Thursday, February 22, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

በአማራ ክልል የመጀመርያው የመድኃኒት ፋብሪካ ሥራ ሊጀምር ነው

ተዛማጅ ፅሁፎች

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሀገረ ማርያም ወረዳ ቱለፋ ከተማ የተቋቋመው የመጀመርያው የመድኃኒት ፋብሪካ ሥራ ሊጀምር ነው፡፡

በቻይና ባለሀብቶች የተቋቋመውና ሒዩማን ዌል ፋርማሲዩቲካል በተሰኘው ድርጅት አማካይነት በአማራ ክልል ለመጀመርያ ጊዜ የተቋቋመው ‹‹ሒዩማን ዌል›› የተሰኘውና የመጀመርያ የሆነው የመድኃኒት ፋብሪካ፣ እሑድ ኅዳር 24 ቀን 2010 ዓ.ም. ተመርቆ ሥራ እንደሚጀምር የአማራ ክልል ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ይኼነው ዓለም ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

በሰሜን ሸዋ ዞን ሀገረ ማርያም ወረዳ ቱለፋ ከተማ ላይ የተቋቋመው የመድኃኒት ፋብሪካ ለ89 ዜጎች በቋሚነትና ለ209 ዜጎች በጊዜያዊነት የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር የተናገሩት ደግሞ፣ የሰሜን ሸዋ ዞን ኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ቡድን መሪ አቶ ዮሐንስ ሽፈራው ናቸው፡፡

አቶ ዮሐንስ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ሒዩማን ዌል ፋርማሲዩቲካል የተሰኘው ድርጀት በክልሉ የመጀመርያውን የመድኃኒት ፋብሪካ ያቋቋመው በሰባት ሔክታር መሬት ላይ ነው፡፡ ድርጅቱ ለፋብሪካው ግንባታም ሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ለማድረግ ውል እንደገባና በውሉ መሠረት ሠርቶ እንዳጠናቀቀ ጠቁመዋል፡፡

በአማራ ክልል ከኃይል መቆራረጥና ጋር በተያያዘ ከ100 በላይ ድርጅቶች ወደ ሥራ መግባት እንዳልቻሉ ከዚህ በፊት መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን፣ ችግሩን ለመቅረፍም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አዳዲስ የኃይል ማሠራጫ ጣቢያዎችን ለመገንባትና ነባሮችን በአዳዲስ ለመተካት በእንቅስቃሴ ላይ መሆኑን አቶ ይኼነው ጠቁመዋል፡፡ 

በአራት ወራትም ከአራት መቶ በላይ የሚሆኑ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መውሰዳቸውንና ወደ ሥራ ለመግባት እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ በካፒታል ደረጃም 8.15 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሀብቶች ፈቃድ ያወጣሉ ተብሎ በዕቅድ ተይዞ፣ 13.3 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መውሰድ መቻላቸውን አቶ ይኼነው አስረድተዋል፡፡

የኢንቨስትመንት ፈቃድ የወሰዱ ባለሀብቶች በዋናነት በኮንስትራክሽን፣ በማኑፋክቸሪንግና በሌሎች ዘርፎች ለመሠማራት ያቀዱ መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች