Friday, February 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅ‹‹ተውበሻል አሉ ተውበሻል. . .››

‹‹ተውበሻል አሉ ተውበሻል. . .››

ቀን:

በደቡብ ኢትዮጵያ በቤንች ማጂ ዞን ከሚገኙ ብሔረሰቦች መካከል አንዱ የሆነው ሱርማ ከልዩ ልዩ መገለጫዎቹ አንዱ የተለየ የአለባበስ ባህል ያለው መሆኑ ነው፡፡ ልጃገረዶች አለባበሳቸው ከፊል ዕርቃንነትን ያጀበ ነው፡፡ ስለሱርማ የባህል እሴቶች የጻፈችው ለምለም መንግሥቱ እንደገለጸችው፣ ብትኑን ጨርቅ ከአንድ ወገን ቋጥረው በአንደኛው እጃቸው መካከል በማስገባት ቋጠሮው በትከሻቸው ላይ እንዲውል ያደርጉታል፡፡ ጨርቁ ሙሉ ለሙሉ አካላቸውን አይሸፍነውም፡፡ ከውስጥ ምንም አይነት ልብስ አይጠቀሙም፡፡ ማንኛውንም ዓይነት ብትን ጨርቅ ቢጠቀሙም በአብዛኛው ግን አቡጄዲን ይመርጣሉ፡፡ ለምለም በምልከታዋ እንደታዘበችውሱርማዎች ከአልባሳቱ ይልቅ ሙሉ ሰውነታቸውን በተለያየ ቀለማት ማስዋብ ያስደስታቸዋል፡፡ ውበት ያጎናጸፋቸውን ቀለም ልብ ብሎ ላየ ሰው ሠዓሊ በቀለም ብሩሹ የተጠበበት ይመስላል፡፡ ውብና ማራኪ ነው፡፡ ሰውነት ላይ እንዲህ በቀለማት የተለያየ ዲዛይን መሥራት በራሱ ድንቅ ነው፡፡  

                                                        ፎቶ አንጄላ ፊሸር

ሔኖክ መደብር

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

* * *

ኢትዮጵያ!

ሳለሽ ልትኖሪልኝ ሳለሁ ልኖርልሽ

ሳለን አንድ ኪዳን የሚያስተማምን

እንደ ጧፍ ነደንም እንደ ሰም ቀልጠን

እንደ ተያያዝን

አማን በአማን አማን በአማን

ለሰላምሽ ደምቀን እናበራለን

ለዙፋንሽ ክብር በመቅረዝሽ ላይ

እንደ ተተከለ ዐምደ ብርሃን

ሠርክ ኾነ ማለዳ ቀን ሌትም ቢኾን

ምን ጊዜም አይጠፋ ቃል ኪዳናችን

ለኪዳነ አዳም በታጨሽበት ምድር

ኢትዮጵያ በምድርሽ በብሔረ ሕያዋን፣

ያለም መፋረጃ መኾንሽ ዙፋን

መኾንሽም ሚዛን ለተዘነጋን፣

የምሕረት እጅሽ አይታጠፍብን

እንደ ተዘረጋ በዕለተ ደይን

ዘውድሽ ኢት ዮጳ የከበረ ሉል

ዕንቈ ጳዝዮን

ሕግሽም የወል ምክሓ ምዕመናን

ወመሃይምናን

ዓለም ግን ይመዘን በዚያ ፍርድ ቀን

የዚሁ ሥልጣን ባረገሽ መካን።

                                                                        ኃይለ ልዑል ካሣ ኅዳር 12 / 2010 ዓ.ም.

* * *

የኒውዮርክ ታይምስ የትዊተር ገጽ ለአንድ ቀን ተዘጋ

በኒውዮርክ ታይምስ ስም ከተመዘገቡ የትዊተር ገጾች መካከል የአንደኛው ገጽ ለአንድ ቀን ያህል ተዘግቶ መዋሉ ሥራ አስተጓጎለ፡፡ ዴይ ታይምስ ወርልድ ቲም የተባለው ይኼ ገጽ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ክስተቶችን በመዝገብ ይታወቃል፡፡ በየቀኑ 100 የሚሆኑ አዳዲስ መረጃዎችም ትዊት ያደርጋል፡፡ 1.9 ሚሊዮን ተከታዮች ያሉት ገጹ የታገደው የጥላቻ ንግግርን አስመልክቶ ትዊተር ያወጣውን ሕግ ተላልፏል በሚል ነው፡፡ ከጥላቻ ንግግር የተፈረጀው ጽሑፍ የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር በካናዳ ነባር የሆኑ ጎሳዎችን አስመልክቶ የተናገሩትን ንግግር በማስፈሩ ነው፡፡ ገጹ ከ24 ሰዓታት በኋላ መከፈቱን ቢቢሲ ሰግቧል፡፡

የኒውዮርክ ታይምስ የትዊተር ገጽ ለአንድ ቀን ተዘጋ

***

 

በነዳጅና በኤሌክትሪክ የሚሠራ አውሮፕላን ሊሠራ ነው

ሮልስ ዴይስና ሳይመዝ የተባሉ ግዙፍ የበረራው ኢንዱስትሪ ኩባንያዎች በነዳጅና በኤሌክትሪክ የሚሠራ አውሮፕላን ለመሥራት ተስማሙ፡፡ 100 ሰዎችን ማሳፈር የሚችለው አዲስ አውሮፕላን እ.ኤ.አ. በ2020 የሙከራ በረራ እንደሚያደርግ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ እ.ኤ.አ. በ2030ም ምርቱ ወደ ገበያ ይገባል፡፡ በኤሌክትሪክ የሚሠራ አውሮፕላን ለመሥራት የተስማሙት ከበረራው ኢንዱስትሪ የሚወጣውን የጋዝ ልቀት ለመቀነስ ከአውሮፓ ኅብረት በኩል በተደጋጋሚ ጥሪ በመቅረቡ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ይኼንን አዲስ ቴክኖሎጂ ለመሥራት በመቶ ሚሊዮን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ ወጪ ይደረጋል፡፡

በነዳጅና በኤሌክትሪክ የሚሠራ አውሮፕላን ሊሠራ ነው

* * *

 

የራሱን የትራፊክ ምልክት የሠራው ቻይናዊ ተቀጣ

የ28 ዓመቱ ቻይናዊ ካይ፣ ዘወትር ወደ ሥራ ሲሄድ በትራፊክ መጨናነቅ ምክንያት ሥራ መድረስ ካለበት ሰዓት ይዘገያል፡፡ ሁሌ በሚጓጓዝበት መንገድ ወደ አንድ አቅጣጫ የሚሄዱ መኪኖች ዘለግ ያለ ጊዜ ስሚወስዱ ለመሻገር ይቸገራል፡፡ ቻይናዊው ለዚህ ችግሩ መፍትሄ ብሎ ያሰበው ወደ አንድ አቅጣጫ የሚሄዱትን መኪኖች አቅጣጫ ማስለወጥ ነበር፡፡ አንድ ቀን ጠዋት ተነስቶም፣ የአገሪቱ የትራፊክ ፖሊስ ከፈቀደው የትራፊክ አቅጣጫ በተጨማሪ፣ ተሽከርከሪዎች ወደ ሌላ አቅጣጫ እንዲሄዱ የሚያሳይ ምልክት አስፋልቱ ላይ በነጭ ቀለም መሣል ጀመረ፡፡ ሁኔታውን በደህንነት መቆጣጠሪያ ካሜራ ይከታተሉ የነበሩ ፖሊሶች አቅጣጫ መጠቆሚያውን በመሣል ላይ ሳለ በቦታው ደርሰው በቁጥጥር ሥር እንዳዋሉትም ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ ‹‹የትራፊክ አቅጣጫ መለወጫ ቀለም የቀባሁት መኪኖች በተለያየ አቅጣጫ እንዲሄዱና ቶሎ መሻገር እንድችል ነው፤›› ሲል ነበር የተናገረው፡፡ ሆኖም የአገሪቱ የትራፊክ ፖሊሶች፣ ወጣቱ በቁጥጥር ሥር ሳይውል የትራፊክ ምልክቱን አስፋልት ላይ ሠርቶ ቢጨርስ ኖሮ በርካታ የመኪና  አደጋዎች ይከሰቱ እንደነበር ገልጸው፣ 151 ዶላር ቀጥጠውታል፡፡

የራሱን የትራፊክ ምልክት የሠራው ቻይናዊ ተቀጣ

 

* * *

በኢንስታግራም ፎቶ የባሏን አለመታመን ያወቀችው እንግሊዛዊት

እንግሊዛዊቷ ዮሊያ አግራምቪች ባሏ ከሌላ ሴት ጋር እየማገጠ መሆኑን ያወቀችው ባልተለመደ ሁኔታ ነበር፡፡ ከሰሞኑ በሜትሮ ዮኬ የተለቀቀው ዘገባም፣ የብዙዎች መነጋገሪያ ሆኗል፡፡ በኢንስታግራም ገጽ ላይ የተለያዩ መረጃዎችን ስትመለከት ‹‹የከማዋ መብራቶች›› በሚል ስያሜ የተለቀቀ ከአንድ ቤት ወደ ውጪ የተነሳ የመኪኖች ፎቶ ታያለች፡፡ ፎቶውን ስታጤነው ከሷና ከባለቤቷ መኝታ ክፍል የተነሳ መሆኑን ደረሰችበት፡፡ ፎቶውን በኢንስታግራም የለጠፈችው ሌላ ሴት በመሆኗም ጥርጣሬ ገባት፡፡ በሴትየዋ የኢንስትታግራም ገጽ ላይ የተለቀቁ ሌሎች ፎቶዎችን ስትመለከት ሴትየዋ ከባለቤቷ ጋር የተነሳቻቸውን ፎቶዎች አገኘች፡፡ ባሏ ታማኝ እንዳልሆነ ያወቀችው ሴት ባለቤቷን ከመፍታት ባሻገር ታሪኩ ለሌሎች መማሪያ እንዲሆን ብላ የኢንስታግራም መነጋገሪያ አድርጋዋለች፡፡

በኢንስታግራም ፎቶ የባሏን አለመታመን ያወቀችው እንግሊዛዊት

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ የካቤኔ አባል የሆኑት አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሚያቀርቡትን ቅሬታ እያዳመጡ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር በእጅጉ ስላሳሰበኝ ነው በአካል...

የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔና የሶማሊያ ፕሬዚዳንት የፈጠሩት አምቧጓሮ

ባለፈው ቅዳሜና እሑድ በአዲስ አበባ የተካሄደው የአፍሪካ ኅብረት 37ኛው...

የብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ትግበራ የፈጠራቸው አሉታዊና አዎንታዊ ጎኖች

የአገሪቱ ንግድ ባንኮች በዓመት የሚሰጡት የብድር መጠን ላይ የኢትዮጵያ...

ቱግ ቱግ!

የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ ለመታደም የመጡ እንግዶችን ሸኝተን ከፒያሳ ወደ...