Friday, December 1, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

አምስተኛው የአፍሪካ ቢዝነስ ጉባዔ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

ተዛማጅ ፅሁፎች

አምስተኛው የአፍሪካ ቢዝነስ ጉባዔ በቀጣዩ ወር በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡ ሼክ መሐመድ አል አሙዲ አምስተኛውን የአፍሪካ ቢዝነስ ፎረም ስፖንሰር እንደሚያደርጉት የተገለጸ ሲሆን፣ ከጉባዔው ዋና የመወያያ አጀንዳዎች መካከል የፋይናንስና የካፒታል ኢንቨስትመንት በአፍሪካ የሚለው ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶታል፡፡

ኢትዮጵያ ለውጭ የፋይናንስ ተቋማት በሯን ብትዘጋም፣ የተለያዩ የውጭ ኩባንያዎች በካፒታል ኢንቨስትመንት ዘርፍ በኢትዮጵያ ፉክክር ላይ መሆናቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ግንባር ቀደም የሆነው የአሜሪካው ሹልዝ ግሎባል ኢንቨስትመንት አንዱ ሲሆን፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተፎካካሪ ሆኖ የቀረበው ደግሞ የእንግሊዙ 54 ካፒታል የተባለው የካፒታል ኢንቨስትመንት ኩባንያ ይገኝበታል፡፡

በአዲስ አበባ ከሚካሄደው አምስተኛው የአፍሪካ ኢንቨስትመንት ጉባዔ ቀደም ብሎ፣ ‹‹ቢዝነስ ቱ ቢዝነስ›› ጉባዔ በዱባይ እንደሚካሄድም የአዘጋጆቹ መግለጫ ያመለክታል፡፡

በሒልተን ሆቴል በሚካሄደው በዚህ ጉባዔ የባህረ ሰላጤው አገሮች ኩባንያዎች በብዛት እንደሚሳተፉ አዘጋጆቹ ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም በርካታ የመካከለኛው ምሥራቅ ‘ኢኪውቲ ኢንቨስተሮች’ እንደሚሳተፉ ይጠበቃሉ፡፡

በኢትዮጵያ በኩል የአገሪቱን ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታዎች አስመልክቶ የኢንቨስትመንት ኮሚሽነሩ አቶ ፍፁም አረጋና የኧርነስት ኤንድ ያንግ ማኔጂንግ ፓርትነር አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ ማብራሪያ እንደሚሰጡ ተገልጿል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች