Wednesday, February 28, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየከርሰ ምድር ውኃ መንጠፍና የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ አዲስ አበባን ለውኃ እጥረት ዳረገ

የከርሰ ምድር ውኃ መንጠፍና የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ አዲስ አበባን ለውኃ እጥረት ዳረገ

ቀን:

ባለፉት ሁለት ዓመታት በከፍተኛ ወጪ ተገንብተው ወደ ሥርጭት የገቡ የከርሰ ምድር ውኃ ማመንጫዎች በገጠማቸው ችግር ምክንያት፣ አዲስ አበባ በድጋሚ የውኃ አቅርቦት እጥረት ገጠማት፡፡

የችግሩ መነሻ ከአዲስ አበባ ከተማ ወደ ቢሾፍቱ በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው አቃቂ አካባቢ የተቆፈሩ ጥልቅ ጉድጓዶች፣ እንዲሁም ለአጭር ጊዜ መፍትሔ ይሰጣሉ ተብለው በሰሜን አዲስ አበባ የተቆፈሩ ጉድጓዶች በቂ ውኃ ማቅረብ ባለመቻላቸው ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን የውኃ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ፍቃዱ ዘለቀ ረቡዕ የካቲት 1 ቀን 2008 ዓ.ም.  ለጋዜጠኞች እንደገለጹት፣ የአቃቂ ከርሰ ምድር ክፍል ሦስት ሀ እና ለ የውኃ ምርት ቀንሷል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

አቃቂ ክፍል ሦስት ሀ በቀን 70 ሺሕ ሊትር ውኃ የማምረት አቅም አለው፡፡ ይህ የከርሰ ምድር ውኃ ጀሞ፣ ጎተራ፣ 22 ማዞሪያ፣ ለገሃር፣ ሜክሲኮ አደባባይ አካባቢና ኢትዮጵያ ሆቴል አካባቢዎች የነበረውን ከበድ ያለ የውኃ እጥረት ያቀለለ ፕሮጀክት ነው፡፡

አቃቂ ክፍል ሦስት ለ ደግሞ ዓለም ባንክ፣ ቤተል፣ አንፎ፣ ቀራኒዮና ጦር ኃይሎች ድረስ ያሉ አካባቢዎች የነበረባቸውን ከበድ ያለ የውኃ እጥረት ያሻሻለ ፕሮጀክት ነው፡፡

ለአጫጭር ጊዜ መፍትሔ እንዲሆኑ በሰሜን አዲስ አበባ በተለይም ኮልፌ፣ ጉለሌና አዲስ ከተማ አካባቢዎች ውኃ የሚያሠራጩ በርካታ ጉድጓዶች ነበሩ፡፡ እነዚህ ጉድጓዶች እንደ አቃቂ ፕሮጀክቶች ሁሉ ውኃ መስጠት አልቻሉም፡፡

አቶ ፍቃዱ እንደገለጹት፣ የአቃቂ ከርሰ ምድር ውኃ 500 ሜትር ጥልቀት አለው፡፡ የውኃ መሳቢያው ፓምፕ የተተከለው አንድ መቶ ሜትር ላይ ነው፡፡ ችግሩ እንደተከሰት በተደረገው ጥናት ጉድጓዶቹ ውኃ አጥተው ሳይሆን፣ የውኃ መሳቢያው የተተከለው ከፍ ብሎ አንድ መቶ ሜትር ላይ በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡

‹‹ፕሮጀክቱ አገልግሎት ላይ ሲውል በመቶ ሜትር ከፍታ ላይ በቂ ውኃ መሳብ ተችሎ ነበር፡፡ አሁን ግን በቂ ውኃ መሳብ ባለመቻሉ የውኃ መሳቢያውን ዝቅ አድርጎ ለመትከል ከኮንትራክተር ጋር ንግግር እየተደረገ ነው፤›› ሲሉ አቶ ፍቃዱ ገልጸዋል፡፡

‹‹ከዚህ በኋላ ተመሳሳይ ችግር እንዳያጋጥም የከርሰ ምድር ውኃዎችን ቁጥጥር የሚሠራ ክፍል ተዘጋጅቷል፤›› በማለት አቶ ፍቃዱ አክለዋል፡፡

በሰሜን አዲስ አበባ የተከሰተውንም ችግር ለመፍታት ውኃ ያለባቸው አካባቢዎች ተመርጠው አዳዲስ ጉድጓዶች እየተቆፈሩ መሆኑን አቶ ፍቃዱ ገልጸው፣ ችግሩን በዘለቄታ ለመቅረፍ ግን ከእንጦጦ ጀርባ ያለው የገርቢ ወንዝ ላይ የውኃ ማጣሪያ ጣቢያ ይገነባል ብለዋል፡፡

በገርቢ ወንዝ የግድብ ግንባታ ለማካሄድ የቻይና ኢምፖርት ኤክስፖርት ባንክ (ኤግዚም) ለኢትዮጵያ መንግሥት 242 ሚሊዮን ዶላር ብድር በማቅረቡ፣ በቅርቡ ግንባታው እንደሚጀመር አቶ ፍቃዱ አስረድተዋል፡፡

‹‹ሰሜን አዲስ አበባ እንደ ሌሎች ቦታዎች ቋሚ የውኃ መገኛ ስለሌለው ችግር ከገጠመው ቆይቷል፡፡ በአሁኑ ወቅት ግን የገርቢ ፕሮጀክት ፋይናንስ ስለተገኘለት ችግሩ በዘለቄታው ይፈታል፤›› ሲሉ አቶ ፍቃዱ ገልጸዋል፡፡

ውኃ ለተጠማችው አዲስ አበባ የከርሰ ምድር ጉድጓዶች መንጠፍ ብቻ አይደለም ምክንያቱ፡፡ በተለይ ካለፉት ሁለት ወራት ወዲህ በድጋሚ ያገረሸው የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ፣ የሚመረተው ውኃ በአግባቡ እንዳይዳረስ እንቅፋት መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

‹‹የኤሌክትሪክ ኃይል በቀን ሁለት ሦስት ጊዜ ይቋረጣል፡፡ ተመላልሶ የሚመጣ ችግር ሆኖብናል፤›› ሲሉ አቶ ፍቃዱ ችግሩን ተናግረዋል፡፡

በ2006 ዓ.ም. መጨረሻ  የአዲስ አበባ ከተማ ንፁህ ውኃ አቅርቦት 350 ሺሕ ሜትር ኪዩብ ብቻ ነበር፡፡ ከዚያ ወዲህ በተሠሩ በርካታ ፕሮጀክቶች ምክንያት ተጨማሪ 258 ሺሕ ሜትር ኪዩብ ውኃ ተገኝቷል፡፡

ይህ የውኃ መጠን የከተማዋን የውኃ ሽፋን ከማሳደጉም በላይ፣ በፈረቃ ውኃ ሲያገኙ የነበሩ አካባቢዎችን በአብዛኛው 24 ሰዓት አገልግሎት መስጠት ችሎ እንደነበር መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ነገር ግን በአሁኑ ወቅት የውኃ ጉድጓዶች በመንጠፋቸውና፣ በኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ምክንያት ዕፎይታ አግኝተው የነበሩ አካባቢዎች በድጋሚ ለውኃ እጥረት ተዳርገዋል፡፡

‹‹24 ሰዓት ውኃ ከሚያገኙ አካባቢዎች ቀንሰን ማግኘት ላልቻሉ አካባቢዎች እየሰጠን ነው፤›› ሲሉ አቶ ፍቃዱ ባለሥልጣኑ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት እያደረገ ያለውን ጥረት ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...