንዲሁም የያሬድ ዘለቀ ‹‹ላምብ›› ናቸው፡፡

ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሩዋንዳ፣ ኬንያ፣ ቡርኪናፋሶ፣ ቤኒን፣ ጋናና ሌሎችም የአፍሪካ አገሮች የተውጣጡ ፊልሞች የፌስቲቫሉ ተካፋይ ይሆናሉ፡፡ ፌስቲቫሉ ከጥር 19 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ ለአንድ ሳምንት ይካሄዳል፡፡ የ‹‹ፍሬ›› ደራሲና አዘጋጅ ክንፈ ባንቡ ለሪፖርተር እንደገለጸው፣ እሱና ከፊልሙ መሪ ተዋንያን አንዷ የ14 ዓመቷ ኤንዋ ብዙነህ ወደ ቡርኪናፋሶ ጥር 17 ቀን 2009 ዓ.ም. ለማቅናት እየተሰናዱ ነው፡፡

በየሁለት ዓመቱ በሚካሄደው ፌስቲቫል ለመሳተፍ ካመለከተ በኋላ ፊልሙ ምርጥ 20 ውስጥ መግባት እንደቻለ ክንፈ ይናገራል፡፡ ‹‹ግርታ›› በአጭር ፊልም ዘርፍ ካሉት 26 ፊልሞች አንዱ ነው፡፡ እሱ እንደሚለው፣ ፊልሙ ኢትዮጵያ ውስጥ በታየበት ወቅት ጥሩ ምላሽ ያገኘ ሲሆን፣ ለአፍሪካዊ ፌስቲቫል መታጨቱ ደግሞ ዕውቅናውን ያሳድገዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ባለሙያው ከ‹‹ፍሬ›› በፊት የሠራው ‹‹ብላቴና›› የተሰኘው ፊልም በ23ኛው አፍሪካን ዳያስፖራ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል ኒውዮርክ ውስጥ መሳተፉ ይታወሳል፡፡ ‹‹ግርታ›› ከሁለት ዓመት በፊት ጣሊያን ውስጥ በተካሄደው ዘጠነኛው ሪቨር ፊልም ፌስቲቫል ላይ በአጭር ፊልም ዘርፍ ማሸነፉም ይታወሳል፡፡ ‹‹ላምብ›› በዛው ዓመት የፈረንሣዩን ካንስ ፊልም ፌስቲቫል ጨምሮ በበርካታ ፌስቲቫሎች መታየቱና መሸለሙም ይታወሳል፡፡ የኢትዮጵያ ፊልሞች በአህጉር አቀፍና ዓለም አቀፍ መድረክ በመታየት ረገድ ብዙ ርቀት ተጉዘዋል ማለት ባይቻልም፣ እነዚህ ፊልሞች ጅማሮ መኖሩን ያመላክታሉ፡፡

ክንፈ እንደሚለው፣ በፌስቲቫሎች መሳተፍ የአገሪቱን ፊልም ከማሳደግ በተጨማሪ ባለሙያዎች ትምህርት የሚቀስሙበት አጋጣሚም ይፈጥራል፡፡ ‹‹ፌስቲቫሎች ለፊልም ሠሪዎች ብርታት ይሰጣሉ፤›› የሚለው ክንፈ፣ ያለ መደበኛ የፊልም ትምህርት ለሚሠሩ የኢትዮጵያ ባለሙያዎች ፌስቲቫሎች መማሪያ ናቸው ሲል ይገልጻል፡፡

ፌስቲቫሉ ዘንድሮ ለ25ኛ ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን፣ በ21ኛው ዙር ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ በ‹‹ጤዛ›› ፊልም አሽንፎ 20,000 ዶላር እንደተሸለመ ይታወሳል፡፡ ሽልማቱ ሲበረከትለት ‹‹ጤዛ ከፈጠራዎች ሁሉ የላቀ ነው፡፡ በፊልሙ ኃያልነትና በምስሉ ጠንካራነት የተሳካለት ሥራ ነው፤›› ተብሎ ነበር፡፡ በፌስቲቫሉ ታሪክ ሌሎችም የኢትዮጵያ ፊልሞች ተሳትፈዋል፡፡ በዘንድሮው ፌስቲቫል ድል መቀዳጀት መቻል መልካም ቢሆንም መሳተፍ በራሱ ቀላል እንዳልሆነ ክንፈ ያምናል፡፡

እሱ እንደሚለው፣ በአንድ ፌስቲቫል መሳተፍ ለሌሎች ፌስቲቫሎችም በር ይከፍታል፡፡ በዚህ ረገድ የአገሪቱ ፊልም ሠሪዎች ወጥ ታሪኮች ላይ የተመረኮዘ ሥራ ቢያቀርቡና ሥራቸውንም በፌስቲቫል ለማሳየት ጥረት ቢያደርጉም መልካም ነው ይላለ፡፡ በእርግጥ በኦንላየን ክፍያ ምዝገባ የሚያካሂዱ ፌስቲቫሎች ላይ ለመሳተፍ የኦንላየን ክፍያ ሥርዓት ባለመኖሩ ባለሙያዎች እንደሚቸገሩ ገልጿል፡፡ ሆኖም ከፌስቲቫሉ አዘጋጆች ጋር ስለ ሁኔታው በመነጋገር ችግሩን መፍታት እንደሚቻል ይናገራል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር የጨረታ ማስታወቂያ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በገቢ እና በውጭ ንግድ እንዲሁም...

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...