Tuesday, April 16, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ኦሮሚያና አዲስ አበባ ለሥራ ዕድል ፈጠራ ከፍተኛ በጀት ይዘው ቀረቡ

ተዛማጅ ፅሁፎች

– ኦሮሚያ ለወጣቶች ፋብሪካዎች ሊያቋቁም ነው

የኦሮሚያ ክልልና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለዓመታት የተከማቸውን የሥራ አጥነት ችግር ለመቅረፍ ከፍተኛ በጀት፣ አዳዲስና ያልተለመዱ የሥራ ዕድሎች ይዘው ቀረቡ፡፡

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት 6.6 ቢሊዮን ብር በመመደብ 1.2 ሚሊዮን ለሚሆኑ ሥራ አጦች በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ሥራ ለመፍጠር መዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ወጣት ባለሀብቶችን ለመፍጠር ከዚህ በፊት ለወጣት ሥራ አጦች ያልተለመደውን የመንግሥትና የግል ዘርፍ አጋርነት ፕሮግራም ይዞ የቀረበ ሲሆን፣ በዚህም የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ከወጣቶች ጋር በማስተሳሰር አዳዲስ ፋብሪካዎችን ለመገንባት አቅዷል፡፡

በዚህ ዕቅድ በመንዲና በጭሮ ከተሞች በ256 ሚሊዮን ብር ሁለት የእምነበረድ ፋብሪካዎች፣ በነቀምት ከተማ በ146 ሚሊዮን ብር የማንጎና የቲማቲም ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች፣ በሻሸመኔ፣ በጂማና በኦሮሚያ ልዩ ዞን በ78 ሚሊዮን ብር የኤሌክትሪክ ምሰሶዎች መቀቀያ ፋብሪካዎች፣ በጌዶና በቢሾፍቱ ከተሞች ሁለት የማዕድን ውኃ ፋብሪካዎች ለማቋቋም የአዋጭነት ጥናቶችን በማካሄድ ሥራ አጦችን ሥራ ለማስጀመር መዘጋጀቱ ታውቋል፡፡

ለፋብሪካዎቹ ግንባታ የሚያስፈልገው መነሻ ካፒታል የመንግሥት የልማት ድርጅቶች በድርሻቸው ልክ እንደሚያዋጡ፣ ሥራ ፈላጊዎች ደግሞ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ብድር እንዲያገኙ ተደርጎ ወጪው እንደሚሸፈን ከኦሮሚያ ክልል የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በክልሉ የሚገኙ የማዕድን ማውጫዎች ለአብነት ፑሚስ፣ ቀይ አሸዋ፣ አሸዋ፣ ድንጋይ (ካባ)፣ ታንታለም የመሳሰሉ የማዕድን ቦታዎች ለወጣት ሥራ አጦች እንዲሰጡ ይደረጋል፡፡ ወጣቶቹ የሚያመርቷቸውን ማዕድናት ለኢንቨስተሮች እንዲያቀርቡ እንደሚደረግ የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንትና የከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዓብይ አህመድን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በግብርና መስክ ለሚሰማሩ ወጣቶች 180,855 ሔክታር መሬት መዘጋጀቱም ተገልጿል፡፡

በኦሮሚያ ክልል በየዓመቱ ዕድሜያቸው 15 ዓመት የሚሞሉ አንድ ሚሊዮን ታዳጊ ወጣቶች እንደሚኖሩ፣ ከዚህ ቀደም በበቂ ደረጃ የሥራ ዕድል ባለመፈጠሩ ክልሉ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ለሆኑ ሥራ ፈላጊዎች ሥራ መፍጠር ይኖርበታል ተብሏል፡፡

የፌዴራል መንግሥት በአገር አቀፍ ደረጃ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር ከአሥር ቢሊዮን ብር ተዘዋዋሪ ፈንድ ማፅደቁ ይታወሳል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከዚህ በጀት ውስጥ 417 ሚሊዮን ብር ተመድቦለታል፡፡

አስተዳደሩ ከራሱ ግምጃ ቤትና ከተለያዩ የገንዘብ ምንጮች የሥራ አጥነትን ችግር ለመፍታትና ለምግብ ዋስትና ችግር የተዳረጉ ዜጎችን ለመታደግ 3.6 ቢሊዮን ብር በጀት ይዟል፡፡

አስተዳደሩ በአጠቃላይ በሚቀጥሉት ወራት ከ206 ሺሕ በላይ ወጣቶችን በተለያዩ ሥራዎች በጊዜያዊነትና በቋሚነት ሥራ እንዲያገኙ ለማድረግ ማቀዱን ከአስተዳደሩ የወጡ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በዚህ መሠረትም ሥራ አጦችንና ለምግብ ዋስትና ችግር የተዳረጉ የከተማው ነዋሪዎችን በመመዝገብ ላይ ይገኛል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች