Friday, September 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየጂቡቲ መንግሥት ለኢትዮጵያ የመደበውን የነዳጅ ዴፖዎች መጠን እንዲጨምር ሊጠየቅ ነው

የጂቡቲ መንግሥት ለኢትዮጵያ የመደበውን የነዳጅ ዴፖዎች መጠን እንዲጨምር ሊጠየቅ ነው

ቀን:

የጂቡቲ መንግሥት ለኢትዮጵያ የመደበውን የነዳጅ ማጠራቀሚያ ዴፓዎች መጠን እንዲጨምር የማግባባት ሥራ እንደሚያከናውን የማዕድን፣ ተፈጥሮ ጋዝና ፔትሮሊየም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስትሩ አቶ ሞቱማ መቃሳ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በጂቡቲ የነዳጅ ወደብ የሚገኙ ዴፓዎች ኢትዮጵያ ከምታስገባው የነዳጅ መጠን ጋር ማጣጣም አልተቻለም፡፡ በመሆኑም በመንግሥት ደረጃ ከጂቡቲ መንግሥት ጋር ድርድር መጀመሩ አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ሆራይዘን ተርሚናል የሚባለው የጂቡቲ የነዳጅ ወደብና ማጠራቀሚያ ተርሚናል ውስጥ ኢትዮጵያ ለምታስገባው ነዳጅ የተፈቀደው፣ አገሪቱ ከአሥር ዓመታት በፊት የምታስገባውን የነዳጅ መጠን መሠረት አድርጎ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ የምታስገባው የነዳጅ መጠን ቀድሞ ከነበረው 1.5 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ወደ 3.6 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ማደጉን ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትሩ አቶ ሞቱማ ባለፈው ሳምንት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተፈጥሮ ሀብትና አካባቢ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ፊት ቀርበው የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸማቸውን ባቀረቡበት ወቅት፣ በነዳጅ ሥርጭት ዘርፉ ያሉትን ችግሮች አብራርተዋል፡፡

በተለይ የነዳጅ ማደያ ጣቢያዎች ከአገሪቱ የቆዳ ስፋትና የፍላጎት መጠን ጋር ጥራታቸውና ሥርጭታቸው የማይጣጣም መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በአገር አቀፍ ደረጃ 700 ማደያዎች ብቻ እንዳሉ፣ ከእነዚህ ውስጥ 103 የሚሆኑት አዲስ አበባ እንደሚገኙ አስረድተዋል፡፡

በሕዝብ ብዛት ከኢትዮጵያ በእጅጉ የምታንሰው ኬንያ ውስጥ ከ1,700 በላይ የነዳጅ ማደያዎች እንዳሉ ገልጸው፣ በዚህ ውጥረት ምክንያት የትራንስፖርት ችግር ከተፈጠረ የነዳጅ ሥርጭቱ ላይ ከፍተኛ ችግር እንደሚታይ ተናግረዋል፡፡ በዘርፉ ውስጥ ያሉ ችግሮች በአግባቡ መፈታት እንዳለባቸውም አክለዋል፡፡

የጂቡቲ የነዳጅ ወደብና ተርሚናል የሚያስተዳደረው የኤሜሬትስ ናሽናል ኦይል ኩባንያ ሲሆን፣ በተርሚናሉ ላይ የ90 በመቶ ድርሻ እንዳለው መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

የዚህ ተርሚናል አጠቃላይ የመያዝ አቅም 399,304 ሜትሪክ ቶን እንደሆነ የድርጅቱ ድረ ገጽ ላይ ያለው መረጃ ያስረዳል፡፡

ኢትዮጵያ በዓመት የምታስገባው የነዳጅ መጠን 3.6 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የደረሰ ሲሆን፣ ይህ ተርሚናል ለአጭር ጊዜ የማስተናገድ አገልግሎት ነው የሚሰጠው፡፡

ከአጠቃላይ አቅሙ ላይም 30 በመቶ የሚሆነው በጂቡቲ ለሚገኘው የአሜሪካ የባህር ኃይል የተከራየ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

በመሆኑም በጂቡቲ መንግሥት ተጨማሪ የተርሚናል ግንባታ ካልተካሄደ፣ ኢትዮጵያ የምታስገባውን የነዳጅ መጠን ማስተናገድ እንደማይችል ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ዋናው መፍትሔም የነዳጅ ክምችቱን በፍጥነት ከተርሚናል ማንሳት የሚያስችል የሎጂስቲክስ አቅም መፍጠር መሆኑን አክለዋል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...