Thursday, October 6, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ሥነ ፍጥረትየሌሊት ወፍ

  የሌሊት ወፍ

  ቀን:

  ከስድስት ያላነሱ የሌሊት ወፍ ዝርያዎች ሲኖሩ፣ ከአጥቢ እንስሳትም በመብረር ብቸኛዎቹ ናቸው፡፡ አብዛኛዎቹ የሌሊት ወፍ ዝርያዎች በሽታን በማስተላለፍ ይታወቃሉ፡፡ በማዕከላዊና ደቡብ አሜሪካ እንዲሁም በሜክሲኮ የሚገኘው ‹‹ቫምፓየር የሌሊት ወፍ›› ግን ከሌሎቹ የሚለየው ደም በመምጡ ነው፡፡

  የኪድስ ባዮሎጂ ድረ ገጽ እንዳሰፈረው፣ ከአጥቢ እንስሳ የሚመደበው ቫምፓየር የሌሊት ወፍ ምግቡ ደም ብቻ ነው፡፡ እንደ ፈረስ፣ በግና ፍየል ያሉ የቤት እንስሳትን በመንከስ ደም ይመጣል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የሰዎችን ደም በመምጠጥ ይታወቃል፡፡

  አስቸጋሪ የሚባሉት ቫምፓየር የሌሊት ወፎች፣ 100 ያህል ሆነው በቡድን የሚኖሩ ሲሆን፣ አንዳንድ ጊዜ 1,000 እና ከዚያም በላይ ሆነው ተሰባስበው ይኖራሉ፡፡

  ቀን በመተኛት ለአደን የሚወጡም ሌሊት ነው፡፡ ሌሊት ላይ ተኝተው ያገኟቸውን በተለይ የፈረሶችና የላሞች ደም ይመጣሉ፡፡ ሆኖም በአንድ ጊዜ አንድ የያዙትን እንስሳ ደም መጠው አይጨርሱም፣ እንስሳውንም ለሞት አይዳርጉም፡፡ ሆኖም በተለይ ሬቢሲ (የእብድ ውሻ በሽታ) ስለሚያስተላልፉ እንስሳትንም ሆነ ሰዎችን በቀላሉ ይበክላሉ፡፡

  100 ሆነው የሚኖሩ ቫምፓየር የሌሊት ወፎች፣ በአንድ ዓመት ውስጥ የ25 ላሞችን ደም ይጨርሳሉ፡፡ ከሥጋ በሊታ እንስሳት የሚመደበው የሌሊት ወፍ፣ የዕድሜ ጣሪያው ዘጠኝ ዓመት ነው፡፡

   

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img