Tuesday, November 28, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊለወጣቶች የሥራ ዕድል የሚውለው የአሥር ቢሊዮን ብር ፈንድ ማቋቋሚያ ፀደቀ

ለወጣቶች የሥራ ዕድል የሚውለው የአሥር ቢሊዮን ብር ፈንድ ማቋቋሚያ ፀደቀ

ቀን:

 

  • ተጠቃሚ መሆን የሚፈልጉ በጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ መደራጀት ይኖርባቸዋል
  • የጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ የካፒታል ጣሪያ 100 ሺሕ ብር ነው

መንግሥት ለወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ ቃል የገባውን የአሥር ቢሊዮን ብር ተዘዋዋሪ ፈንድ የሚያቋቁም አዋጅ፣ ማክሰኞ ጥር 30 ቀን 2009 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀደቀ፡፡

የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በገቢ ማስገኛ እንቅስቃሴዎች ተደራጅተው ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ችግሮቻቸውን እንዲያቃልሉ፣ የገንዘብና የቴክኒክ ድጋፍ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፈንዱ እንደተቋቋመ የአዋጁ መግቢያ ያስረዳል፡፡

የፈንዱ ምንጭ የፌዴራል መንግሥት በሚመድበው አሥር ቢሊዮን ብር በጀት እንደሚሆን አዋጁ ያስረዳል፡፡ ፈንዱን የሚያስተዳድረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንደሆነ፣ ነገር ግን የፈንዱ ተጠቃሚዎች አነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት ብድሩን የማቅረብ ሥራ እንዲሠሩ፣ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት በሌሉበት የንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብድሩን እንዲያቀርቡ ተደንግጓል፡፡

በዚህም መሠረት የንግድ ባንክ ኃላፊነት ለክልሎች የተደለደለውን በመለየት ለሚመለከታቸው አነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት ማስተላለፍ፣ ተቋማቱ የተላለፈላቸውን ገንዘብ ለታለመለት ዓላማ ማዋላቸውን መቆጣጠር፣ ስለፈንዱ ገንዘብ አጠቃቀም ዝርዝር መግለጫ የያዘ ሪፖርት በየስድስት ወሩና በየዓመቱ የተመረመረ የፈንዱ ሒሳብን ለገንዘብና ለኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ማቅረብ ይገኙበታል፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲተር ወይም እርሱ የሚመድበው ኦዲተር በየዓመቱ የፈንዱን ሒሳብ የመመርመር ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ከተሰጠው ኃላፊነቶች መካከል ደግሞ የክልሎችን ድርሻ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ትንበያዎችን መሠረት በማድረግ መደልደል፣ ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር በመመካከር በፈንዱ ለሚሸፈኑ ፕሮጀክቶች የሚሰጥ የብድር ጣሪያ፣ የወለድ መጠን፣ የእፎይታ ጊዜና ተከፍሎ የሚያልቅበትን ጊዜ የተመለከቱ መመርያዎችን የማውጣትና የመወሰን ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡

ከፈንዱ ተጠቃሚ መሆን የሚችሉት በ18 እና በ34 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ማንኛቸውም ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን አዋጁ ያመለክታል፡፡

ከፈንዱ ተጠቃሚ ለመሆንም በጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ መደራጀት የሚጠበቅባቸው ሲሆን፣ ብድሩን ለማግኘት የንብረት ዋስትና የማይጠየቁ መሆኑን ያመለክታል፡፡ ከፈንዱ ለሚያገኙት ብድር ኃላፊነት እንዲሰማቸው ግን እርስ በርሳቸው ዋስ እንዲገቡ ይጠየቃል፡፡

ጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ ማለት ለሚለው የፌዴራል ከተሞች የሥራ ዕድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲን ለማቋቋም በወጣው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የተሰጠውን ትርጓሜ ይዟል፡፡

በዚህ ደንብ መሠረት ጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ ማለት የኢንተርፕራይዙን ባለቤት ሳይጨምር፣ የቤተሰቡን አባላትና ተቀጣሪ ሠራተኞችን ጨምሮ አምስት ሰዎችን የሚያሰማራና ጠቅላላ የካፒታሉ መጠን ሕንፃን ሳይጨምር በአገልግሎት ዘርፍ ከሆነ 50 ሺሕ ብር፣ በኢንዱስትሪ ዘርፍ ከሆነ ከብር አንድ መቶ ሺሕ ያልበለጠ መሆን እንዳለበት ተደንግጓል፡፡

በመሆኑም የአሥር ቢሊዮን ብር ተዘዋዋሪ ፈንዱ ተጠቃሚ መሆን የሚችሉ ወጣቶች ሊያገኙ የሚችሉት የካፒታልና የሥራ ማስኬጃ ብድር በኢንዱስትሪ ዘርፍ ከሆነ እስከ አንድ መቶ ሺሕ ብር፣ በአገልግሎት ከሆነ ደግሞ እስከ 50 ሺሕ ብር ነው፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሲኒመር ትሬዲንግ አ/ማ አባላት በሙሉ የጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ

ለሲኒመር ትሬዲንግ አ/ማ አባላት በሙሉ የጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ ሲኒመር ትሬዲንግ...

የባህር በር በቀጣናዊ ተዛምዶ ውስጥ

በበቀለ ሹሜ መግቢያ በ2010 ዓ.ም. መጋቢት ማለቂያን ይዞ ዓብይ አህመድ በጠቅላይ...

ሥጋት ያስቀራል ተብሎ የሚታሰበው የጫኝና አውራጅ መመርያ

በአዲስ አበባ ከተማ በሕገወጥ መልኩ በመደራጀት ማኅበረሰቡ ላይ እንግልትና...

ማወቅ ወይስ አለማወቅ – ድፍረት ወይስ ፍርኃት?

በአሰፋ አደፍርስ ወገኖቼ ፈርተንም ደፍረንም የትም አንደርስምና ለአገራችን ሰላምና ክብር...