Saturday, September 24, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊየአፍሪካን ገበሬዎች ሥጋት ላይ የጣለው የበቆሎ ትል

  የአፍሪካን ገበሬዎች ሥጋት ላይ የጣለው የበቆሎ ትል

  ቀን:

  በአብዛኞቹ የአፍሪካ አገሮች ለዋና ምግብነት በሚውለው የበቆሎ አዝርዕት ላይ የተከሰተው ትል የአፍሪካ ገበሬዎችን ሥጋት ላይ ጥሏል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

  በበቆሎ ላይ የተከሰተው ትል የምግብ ዋስትናንና የግብርና ምርት ንግድን አደጋ ላይ እንደሚጥለው ደግሞ ሴንተር ፎር አግሪካልቸር ኤንድ ባዮሳይንስ ኢንተርናሽናል (ሲኤቢአይ) አስታውቋል፡፡ ሣይንቲስቶች ደግሞ በበቆሎ ላይ የተከሰተውንና በአፍሪካ አገሮች በፍጥነት እየተዛመተ ያለውን የበቆሎ ትል መቆጣጠር ካልተቻለ፣ የበቆሎ ምርት ሙሉ ለሙሉ ይወድማል ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡

  በሰሜንና በደቡብ አሜሪካ ብቻ ይገኝ የነበረው ይኸው ትል፣ ከዓምና ማብቂያ ጀምሮ በአፍሪካ መታየት የጀመረ ሲሆን፣ አመጣጡ ከውጭ ከሚገቡ ምርቶች ጋር ተቀላቅሎ ሊሆን እንደሚችል ሣይንቲስቶች ገምተዋል፡፡

  በበቆሎ ላይ የዘመተው ትል ዚምባቡዌና ጋና መግባቱ የተረጋገጠ ሲሆን፣ የመጀመሪያ ደረጃ ዳሰሳዎች ደግሞ ትሉ በማላዊ፣ በሞዛምቢክ፣ በናሚቢያ፣ በደቡብ አፍሪካና በዛምቢያ ሊኖር እንደሚችል አመላክተዋል፡፡

  ከደቡብና ሰሜን አሜሪካ የመጣው ትል አፍሪካን በፍጥነት እያዳረሰ ሲሆን፣ ምሥራቅ አፍሪካም ሊገባ ይችላል የሚል ሥጋት አለ፡፡ ከዚህም አልፎ እስያና ሜዲትራኒያን ሊዘልቅ እንደሚችል ሲኤቢአይ ገልጿል፡፡

  በአፍሪካ ላይ አስፈሪ ሥጋት የሆነውን ክስተት መቆጣጠር ካልተቻለ፣ ቀጥሎ የሚከሰተው የምግብ ቀውስ ገበሬውንም ሆነ ነዋሪውን እንደሚጎዳ ያስታወቀው ሲኤቢአይ፣ የበቆሎ አዝርዕትን እያወደመ የሚገኘው ትል ከዚህ ቀደም በአገሪቱ አዝርዕት ላይ ከሚገኙ ትሎች ተመሳሳይ ይሁን የተለየ ለመለየት ለጊዜው እንዳዳገተውም ተናግሯል፡፡

  ዛምቢያ በትሉ የተጎዱ ሰብሎችን ለማዳንና ያልደረሰባቸውን ለመጠበቅ የኬሚካል ርጭት የጀመረች ሲሆን፣ ዓለም አቀፉ የምግብ ድርጅት ደግሞ በበቆሎ ላይ የዘመተውን ትል ለመቆጣጠርና የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ እንደሚያስፈልግ ለመወሰን ከየካቲት 7 እስከ 9 ቀን 2009 ዓ.ም. የአስቸኳይ ጊዜ ስብሰባ በሐራሬ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡ 

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ወ/ሮ መሰንበት ሸንቁጤ የአዲስ አበባን ንግድና ዘርፍ ምክር ቤትን በፕሬዚደንትነት ለመምራት በተደረገው ምርጫ አሸነፉ

  የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤትን በፕሬዚደንትነት ለመምራት፣...

  ለቻይናው ፖሊጂሲኤል ኩባንያ የተሰጠው ውል ተቋረጠ

  የማዕድንና ሚኒስቴር በሶማሌ ክልል የተገኘውን የተፈጥሮ ጋዝ አልምቶ ኤክስፖርት...

  የሕግ ክልከላዎችና የሚያስነሱት ቅሬታ

  በኢትዮጵያ የአገርና የዜጎችን ደኅንነት ለመጠበቅ ተብለው የሚወጡ አንዳንድ ሕጎች፣...