Wednesday, June 12, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊየተቋረጠው የኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ ተጀመረ

የተቋረጠው የኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ ተጀመረ

ቀን:

  • 16 ቢሊዮን ብር እንዲለቀቅ ተወስኗል

በፋይናንስ አቅርቦት መስተጓጎል ምክንያት ተቋርጦ የቆየው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ የኮንዶሚኒየም የቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት እንደገና ተጀመረ፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ግንባታ ፕሮግራም ቅድሚያ ተሰጥቶት ፋይናንስ እንዲለቀቅለት በመወሰኑ፣ ተቀዛቅዞ የነበረው የቤቶች ግንባታ እንደገና መቀጠሉ ታውቋል፡፡

የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ደምሴ ሽቶ እንደገለጹት፣ በተፈጠረው የፋይናንስ አቅርቦት ችግር ምክንያት በቤቶች ግንባታ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ኮንትራክተሮችና ሠራተኞች ተበትነው ነበር፡፡

- Advertisement -

‹‹በአሁኑ ወቅት የፋይናንስ ችግሩ በመፈታቱ፣ የተበተኑት ኮንትራክተሮችና ሠራተኞች ተመልሰው ወደ ሥራ ገብተዋል፤›› ሲሉ አቶ ደምሴ አስረድተዋል፡፡

በ2009 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ሰብሳቢነት ከተካሄደ በኋላ፣ በአዲስ አበባ የተጀመሩ የኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ በፋይናንስ አቅርቦት ችግር ምክንያት መስተጓጎላቸው ተመልክቷል፡፡

የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት እንደሚገልጸው፣ ለቤቶች ግንባታ ግብዓቶች መግዣ የሚውል የቦንድ ብድርና የውጭ ምንዛሪ ፍላጎት ለማሟላት 31.03 ቢሊዮን ብር እንዲፈቀድ ለብሔራዊ ባንክ ቀርቧል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከዚህ ገንዘብ ውስጥ 15 ቢሊዮን ብር የቦንድ ብድር ፈቅዷል፡፡

‹‹ከዚህ ውስጥ 8.5 ቢሊዮን ብር ለአዲስ አበባ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት (20/80) እንዲሁም 6.5 ቢሊዮን ብር ለአዲስ አበባ ቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ (40/60) ተደልድሏል፤›› ሲል የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቱ ያመለክታል፡፡

ነገር ግን ባለፉት ስድስት ወራት ለሁለቱም ግዙፍ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክቶች የተለቀቀው 2.45 ቢሊዮን ብር ብቻ ነው፡፡

በዚህ ምክንያት በግንባታ ላይ የነበሩ ኮንትራክተሮች፣ አማካሪዎች፣ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች፣ ግብዓት አቅራቢዎችና የትራንስፖርት ባለንብረቶች፣ እንዲሁም ሠራተኞች ተበትነዋል፡፡ በተለያዩ ጊዜያትም ክፍያ እንዲለቀቅላቸው ሲወተውቱ ቆይተዋል፡፡

‹‹በአጠቃላይ የ20/80ም ሆነ የ40/60 የቤቶች ግንባታ ዝቅተኛ አፈጻጸም ላይ ይገኛል፤›› ሲል ሪፖርቱ ያመለክታል፡፡

ነገር ግን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በአገር አቀፍ ደረጃ ከሚካሄዱ ሜጋ ፕሮጀክቶች ውስጥ አንዱ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ግንባር ቀደም እንደመሆኑ፣ 16 ቢሊዮን ብር እንዲለቀቅ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

አቶ ደምሴ እንዳሉት ኅብረተሰቡ የቤቶች ግንባታ ፕሮጀክቶችን በልማት መንገድ ሊያጤናቸው ይገባል፡፡ በአብዛኛው እየታየ ያለው ግን የአስተዳደር ጉዳይ ተደርጎ ነው፡፡

‹‹ልማት ሲካሄድ የተለያዩ ክፍተቶች ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡ ከፍላጎትና ከአቅርቦት አንፃርም ክፍተት ሊኖር ይችላል፡፡ ነገር ግን እየተካሄደ ያለው ሥራ ሰፊ ነው፡፡ ከፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል በማምጣት፣ አሮጌ ከተማ መልሶ በመገንባትና በሥራ ፈጠራ ያበረከተው አስተዋጽኦ ሊታይ ይገባል፤›› ሲሉ አስታውቀዋል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...