Monday, March 27, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሠልጣኙን አሰናበተ

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሠልጣኙን አሰናበተ

ቀን:

ለዓመታት በባንኮች ማኅበር ሲተዳደር ቆይቶ ከ2003 ዓ.ም. ጀምሮ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተላልፎ የተሰጠው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እግር ኳስ ክለብ፣ የቡድኑ ዋና አሠልጣኝ ሆነው የቆዩትን አቶ ፀጋዬ ኪዳነማርያምን አሰናብቷል፡፡ በምትካቸው ምክትላቸው የነበሩት አቶ ሲሳይ ከበደና የተስፋ ቡድኑን አሠልጣኝ አቶ ግርማ ፀጋዬን ደግሞ በምክትልነት መሾሙ ታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2009 የመጀመርያ ዙር የጨዋታ መርሐ ግብር በተጠናቀቀ ማግስት የተናበቱት አሠልጣኝ ፀጋዬ፣ የቀድሞ ሐረር ቢራ የአሁኑ ሐረር ሲቲን ለረዥም ዓመታት አሠልጥነዋል፡፡ ከዚያም በ2005 የውድድር ዓመት ወደ ኢትዮጵያ ቡና አምርተው ለወራት ያህል አሠልጥነው ለከፍተኛ የአሠልጣኝነት ሥልጠና ወደ ሐንጋሪ ሄደው ከተመለሱ በኋላ፣ ከ2006 ዓ.ም. ጀምሮ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ተቀላቅለው ቆይተዋል፡፡

ማክሰኞ የካቲት 7 ቀን 2009 ዓ.ም. የስንብታቸው ዜና ይፋ እስከሆነበት ድረስ በተለይም በዚህ ዓመት ካደረጓቸው 15 ጨዋታዎች ሦስቱን አሸንፈው፣ አራት አቻ ወጥተው፣ ስምንት ጨዋታዎችን ተሸንፈው በ13 ነጥብ 15 ደረጃ ላይ ነበሩ፡፡ በ2010 የውድድር ዓመት ከፕሪሚየር ሊጉ ወደ ከፍተኛ (ሱፐር ሊግ) የሚወርዱት ቡድኖች ሦስት መሆናቸውም ይታወቃል፡፡

አሠልጣኙ በዚህ ሳምንት ይፋ ይሆናል ተብሎ በሚጠበቀው ለዋሊያዎቹ ዋና አሠልጣኝ ቅጥር ቅድሚያ ግምት ከተሰጣቸው አሠልጣኞች አንዱ ስለመሆናቸውም እየተነገረ ይገኛል፡፡ አሠልጣኝ ፀጋዬ በውድድር ዓመቱ አራተኛው ተሰናባቹ አሠልጣኝም ናቸው፡፡ አሠልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ ከደደቢት ከሦስት ጨዋታ በኋላ፣ ሰርቢያዊው አሠልጣኝ ከኢትዮጵያ ቡናና ደረጃ በላይ ከጅማ አባቡና ይጠቀሳሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...