Wednesday, February 28, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልጎንደር ሰባተኛውን የከተሞች መድረክ ልታዘጋጅ ነው

ጎንደር ሰባተኛውን የከተሞች መድረክ ልታዘጋጅ ነው

ቀን:

ታሪካዊቷ የጎንደር ከተማ ሰባተኛውን የከተሞች መድረክ (ፎረም) ለማስተናገድ እየተዘጋጀች ነው፡፡ ከሚያዝያ 22 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ ለአንድ ሳምንት በሚቆየው መድረክ 200 ከተሞች፣ የእነዚህ ከተሞች እህት የሆኑ የውጭ አገር ከተሞችና 20 ኩባንያዎች ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሏል፡፡

የአማራ ክልል መንግሥት ለዚህ ፕሮግራም 25 ሚሊዮን ብር እንደመደበ፣ የጎንደር ከተማ አስተዳደርም ተጨማሪ በጀት በመመደብ የተለያዩ ዝግጅቶችን እያካሄደ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በዚህ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ከተሞች የእርስ በርስ ግንኙነት እንዲዳብር የኢንቨስትመንት፣ የገበያና የቱሪዝም ትስስራቸው የጠበቀ እንዲሆን እንደሚያደርግ የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡  

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ከዚህ ቀደም በነበሩት ወራት ጥንታዊቷ ጎንደር ከተማ የፀጥታ መደፍረስ ያጋጠማት ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ግን ሰላሟን መልሳ ማግኘቷን የሥራና ከተማ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ደምሴ ሽቶ ማክሰኞ የካቲት 14 ቀን 2009 ዓ.ም. ለጋዜጠኞች ገልጸዋል፡፡

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከዚህ ቀደም ዝነኛ የነበረውንና በኋላም ፈርሶ የነበረውን የፋሲለደስ ባህል ቡድንን እንደገና እንዳቋቋመው፣ የሚኒስቴሩ መረጃ አመልክቷል፡፡ ይህ ዝነኛ የባህል ቡድን የከተሞች ቀንን ያደምቀዋል ተብሏል፡፡

በስድስተኛው የከተሞች ፎረም 166 ከተሞችና 17 ኩባንያዎች ተሳታፊ ነበሩ፡፡ በየዓመቱ የተሳታፊዎች ቁጥር እያደገ የመጣ ሲሆን፣ በሰባተኛው የከተሞች ፎረም 200 ከተሞችና 20 ኩባንያዎች ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሏል፡፡ በከተሞች ፎረም ተሳታፊ የሚሆኑ ከተሞች ያስመዘገቧቸውን መልካም ሥራዎቻቸውን ይዘው እንደሚቀርቡ ተገልጿል፡፡ ይህ ዝግጅት ከተሞች ራሳቸውን የሚያስተዋውቁበትና ለከተማ ነዋሪዎች መረጃ የሚሰጡበት፣ እርስ በርሳቸውም ልምድ የሚቀስሙበት እንደሚሆን አቶ ደምሴ አስረድተዋል፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...