Monday, December 5, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊየመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ ከ25 ዓመታት በኋላ ወደ ግንባታ እንዲመለስ ተወሰነ

  የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ ከ25 ዓመታት በኋላ ወደ ግንባታ እንዲመለስ ተወሰነ

  ቀን:

  ከቀድሞው መንግሥት ውድቀት በኋላ ከመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ውጭ የተደረገው የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ፣ ከ25 ዓመታት ረጅም ቆይታ በኋላ ወደ ግንባታ መግባት የሚያስችለውን ፈቃድ አገኘ፡፡

  የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዓርብ ጥር 26 ቀን 2009 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ፣ የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ አደረጃጀቱ ተለውጦ ‹‹የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን›› በሚል ስያሜ በድጋሚ እንዲዋቀር ወስኗል፡፡

  በዚህ መሠረት አዲሱ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የቤቶች ልማት፣ የማከራየት፣ የጥገናና የማስተዳደር ሥልጣን ይኖረዋል፡፡ የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ በተለያዩ መዋቅሮች ውስጥ አልፎ በ2000 ዓ.ም. በአዋጅ ቁጥር 555 መሠረት አሁን የነበረውን ቅርጽ ይዟል፡፡

  ኮርፖሬሽኑ በመጀመሪያ ሲቋቋም በደርግ ዘመን በአዋጅ ቁጥር 47/1967 የተወረሱ ቤቶችን ለማስተዳደር ነበር፡፡ በአዋጅ ቁጥር 59/1968 የኪራይ ቤቶች አስተዳደር፣ በኋላም የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ በሚባሉ መዋቅሮች ውስጥ አልፏል፡፡

  የተሻሻለው የቤቶች አስተዳደር መመርያ ኤጀንሲው ያሉትን መኖሪያ ቤቶች ለተሿሚዎች ብቻ እንዲያቀርብ በመደንገጉና ተሿሚዎች ደግሞ ቁጥራቸው እየጨመረ በመምጣቱ፣ ተከራዮችን በማስለቀቅ ተጠምዶ ቆይቷል፡፡

  አዲሱ ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባና በድሬዳዋ ከተሞች 20 ሺሕ ያህል ቤቶችን ሲያስተዳድር ቆይቷል፡፡ ነገር ግን በመልሶ ማልማት ፕሮግራም የሚያስተዳድራቸው ቤቶች እየፈረሱ በመምጣታቸው፣በአሁኑ ወቅት 17 ሺሕ ቤቶችን ብቻ ያስተዳድራል፡፡ በአንፃሩ ደግሞ የመኖሪያ ቤት ፍላጎት እየጨመረ በመምጣቱ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቶ ቆይቷል፡፡

  የፓርላማ አባላት የሚኖሩባቸውን ሕንፃዎች ጨምሮ አሥር ሺሕ ያህል ቤቶችን መገንባቱን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

  ከዚህ በተጨማሪም ተቋሙ በመጨረሻ ይዞ በቆየው ቅርፅ በሲፒኤ አደረጃጀት የሚገኝ በመሆኑ፣ ሠራተኞች ከጥቅም አንፃር ቅሬታ ሲያቀርቡ ቆይተዋል፡፡ በዚህ ቅርፅ ውስጥ በማለፉም ነባሩ የሠራተኞች ማኅበር ሊፈርስ ችሏል፡፡

  የመሥሪያ ቤቱ ማኔጅመንት በተደጋጋሚ ወደ ቤቶች ግንባታ ለመመለስ ጥያቄ ቢያቀርብም፣ ፈቃድ ማግኘት ግን አልቻለም፡፡ ከተሞች በከፍተኛ ደረጃ እያደጉ በመምጣታቸው የዚያኑ ያህል የመኖሪያ ቤት እጥረት በመፈጠሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ኤጀንሲው በኮርፖሬሽን ደረጃ ተዋቅሮ ወደ ግንባታ እንዲገባ መመርያ መስጠታቸውን ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡  

  መንግሥት ይህንን ችግር ለመፍታት አራት ዓይነት ፕሮግራሞችን ቀርጾ ቢንቀሳቀስም፣ ዘግይቶም ቢሆን ኤጀንሲው ያለውን ልምድ ተጠቅሞ የመፍትሔው አካል እንዲሆን ወስኗል፡፡ 

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ዳግም ነፍስ የዘራው የተማሪዎች ማርች ባንድ

  የሙያው ፍቅር ያደረባቸው ገና በልጅነታቸው ነው፡፡ በ1970ዎቹ መጀመርያ፣ ለቀለም...

  በስንደዶና ሰበዝ የተቃኘው ጥበብ

  በአንዋር አባቢ ተወልዳ ያደገችው መሀል አዲስ አበባ አራት ኪሎ ነው፡፡...

  አዲስ ጥረት የሚጠይቀው  ኤችአይቪ  ኤድስን  የመግታት  ንቅናቄ

  ‹‹ኤችአይቪ በመላው ዓለም  በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚያጠቃ ዋነኛ የሕዝብ...

  የኅትመት ብርሃን ያየው ‹‹የቃቄ ወርድዎት›› ቴአትር

  ከአራት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ ላይ ይታይ...