Monday, December 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊቤቶች ኮርፖሬሽን በመሀል ከተማ ሰፋፊ ይዞታዎቹ ላይ አፓርትመንቶችን ለመገንባት ዝግጅት ጀመረ

ቤቶች ኮርፖሬሽን በመሀል ከተማ ሰፋፊ ይዞታዎቹ ላይ አፓርትመንቶችን ለመገንባት ዝግጅት ጀመረ

ቀን:

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በቅርቡ ያቋቋመው የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን (የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ) በሥሩ በሚገኙ ሰፋፊ ይዞታዎች ላይ ያረፉ ቪላ ቤቶችን በማፍረስ፣ አዳዲስ አፓርታማዎችን ለመገንባት ዝግጅት ማድረግ ጀመረ፡፡

በተለያዩ የመዋቅር ለውጦች አልፎ ጥር 26 ቀን 2009 ዓ.ም. መጨረሻ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በሚል ስያሜ በድጋሚ የተደራጀው የቀድሞ የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ፣ በመሀል ከተማ ከአምስት ሺሕ ካሬ ሜትር ቦታ በላይ ስፋት ያላቸው በርካታ ቪላ ቤቶች አሉት፡፡

ከእነዚህ ቪላ ቤቶች ውስጥ ከ30 እስከ 40 የሚሆኑትን በመለየት ሒደት ላይ ነው፡፡ የተያዘው በጀት ዓመት ሳይጠናቀቅ የለያቸውን ይዞታዎች በማፍረስ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማስተር ፕላን በሚፈቅደው ደረጃ መሠረት አፓርታማዎችን ለመገንባት ማቀዱን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ኮርፖሬሽኑ የተቋቋመበትን ደንብ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ መውጣቱን በመጠባበቅ ላይ ሲሆን፣ ከደንቡ በኋላ መመርያዎችን አሻሽሎ ለማውጣት የተለያዩ ጥናቶችን እያካሄደ መሆኑ ታውቋል፡፡

የቤቶች ኮርፖሬሽን የሚገነባቸውን አፓርታማዎች ለኪራይ የሚያቀርብ ሲሆን፣ ለመንግሥት ባለሥልጣናት አገልግሎት የሚውሉ ቤቶችን የመገንባት ዕቅድም አለው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በመንግሥት ውሳኔ ለሽያጭ የሚያቀርባቸው ቤቶች እንደሚኖሩም ታውቋል፡፡

በቀድሞው መንግሥት የኪራይ ቤቶች አስተዳደር በሚባል መጠሪያው ከአሥር ሺሕ ቤቶች በላይ የገነባው የአሁኑ ቤቶች ኮርፖሬሽን፣ ከመንግሥት ለውጥ በኋላ ወደ መኖሪያ ቤት ግንባታ ለመግባት የተለያዩ ሙከራዎችን ቢያደርግም ሳይሳካለት ቀርቷል፡፡

በተለይ ዶ/ር አርከበ ዕቁባይ የሥራና ከተማ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ በነበሩበትና አቶ መኩሪያ ኃይሌ የኮንስትራክሽንና ቤቶች ሚኒስትር በነበሩበት ወቅት፣ ኮርፖሬሽኑ ወደ ግንባታ ለመግባት የተለያዩ ጥናቶችን አካሂዶ ለውሳኔ ቢያቀርብም ፈቃድ ማግኘት ሳይችል ቀርቷል፡፡

ነገር ግን በአሁኑ ወቅት የመኖሪያ ቤት አቅርቦት እጥረት በመኖሩ የመንግሥት ባለሥልጣናትን ብቻ እንዲያስተናግድ ቢደረግም፣ ኮርፖሬሽኑ ለባለሥልጣናትም መኖሪያ ቤት ማቅረብ አልቻለም፡፡ ባለሥልጣናትን አስተናገደ ከተባለም ነባር ደንበኞቹን በተለያየ ምክንያት እያስወጣ መሆኑ ከፍተኛ የመልካም አስተዳደር ችግር ተፈጥሯል፡፡

ይህም ደንበኞች ባገኙት አጋጣሚ የሚያነሱት ቅሬት ከመሆኑም በላይ፣ ከየክልሉ በሹመት የሚመጡ ባለሥልጣናት የቤት ፍላጎት ጥያቄ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትን አጨናንቋል፡፡

በዚህ መሠረት የአሁኑ ኮርፖሬሽን ጥናት እንዲያቀርብ በተሰጠው መመርያ መሠረት ጥናቱን ያቀረበ ሲሆን፣ ጥናቱ የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝን ድጋፍ በማግኘቱ በመጨረሻ ኮርፖሬሽኑ ከ24 ዓመታት በኋላ የቤት ልማት ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆን ተወስኗል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ወደ ቤት ግንባታ የሚገባበት የፋይናንስ አቅርቦት እስካሁን በግልጽ ባይቀመጥም፣ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች እንደሚሉት በሥሩ 17 ሺሕ ቤቶች የሚገኙ በመሆኑ እነዚህን ቤቶች እያስያዘ ብድር ሊያገኝ ይችላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የአሁኑ ኮርፖሬሽን የመንግሥት የልማት ድርጅት በነበረበት ወቅት ከ700 ሚሊዮን ብር በላይ በአካውንቱ ይገኝ እንደነበር የሚገልጹት እነዚህ የመረጃ ምንጮች፣ መንግሥት ይህን ገንዘብ መልሶ ፈሰስ ሊያደርግለት እንደሚችልም ያስረዳሉ፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...