Friday, December 2, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊከዲዛይን ጋር የተያያዙ ችግሮች የግንባታ ዋጋዎችን ለማናርና ጊዜን ለማጓተት ምክንያት እየሆኑ ነው

  ከዲዛይን ጋር የተያያዙ ችግሮች የግንባታ ዋጋዎችን ለማናርና ጊዜን ለማጓተት ምክንያት እየሆኑ ነው

  ቀን:

  በመንግሥት በጀት የሚካሄዱ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች የግዥ ዑደት መረጃዎች ለባለድርሻ አካላት ተደራሽ እንዲሆኑና በዘርፉ ውስጥ ግልጽነት እንዲሰፍን በማድረግ፣ ለየፕሮጀክቶች ከሚመደብ ሀብት ተመጣጣኝ እሴት እንዲገኝ የሚሠራው፣ ኮንስትራክሽን ሴክተር ትራንስፓረንሲ ኢንሼቲቭ – ኢትዮጵያ (ኮስት ኢትዮጵያ) በመንግሥት ወጪ የሚሠሩ ግንባታዎች ላይ የሚከሰተው የዋጋ መናርና የጊዜ መራዘም ባብዛኛው ከዲዛይን ጋር በተያያዙ ችግሮች መሆኑን አመለከተ፡፡

  በሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሻምፒዮንነት የሚመራው ኮስት ኢትዮጵያ ሦስተኛውን የባለድርሻ አካላት ጠቅላላ ስብሰባ የካቲት 14 ቀን 2009 ዓ.ም. ሲያካሂድ፣ የኮስት ኢትዮጵያ ሥራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ ያለው እንደገለጹት፣ ኢንሼቲቩ በ52 ፕሮጀክቶች ላይ ጥናት አካሂዷል፡፡ በጥናቱ የመንገድ፣ የውኃበተለይ በመስኖና ግድብ እንዲሁም የሕንፃ (ጤናና ትምህርት) ግንባታዎች ዙሪያ በአዋጭነት ጥናታቸው፣ በጨረታና ግዥ ሥርዓታቸው፣ በግንባታ ዋጋ፣ ግንባታው በሚወስደው ጊዜና ተያያዥ በሆኑ መመዘኛዎች የተዳሰሱ ሲሆን፣ ከእነዚህም ብዙዎቹ የመንገድ ዘርፍ ነበሩ፡፡

  በሁሉም ዘርፎች ላይ የጊዜና የዋጋ መናር ታይቷል ያሉት አቶ ተስፋዬ፣ ለዚህም በዋነኛነት የተጠቀሱት ከዲዛይን ጋር የተያያዙ ችግሮች ናቸው፡፡ በአብዛኛው ለዋጋና ጊዜ መንሸራተት ከዲዛይን ጋር የተያያዙ ችግሮች ቢኖሩም፣ መጀመሪያ ሊሠራ የታቀደን ሥራ ከታቀደው በተለየ መልኩ ከፍ አድርጎ ዳግም ማቀድም ሌላው ምክንያት ነው፡፡

  ስለግንባታ ሲታሰብ፣ ከመጀመሪያው ጀምሮ ደረጃውን የጠበቀ ዲዛይን ቢሠራ ጥሩ ውጤት ሊመጣ እንደሚችል ጥናቱ ያመላከተ መሆኑን አቶ ተስፋዬ ተናግረዋል፡፡

  በመንግሥት በጀት የሚከናወኑ ግንባታዎችን ግልጽና ከብልሹ አሠራር የራቁ ከማድረግ አንጻር ተጨማሪ 33 ዩኒቨርሲቲዎችና 10 ትላልቅ ግዢ ያላቸው የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶችን ለማካተት፣ መሠረታዊ የኮንስትራክሽን ሴክተር ትራንስፖረንሲ ጽንሰ ሐሳቦች ምንድን ናቸው? በሚለውና በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ተጠቅሞ ግልጽ አሠራርን ማስፈን በሚቻልበት ሁኔታ ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡ በዚህ 10 ዩኒቨርሲቲዎች ያልተገኙ ቢሆንም፣ በተሰጠው ሥልጠና መሠረት እንዲሠሩ ለማስቻል እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡

  በኢንሼቲቩ የታቀፉ ተቋማት ሥራቸውን በአግባቡ እያከናወኑ ስለመሆኑ ለመከታተል፣ ከሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን፣ ከዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤትና ከመንግሥት ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ጋር ኢንሼቲቩ የአራትዮሽ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

  በዚህም ኤጀንሲው ድረ ገጹን ያስተዳድራል፣ መረጃዎች መጫናቸውን ይከታተላል፣ እንዲሁም ከግዢ ጋር የተያያዙ ሥራዎችን ይሠራል፡፡ ኮሚሽኑ በኢንሼቲቩ እስካሁን ያልተደረሱ መሥሪያ ቤቶችን ለመድረስ ይሠራል፡፡ የኦዲት መሥሪያ ቤት በበኩሉ የኮንስትራክሽን ዘርፉ መረጃዎችን ይፋ ስለማድረጉ ከኦዲት ሥራው እንደ አንድ ነጥብ አድርጎ የሚያየው ይሆናል፡፡ ይህም በኮንስትራክሽኑ ዘርፍ ብልሹ አሠራርንና ሙስናን ለማስቀረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሏል፡፡    

  የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣንንና የውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን በሚያከናውኗቸው ግንባታዎች ላይ ግልጽ አሠራር ለማስፈን የመግባቢያ ሰነድ ለመፈራረም በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡ የቤቶች ልማት ኤጀንሲ ታሳቢ የተደረገ ቢሆንም የግዥ ሥርዓቱ ከሌሎቹ ለየት ያለ በመሆኑ በቅድሚያ የሚጠቀምበትን አሠራር ለማየት እየተሞከረ መሆኑ ተነግሯል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...