Wednesday, September 27, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተናጠል የኢንዱስትሪ ልማት መሬት ጥያቄ መቀበል አቆመ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተናጠል የኢንዱስትሪ ልማት መሬት ጥያቄ መቀበል አቆመ

ቀን:

– በ3.5 ቢሊዮን ብር አዲስ ኮርፖሬሽን አቋቋመ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተናጠል የኢንዱስትሪ ግንባታ መሬት ጥያቄ መቀበሉን አቆመ፡፡ በ3.5 ቢሊዮን ብር ካፒታል ‹‹የኢንዱስትሪ ክላስተር ልማት ኮርፖሬሽን›› በሚባል ስያሜ አዲስ ያቋቋመው ድርጅት፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን እያለማ ለኢንቨስተሮች እንዲያቀርብ ወሰነ፡፡

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ከዚህ ቀደም ለቀረቡለት የኢንዱስትሪ ልማት መሬት ጥያቄዎች፣ በአብዛኛዎቹ ላይ በቅርብ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ ከዚህ በኃላ ግን ከተማው ያለው የመሬት ሀብት አነስተኛ በመሆኑና ለአስተዳደርም አመቺ ባለመሆኑ፣ በተበታተነ መንገድ የፋብሪካ ግንባታ ቦታ ጥያቄ እንዲገታ ወስኗል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጀማል ረዲ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ከዚህ በኋላ ለማምረቻ ኢንዱስትሪ መሬት ሳይሆን በቀጥታ ወደ ምርት የሚያስገባቸው ቦታ ነው የሚቀርበው፡፡

በዚህ ቅኝት መሠረት በኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አስተባባሪነት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ፣ አዲስ የኢንዱስትሪ ክላስተር ልማት ኮርፖሬሽን የተሰኘ ተቋም በ3.5 ቢሊዮን ብር ካፒታል አቋቁማል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ራሱን በማደራጀት ላይ ሲሆን፣ ቀድም ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ የነበሩት አቶ ያብባል አዲስ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው ተሾመውለታል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በተለይ የአዲስ አበባ ከተማ አሥረኛው ማስተር ፕላን ባቀረበው ሐሳብ መሠረት በአቃቂ ቃሊቲ፣ በቦሌና በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍላተ ከተሞች ውስጥ አዳዲስ የኢንዱስትሪ ፓርኮቸን የመገንባት ዕቅድ አውጥቷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በአነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች ቢሮ ከተገነቡ 3,800 ሼዶች ውስጥ 148 የሚሆኑት፣ ለኮርፖሬሽኑ ተላልፈው እንዲሰጡ ካቢኔው መወሰኑን አቶ ጀማል ገልጸዋል፡፡

በከተማ አስተዳደሩ ዕቅድ መሠረት የኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ግንባታ በቅርቡ ይጀመራል፡፡ የመሠረት ልማት አውታሮች፣ እንዲሁም በማዕከል ደረጃ ዘመናዊ የፍሳሽ ማስወገጃ ጣቢያ ግንባታ ይካሄዳል፡፡ በአሁኑ ወቅት አዲሱ ኮርፖሬሽን በሰው ኃይልና በመዋቅሮች እየተደራጀ መሆኑ ታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአዳዲሶቹ ብቻ ሳይሆን በነባሮቹ ኢንዱስትሪ ዞኖች ላይም ግምገማ ማካሄዱ ታውቋል፡፡

በተለይ ከ1996 ዓ.ም. ወዲህ የተከለሉት የአቃቂ ቃሊቲና የለቡ ኢንዱስትሪ ዞኖች ውስጥ ቦታ የወሰዱ ባለሀብቶች ስምምነት የፈጸመበትን ግንባታ አለማካሄዳቸው፣ ከታለመለት ዓላማ ውጪ ቦታውን እየተገለገሉበት መሆኑን ካቢኔው ከቀረበለት ጥናት መሠረት ማወቁ ተመልክቷል፡፡

አቶ ጀማል እንደሚሉት፣ የወሰዱትን የኢንዱስትሪ መሬት ከታለመለት ዓላማ ውጪ ባዋሉ ባለሀብቶች ላይ ዕርምጃ እንዲወሰድ ተወስኗል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...