Monday, December 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊከኮንዶሚኒየም ቤቶች የሚወጣ ፈሳሽ ቆሻሻን ለማከምና መልሶ ጥቅም ላይ እንዲውል የሚያስችል ፕሮጀክት...

ከኮንዶሚኒየም ቤቶች የሚወጣ ፈሳሽ ቆሻሻን ለማከምና መልሶ ጥቅም ላይ እንዲውል የሚያስችል ፕሮጀክት ተጀመረ

ቀን:

በአዲስ አበባ ከተማ ከተገነቡና ለተጠቃሚዎች ከተላለፉ ከኮንዶሚኒየም ቤቶች የሚወጣ ፈሳሽ ቆሻሻ፣ በዘመናዊ መንገድ ተጣርቶ መልሶ ጥቅም ላይ እንዲውል የሚያስችል ፕሮጀክት ተግባራዊ ማድረግ ተጀመረ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕሮጀክቱን ተግባራዊ ለማድረግ ኤምፊስ ከተባለ ተቀማጭነቱ አውስትራሊያ ከሆነ ኩባንያ ጋር ሰሞኑን ውል እንደተፈራረመ ለማወቅ ተችሏል፡፡

አስተዳደሩ ከኩባንያው ጋር የገባው ውል ሁለት የጋራ መኖሪያ ግቢዎች ውስጥ የሙከራ ፕሮጀክት ለማከናወን ሲሆን፣ ለዚህም አንድ ቢሊዮን ብር ወጪ እንደሚያደርግ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ ለሙከራ የተመረጡት የጋራ መኖሪያ ኮንዶሚኒየም ግቢዎች በአዲስ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሙከራ የተገነቡት ገርጂ ቁጥር አንድና ሁለት መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በእነዚህ የጋራ መኖሪያ ኮንዶሚኒየም ግቢዎች ውስጥ 32 የመኖሪያ ብሎኮች ውስጥ ከሚኖሩ 7,000 ነዋሪዎች የሚወጣውን ፈሳሽ ቆሻሻ ወደ ሴፕቲክ ታንኮች የሚፈስ በመሆኑ፣ ከሴፕቲክ ታንኮቹ አቅም በላይ በሚሞላበት ጊዜ በመገንፈል አካባቢውን በማወክ ለጤና አሥጊ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ፕሮጀክቱን ያሸነፈው ኩባንያ ቲቲቪ ከተባለ አጋሩ ጋር በመሆን ሴፕቲክ ታንኮቹን በአዳዲስ የፈሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ዘመናዊ ማሽኖች ይቀይራቸዋል፡፡

ቴክኖሎጂው Membrane Accreted Biofilm Reactor (MABR) የተሰኘ ሲሆን ባለቤትነቱም የአውስትራሊያው ኩባንያ ነው፡፡

ይኼ ቴክኖሎጂ ከጋራ መኖሪያ ቤቶች የሚወጣውን ፈሳሽ ቆሻሻ በማጣራት ከፍተኛ ጥራት ወዳለው ውኃ በመቀየር መልሶ አገልግሎት ላይ እንዲውል አድርጎ የሚያቀርብ እንደሆነ ታውቋል፡፡

የተጣራው ውኃ ለሰዎች በቀጥታ ጥቅም ላይ የማይውል ቢሆንም፣ ለሌሎች አገልግሎቶች ጠቃሚ እንደሚሆንና በአካባቢው ላይም ምንም ዓይነት የሽታ መበከል አያደርስም ተብሏል፡፡

ኩባንያው የሙከራ ፕሮጀክቱን በአራት ወራት እንደሚያጠናቅቅ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ይኼንንም መሠረት በማድረግ ተጨማሪ ፕሮጀክቶችን ሊያገኝ ይችላል  ተብሏል፡፡ ኩባንያው ባደረገው ግምገማ በኢትዮጵያ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ገበያ በፈሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ሊያገኝ እንደሚችል ገምቷል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...