Friday, March 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየአዲስ አበባ ብስክሌት ፌዴሬሽን የውድድር መርሐ ግብሮቹን ይፋ አደረገ

የአዲስ አበባ ብስክሌት ፌዴሬሽን የውድድር መርሐ ግብሮቹን ይፋ አደረገ

ቀን:

በቅርቡ ከኮካ ኮላ ኩባንያ ጋር የአንድ ዓመት የስፖንሰርሽፕ ስምምነት ያደረገው የአዲስ አበባ ብስክሌት ፌዴሬሽን ከእሑድ ጥር 21 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ በተከታታይ የሚያካሂደውን የውድድር መርሐ ግብር ይፋ አድርጓል፡፡ ፌዴሬሽኑ ለሪፖርተር በላከው መግለጫ እንዳመለከተው፣ በዙር በግል ክሮኖ ሜትር (የሰዓት ውድድር) እንዲሁም የጎዳና ውድድሮች በሚስተናገዱበት የብስክሌት ውድድር ከክለቦች፣ ከታዳጊ ወጣቶች ፕሮጀክቶችና ከግል የተውጣጡ ተሳታፊዎች የሚካፈሉበት ነው፡፡

ብስክሌት ፌዴሬሽኑ ከኮካ ኮላ ኩባንያ ጋር በመተባበር በየዓመቱ የሚያናውነው ይኼው የብስክሌት ውድድር ሰባት ክለቦችን ጨምሮ በሁለቱም ጾታዎች ከአሥር እስከ 133 ኪሎ ሜትር ርቀት በሚሸፈኑ የተለያዩ አካበቢዎች ይካሄዳል ተብሎ እንደሚጠበቅ የድርጊት መርሐ ግብሩ ያሳያል፡፡

በዚሁ መሠረት በክለብ እህል ንግድ፣ ጋራድ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ፣ የካ ክፍለ ከተማ፣ የኢትዮጵያ ወጣቶች አካዴሚ፣ የአፍሪካ ስደተኞች ክለብና የግል ተወዳዳሪዎች ሲሳተፉ፣ በታዳጊ ፕሮጀክት የሚወዳደሩት ደግሞ የካ፣ አራዳ፣ ኮልፌ ቀራኒዮ፣ ቦሌ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ ጉለሌና ልደታ ክፍለ ከተማዎች ናቸው፡፡

ውድድሮቹ የሚከናወኑባቸው አካባቢዎችና የሚሸፍኑት ርቀት ቀጥሎ የተመለከተ ነው፡፡

 

ተቁ.

ቀን

የውድድር ዓይነት

የውድድር ቦታ

የውድድር ካታጎሪ

 

 

 

 

በታዳጊ ማውንቴን

የቀድሞ ብስክሌተኞች

በሴቶች ማውንቴን

በወንዶች ማውንቴን

በኮርስ ወንዶች

1

21/05/09

የጎዳና

ዓለም ገና ወደ ቡታጅራ

133 ኪ.ሜ

2

28/05/09

የዙር

ካራ ወሰን

15 ኪ.ሜ

10 ኪ.ሜ

40 ኪ.ሜ

60 ኪ.ሜ

100 ኪ.ሜ

3

01/06/09

የግል ክኖሮ

ጽዮን

7 ኪ.ሜ

10 ኪ.ሜ

20 ኪ.ሜ

4

05/06/09

የዙር

ሳሊተምሕረት ፊጋ

20 ኪ.ሜ

15 ኪ.ሜ

40 ኪ.ሜ

60 ኪ.ሜ

120 ኪ.ሜ

5

08/06/09

የጎዳና

ከለገጣፎ ወደ ሸኖ

60 ኪ.ሜ

80 ኪ.ሜ

6

09/06/09

የጎዳና

ከለገጣፎ ወደ ደ/ብርሃን

110 ኪ.ሜ

7

12/06/09

የዙር

ልደታ

20 ኪ.ሜ

15 ኪ.ሜ

40 ኪ.ሜ

70 ኪ.ሜ

120 ኪ.ሜ

8

16/06/09

የቡድን ክሮኖ

ከጎሮ ወደ ቱሉዲምቱ

20 ኪ.ሜ

40 ኪ.ሜ

9

19/06/09

የዙር

ጽዮን

15 ኪ.ሜ

15 ኪ.ሜ

40 ኪ.ሜ

60 ኪ.ሜ

100 ኪ.ሜ

10

23/06/09

የዳገትና ሜዳ

እንጦጦ ማርያም

5 ኪ.ሜ

10 ኪ.ሜ

11

26/06/09

የዙር

ካራ ወሰን

15 ኪ.ሜ

15ኪ.ሜ

40 ኪ.ሜ

60 ኪ.ሜ

80 ኪ.ሜ

12

03/07/09

የዙር

ስታዲየም ዙሪያ

10 ኪ.ሜ

10 ኪ.ሜ

20 ኪ.ሜ

30 ኪ.ሜ

50 ኪ.ሜ

 

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...