Tuesday, September 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊሶሻል ኢንተርፕራይዞችን የሚያስተዳድር ፖሊሲ እንዲወጣ ተጠየቀ

ሶሻል ኢንተርፕራይዞችን የሚያስተዳድር ፖሊሲ እንዲወጣ ተጠየቀ

ቀን:

ከበጎ አድራጎትና ከንግድ ድርጅቶች ጋር የሚመሳስል ባህሪ ያላቸው የማኅበራዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት(ሶሻል ኢንተርፕራይዞች) የሚተዳደሩበት ራሱን የቻለ ፖሊሲ እንዲወጣላቸው ተጠየቀ፡፡  

ተቋማቱ የተለያዩ አገልግሎቶችንና ምርቶችን በመሸጥ ገቢ የሚያገኙ ሲሆን፣ የሚያገኙት ትርፍ ሥራቸውን ለማጠናከር አሊያም ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሥራዎችን ለመሥራት የሚውል ነው፡፡ ይህ ከሌሎቹ ተቋማት የሚለያቸው ቢሆንም እነሱን የሚያስተዳድር የተለየ ሕግ ባለመኖሩ በበጎ አድራጎት፣ በግል ድርጅትነትና በንግድ ተቋማት ስም ተመዝግቦ ለመሥራት መገደዳቸውን፣ ይህም ሥራቸውን እያደናቀፈው እንደሚገኝ ‹‹ሰርቬይንግ ሶሻል ኢንተርፕራይዝ ኢን ኢትዮጵያ›› በሚል ሰሞኑን ይፋ የተደረገው የዳሰሳ ጥናት ጠቁሟል፡፡

በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በትግራይና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት በሚገኙ ማኅበራዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ የተካሄደው ጥናት፣ የመነሻ ገንዘብ፣ ድጋፍ፣ በዘርፉ የተሠማሩ አማካሪ ድርጅቶች አለመኖር፣ የሠለጠነ የሰው ኃይል እጥረት፣ የሚያቀርቡት ምርትና አገልግሎት በገበያ ላይ ያለው ፍላጎት ዝቅተኛ መሆን፣ ስለማኅበራዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ያለው አነስተኛ ግንዛቤ ፣ ግብር፣ ተጨማሪ እሴት ታክስና የመሳሰሉት መሰናክሎች ዕድገቱን እንደሚፈለገው እንዳይሆን ማድረጉን ጥናቱ አሳይቷል፡፡

 ለዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠርና የማኅበረሰቡን ሕይወት በመለወጥ ረገድ እገዛ የሚያደርጉ ተቋማትን መንግሥት በአግባቡ ሊያሠራ የሚችል የህግ ማዕቀፍና ፖሊሲ በማውጣት የልማት አጋር ማድረግ ጥናቱ በምክረ ሀሳቡ አስፍሯል፡፡

የጠብታ አምቡላንስ ጀኔራል ማናጀር አቶ ክብረት አበበ፣ ማኅበረሰቡ ስለማህበራዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ያለው ግንዛቤ የተዛባ በመሆኑና የሚተዳደሩበት ፖሊሲ አለመኖር ስራቸውን ለመሥራት አስቸጋሪ እንዳደረገው ተናግረዋል፡፡ ‹‹ሥራ ለመጀመር የገንዘብ ብድር ለማግኘት ብዙ ተንከራትቻለሁ፡፡ የካሽ ሬጂስተር ማሽን ካላስገባችሁ ተብሎም ከብዙ ድካም በኋላ እንዲቀር ተደርጓል፡፡ በየቀኑ የተለያዩ ችግሮች እየገጠሙን ይገኛሉ፤›› ሲሉም የችግሩን ጥልቀት አስረድተዋል፡፡

በከተማ ቤቶች ልማት ሚኒስቴር የከተሞች ፅዳትና አረንጓዴ ውበት ዘርፍ አማካሪዋ ወ/ሮ እሩቅያ ሰዒድ በበኩላቸው፣ ተቋማቱን ማስተዳደር የሚችል በግልጽ ተለይቶ የወጣ ፖሊሲ ባይኖርም፣ አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን በሚያስተዳድረው ፖሊሲ ውስጥ ተቋማቱን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች መኖራቸውን ገልፀዋል፡፡

ተቋማቱ መብታቸውን ለማስከበር ባለባቸው ድክመት፣ በአመራር የአቅም ውስንነትና በአፈጻጸም ችግሮች ድንጋጌዎቹ ተግባራዊ እንዳልኑም ተናግረዋል፡፡   ተግባራቸው በትክክል ተለይቶ ሳይታወቅ፣  በንግድ ተቋምና በበጎ አድራጎ ድርጅት ስም ተመዝግበው ሲሰሩ የቆዩት ተቋማት፣ ላይ የተሰራው ጥናት ያለውን ክፍተት አሳይቶናል፡፡ በቅርቡም ፖሊሲ ይወጣል የሚሉት ወ/ሮ እሩቅያ፣ ፖሊሲው ከወጣ በኋላ የተቋማቱ ባህሪ ተጠንቶ የማስተዳደር ሥልጣኑ ለአንድ ተቋም እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡

የብሪቲሽ ካውንስል ሰኞ ጥር 22 ቀን 2009 ዓ.ም. የማኅበራዊ አገልግት ሰጪ ተቋማትን አጠቃላይ ሁኔታ አስመልክቶ በካፒታል ሆቴል ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ በአገሪቱ 54,000 የሚሆኑ የማኅበራዊ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

አብዛኛዎቹ ተቋማትም የሚገኙት በክልሎች ሲሆን፣ በአማራ ክልል 25 በመቶ፣ በትግራይ 24 በመቶ፣ በአዲስ አበባ 22 በመቶ፣ በኦሮሚያ 16 በመቶ፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ደግሞ 13 በመቶ ተሠራጭተው እንደሚገኙ በጥናቱ ተገልጿል፡፡

በጤና፣ በእርሻ፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በአገልግሎና በመሳሰሉት ሴክተሮች የተሠማሩት ተቋማቱ፣ በአብዛኛው በወጣቶች የተያዙ ናቸው፡፡ ሴቶቹን በማሣተፍ ረገድም ከሌሎቹ የሥራ መስኮች አንፃር የተሻሉ ናቸው ተብሏል፡፡ የብሪቲሽ ካውንስል በሚያደርገው ድጋፍ ኢትዮጵያን ጨምሮ በ27 አገሮች የሶሻል ኢንተርፕራይዝ ፕሮግራም በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የቤት ባለንብረቶች የሚከፍሉትን ዓመታዊ የንብረት ታክስ የሚተምን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

በአዋጁ መሥፈርት መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የንብረት ታክስ መጠን...

እንደ ንብረት ታክስ ያሉ ወጪን የሚያስከትሉ አዋጆች ከማኅበረሰብ ጋር ምክክርን ይሻሉ!

የመንግሥትን ገቢ በማሳደግ ረገድ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚታመኑት የተጨማሪ እሴት...

ለዓለምም ለኢትዮጵያም ሰላም እንታገል

በበቀለ ሹሜ ያለፉት ሁለት የዓለም ጦርነቶች በአያሌው የኃያል ነን ባይ...