በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ የሚገኘውና 547 ሲኒዎችን የያዘው ረከቦት
******
ይዞ ጠፊ
ብቻውን የበላ ብቻውን ይሞታል
ይሉ ተረት ሰምቶ፤
አንድም በይሉኝታ አልያም ለነፍስያው
መሰሰትን ፈርቶ፤
ከዘመድ ከወዳጅ ቁጥር ሳያጎድል
ከሁሉም ተስማምቶ፤
ብቻውን እንዳይሞት ከወደደው በላ
አደባባይ ወጥቶ፡፡
እንዲኽ ያለ ለጋስ ሆዱን ያልወደደ
ማንንም ያልጠላ፤
ያለውን ሳይቆጥብ ሳይደብቅ ሳይሸሽግ
ሳይል ወደኋላ፤
ምን ያህል ደግ ነው ሞቱን እያሰበ
አካፍሎ ያበላ?
- መላኩ ደምለው ወልደጊዮርጊስ ‹‹ብልጭታ›› (2008)
******
ጀርመን የውጭ አገር መሪዎችን መስደብ የሚከለክለውን ሕጓን ሻረች
እስከዛሬ በጀርመን ሕግ ማንም ጀርመናዊ በጀርመን ምድር ላይ የውጭ አገር መሪዎችን በግልጽም ይሁን በተዘዋዋሪ ቢሰድብ ተጠያቂ የሚሆንበት ሕግ ነበር፡፡ ነገር ግን የትራምፕ ሹመት በዓልን ተከትሎ ጀርመን ይህን ሕጓን ማንሳቷን ዘ ኢንዲፔንደንት ዘግቧል፡፡ ባለፈው ዓመት በቱርኩ ፕሬዚዳንት የተሳለቀው ጀርመናዊው ኮሜዲ ለክስ ተዳርጐ ነበር፡፡ ይህ ሕግ በመሻሩ የሌሎች አገር መሪዎችም የሰደበና ክብራቸውን የነካ ጀርመናዊ ተላልፎ እንዲሰጣቸው መጠየቅ አይችሉም፡፡ የጀርመን ፍትሕ ሚኒስትር ሒኮ ማስ ሕጉን ዘመን ያለፈበትና አላስፈላጊ ብለውታል፡፡
******
እኩለ ሌሊት ላይ ነቅተው መተኛት ቢያቅትዎ?
እኩለ ሌሊት ላይ ከእንቅልፍ ነቅቶ መልሶ መተኛት እንደ አለመቻል ከባድ ነገር የለም በሚለው ብዙዎች ይስማማሉ፡፡ እንዲህ ነቅተው መልሰው መተኛት ጭንቅላትን ማባበል አስቸጋሪ ቢሆንም የእንቅልፍ ስፔሻሊስቱ ሚሼል ብሩስ ጠቃሚ ያሏቸውን ነገሮች ይገልጻሉ፡፡ በጣም አስፈላጊ ካልሆነ በቀር ወደ መታጠቢያ ቤት አለመሄድና ዘና ማለት ነገር ግን ሰዓት አለመመልከት ናቸው፡፡ ከአልጋ መውረድ በእንቅልፍ ላይ የሚኖረውን የልብ ምት ሥርዓት ማለትም በደቂቃ 60 ጊዜ መምታት ስለሚያደናቅፍ ይበልጥ ከእንቅልፍ ስሜት እንዲወጡ ሊያደርግ ይችላል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሰዎች ከእንቅልፍ ሲነቁ መጀመሪያ የሚያደርጉት ነገር ሰዓት መመልከትና ስንት ሰዓት ቀረኝ የሚለውን ማስላት ሲሆን ብሩስ ይህ ይበልጥ ውጥረትን በማንገሥ ሰዎች መልሰው እንዳይተኙ እንደሚያደርግ ያስጠነቅቃሉ፡፡
******
ወደ ቤቱ ለመሄድ በስህተት 500 ኪሎ ሜትር የነዳው ሰው
የቻይናን አዲስ ዓመት በማስመልከት በመላ አገሪቱ በሳይክል ከዞረ በኋላ ወደ ቤቱ ለመመለስ አስቦ የነበረው ቻይናዊው በስህተት 500 ኪሎ ሜትር ርቀት መሄዱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ ቻይናዊው 1,700 ኪሎ ሜትር ከነዳ በኋላ ወደ ቤቱ ለመመለስ ነበር ያሰበው፡፡ ነገር ግን በጉዞው ማጠናቀቂያ ወደ መኖሪያ ቤቱ ለመመለስ የመረጠው መንገድ የተሳሳተ ስለነበር ተጨማሪ 500 ኪሎ ሜትር ለመጓዝ ተገድዷል፡፡ ይህ ስህተቱ ሲታወቅ ፖሊስ ለቻይናዊው የባቡር ትኬት በመቁረጥ ወደ ቤቱ እንዲመለስ ለማድረግ ቢሞክርም ቻይናዊው አሁንም በሳይክሉ መመለስን ነበር የመረጠው፡፡ ቢሆንም ለሳይክል በማይፈቀድ ሃይዌ ሲያሽከረክር ፖሊስ ይዞታል፡፡
Meskerem