Friday, December 2, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ስፖርትየአፍሪካ ዋንጫ ፍጻሜ ግማሽ ላይ ደረሰ

  የአፍሪካ ዋንጫ ፍጻሜ ግማሽ ላይ ደረሰ

  ቀን:

  የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ውድድርን ለመመልከት ከአዘጋጅ አገሮች ሽር ጉድ ባሻገር በተለይ በኢትዮጵያ ተመልካቾች ዘንድ በጉጉት የሚጠበቅ ነበር፡፡ ዋነኛው ውድድር እንደዚኛው ዘመን ቴክኖሎጂው ባለተስፋፋበት ጊዜ እንኳን ውድድሩን ለመመልከት የነበረው እንቅስቃሴ ልዩ እንደነበር አይዘነጋም፡፡

  በሌላ በኩልም የፖስተር፣ የካላንደርና የታዋቂ ተጫዋቾች ቁጥር የያዘ መለያ በየመደብሮች መመልከትም ውድድሩን የበለጠ ተጠባቂ ያደርገው ነበር፡፡

  31ኛውን የቶታል የአፍሪካ ዋንጫ በምዕራብ አፍሪካዋ ጋቦን ጥር 6 ቀን 2009 ዓ.ም. በ16 አገሮች መካከል ተጀምሮ፣ የመጨረሻዎቹ አራት አገሮች ተለይተዋል፡፡ ከነዚህም ለፍጻሜ ግማሽ የተፋጠጡት ቡርኪና ፋሶ፣ ግብፅ፣ ካሜሮንና ጋና ናቸው፡፡

  በነበራቸው የተጫዋቾች አቅምና ወቅታዊ አቋም ቅድሚያ የማሸነፍ ግምት የተሰጣቸው አልጄሪያ፣ አይቨሪኮስትና አዘጋጀዋ ጋቦንና ማሊ ወደ ሩብ ፍጻሜ መግባት ሲሳናቸው፣ ሴኔጋል፣ ኮንጎ፣ ሞሮኮና ቱኒዚያ ግማሽ ፍጻሜውን መሻገር ተሰንዋቸው ወደየአገራቸው አቅንተዋል፡፡

  የአፍሪካ ዋንጫን ሰባት ጊዜ ያነሳቸው ግብፅ ባለፉት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያዎች ማለፍ ተስኗት ነበር፡፡ ከ2002 ዓ.ም. ወዲህ በዘንድሮ ተሳክቶላት ግማሽ ፍጻሜውን መቀላቀል ችላለች፡፡ ወደ ዋንጫ ጨዋታም ለማቅናት ዛሬ ጥር 24 ቀን 2009 ዓ.ም. ምሽት ከቡርኪና ፋሶ ጋር የምታደርገው ጨዋታ ይጠበቃል፡፡ በማግስቱ ካሜሮን ከጋና አቻው በሚያደርገው ጨዋታ እሑድ ጥር 28 ቀን ለሚከናወነው ፍጻሜ የሚደርሰውን ይለያል፡፡

  የዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ብሔራዊ ቴሌቪዥን አለማስተላለፉ ጨዋታዎችን በቀላሉ ለመከታተል አዳጋች እንዳደረገው ይነገራል፡፡  

  በተጨማሪ ደግሞ በአፍሪካ ብሔራዊ ቡድናቸውን ወክለው የሚጫወቱት በተለያዩ ዓለም አቀፍ የክለቦች ውድድር ላይ ተሳታፊ የሆኑ ተጫዋቾች በክለቦቻቸው በጥብቅ መፈለጋቸው አነጋጋሪ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ለዚህም ምሳሌ ይህን ዘንድ የሊቨርፑሉ አማካይ ሰይዶ ማኔ፣ የአልጄሪያው ሪያድ መሀሬዝ፣ የጀርመኑ ክለብ ዶርቶመንድ ፍሬ የሆነው አቦሞያንግ ለእግራቸው መሠለፍ ቢችሉም ውጤታማ አልሆኑም፡፡ የክለቦቻቸው ደጋፊዎች ያደርጉት የነበረው የቶሎ ይመለሱ ጉትጎታ ከአገራቸው ጋር ብዙ ውድድር ላይ ገነው የወጡት ተጫዋቾች በውድድሩ ላይ ያለመቆየት ለአፍሪካ ዋንጫው መደብዘዝ እንደ ምክንያት ይጠቀሳል፡፡

  60 ዓመታትን ያስቆጠረው የአፍሪካ ዋንጫ ግብፅ ሰባት ጊዜ ዋንጫ በማንሳት ቀዳሚ ስትሆን፣ ጋናና ካሜሮን አራቴ፣ ናይጄሪያ ሦስቴ፣ እንዲሁም አይቮሪኮስት ሁለቴ ዋንጫውን በማንሳት እንደየደረጃቸው ተቀምጠዋል፡፡ ኢትዮጵያ በ1954 ዓ.ም. አዘጋጅ በመሆን ውድድሩን ማሸነፍ ችላ ነበር፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...