Sunday, June 16, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርትየዋሊያዎቹ አዲሱ አሠልጣኝ ይፋ ሆነ

የዋሊያዎቹ አዲሱ አሠልጣኝ ይፋ ሆነ

ቀን:

  •  የደመወዙ መጠን አልተገለጸም

ለዓመታት ደካማ ውጤት ሲታይበት የቆየው የኢትዮጵያ እግር ኳስ እንቅስቃሴ፣ ለበርካታ አሠልጣኞች መቀያየር ምክንያት ሆኖ ቆይቷል፡፡ እግር ኳሱ ከሚያሳየው ዝቅተኛ ውጤት አኳያ የአገር ውስጥም ሆነ የውጭ አሠልጣኞች ዋሊያዎቹን ሲፈራረቁባቸው ኖረዋል፡፡

ለመጪው የ2019 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የዋሊያዎቹ አሠልጣኝ ምርጫ ዘግይቶም ቢሆን ይፋ ተደርጓል፡፡ የብሔራዊ ቡድኑ አሠልጣኝ ሆነው የተሾሙት የአዳማ ከተማ እግር ኳስ ቡድን ዋና አሠልጣኝ አቶ አሸናፊ በቀለ ሲሆኑ ከዚህ ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ የሁለት ዓመት ኮንትራታቸው እንደሚፀና ይጠበቃል፡፡ የብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ጁነዲን ባሻና ዋና ጸሐፊው አቶ ወንድምኩን አላዩ ለዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) ዓመታዊ ጉባኤ ማክሰኞ የካቲት 14 ቀን 2009 ዓ.ም. ወደ ደቡብ አፍሪካ በማቅናታቸው ምክንያት ውሉ እስከ ሳምንት መጨረሻ ይዘገያልም ተብሏል፡፡ አቶ ጁነዲን ዓርብ የካቲት 17 ቀን ወደ አዲስ አበባ እንደሚመለሱ ይጠበቃል፡፡

ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ድረስ ከብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ጋር ሕጋዊ ውል እንዳልተዋዋሉ የሚናገሩት አዲሱ የዋሊያዎቹ አሠልጣኘ አሸናፊ በቀለ፣ ኮንትራታቸውን በይፋ እስከሚወስዱ ድረስም አዳማ ከተማን በማሠልጠን ቆይታ እንደሚኖራቸው ገልጸዋል፡፡

- Advertisement -

ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ የዋሊያዎቹን ዋና አሠልጣኝ ይፋ ያደረገው ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ፣ የአሠልጣኙን ወርኃዊ ክፍያ በተመለከተ ቀደም ሲል ከነበረው ሊያንስም ሊጨምርም እንደሚችል የፌዴሬሽኑ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ አበበ ገላጋይ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ለጋቦኑ የ2017 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ለሁለት ጨዋታ ዋሊያዎቹን በኃላፊነት ተረክበው ሲያሠለጥኑ የነበሩት አሠልጣኝ ገብረመድኅን ኃይሌ ለአምስት ወር ኮንትራት በወር 80,000 ብር ይከፈላቸው ነበር፡፡ ከእሳቸው በፊት የሁለት ዓመት ኮንትራት የነበራቸው አሠልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ ደግሞ 75,000 ብር ይከፈላቸው እንደነበር ይታወቃል፡፡ ከአሠልጣኝ ዮሐንስ ሳሐሌ በፊት ለፖርቱጋላዊ አሠልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ ደግሞ 18,000 ዶላር የተጣራ ወርኃዊ ክፍያ ፌዴሬሽኑ ይከፍል የነበረ መሆኑም የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡

ከ31 ዓመታት በኋላ ለ2012 የደቡብ አፍሪካው የአፍሪካ ዋንጫና በ2013 በዚያው በደቡብ አፍሪካ ከተዘጋጀው የቻን ዋንጫ በኋላ ግን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ውጤት በአሉታዊ ጎኑ ካልሆነ በጥንካሬው ሳይወደስ እስካሁን ዘልቋል፡፡ ከዚህም በመነሳት በሳምንቱ መጀመሪያው በሐዋሳ ኃይሌ ሪዞርት የቡድኑ ዋና አሠልጣኝ መሆናቸው ይፋ የሆነው አቶ አሸናፊም የሚቀበሉት ኃላፊነት ቀላል እንዳልሆነ ገልጸው፣ ለ2019 የአፍሪካ ዋንጫ ኅብረተሰቡ የሚጠበቀውን ውጤት ለማስመዝገብ እንደሚጥሩ ተናግረዋል፡፡ ለዚህ ስኬት በተለይም ከሙያ አጋሮቻቸው ተገቢውን ድጋፍና እገዛም እንደሚጠብቁ በማከል፡፡

የብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የብሔራዊ ቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ዘሪሁን ቀቀቦ ምርጫውን አስመልክቶ ለተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ሲገልጹ እንደተደመጡት ከሆነ፣ የቡድኑ ዋና አሠልጣኝ ከበረኞች አሠልጣኝ በተጨማሪ ሁለት ረዳቶች ይኖሩታል፡፡ ፌዴሬሽኑ መስፈርቱን በማውጣት ደረጃ ካልሆነ ረዳቶቻቸውን የመምረጥ ሥልጣኑ ደግሞ የዋናው አሠልጣኝ ኃላፊነት እንደሚሆንም አቶ ዘሪሁን በይፋ ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡

አቶ አሸናፊ ለሐዋሳ ከተማ፣ ለደደቢትና ለቅዱስ ጊዮርጊስ ክለቦች እንዲሁም ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጫወት የሚታወቀው ሙሉጌታ ምሕረት የዋሊያዎቹ ረዳት አሠልጣኝ አድርገው መምረጣቸው እየተነገረ ይገኛል፡፡ ይህንኑ አስመልክቶ አቶ አሸናፊ፣ ‹‹የራሴን ውል ሳልጨርስ እንዴት አድርጌ ረዳቶቼን እመርጣለሁ?›› በማለት ነው ጥያቄውን በጥያቄ የመለሱት፡፡

አሠልጣኙ ለሚመርጡ አጨዋወት ይመጥናሉ የሚሉዋቸውን ልምድና ብቃቱ ላላቸው ተጨዋቾች ቅድሚያ እንደሚሰጡም ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ ለ2019 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከጋና፣ ከኬንያና ከሴራሊዮን ጋር መደልደሏ ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የምግብ ዋጋ ንረት አጣዳፊ ዕርምጃ ያስፈልገዋል!

መንግሥት የሚቀጥለውን ዓመት በጀት ይዞ ሲቀርብ በአንገብጋቢነት ከሚነሱ ጉዳዮች...

ከባለአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት የመሸጋገራችን እውነታ

በአብዱ ሻሎ አንገት ማስገቢያ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2022 የሩሲያ መንግሥት በዩክሬን ‹‹ልዩ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የሺሕ ዘመናት ታሪኳና እሴቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርበታል

(ክፍል አንድ) በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) እንደ መንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው...

ከአገር ግንባታ ጋር የተያያዙ ወሳኝ የቅርብ ታሪካችን አንጓዎች

በታደሰ ሻንቆ በአያሌው የተመረጡና ልጥ የሌላቸው ነጥቦች የተደራጁበት ይህ ታሪክ...