Friday, September 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

‹‹ሩቅ ምሥራቅ ሳለሁ. . .››

ትኩስ ፅሁፎች

የሁለት ጊዜ ኦሊምፒክ ማራቶን ባለወርቁ አበበ ቢቂላ (በግራ) እና ዋሚ ቢራቱ፣ ከ52 ዓመት በፊት (ግንቦት 1 ቀን 1957 ዓ.ም.) ቶኪዮ አጠገብ በምትገኘው ኦትሱ ከተማ፣ ከወርቃዊ ድላቸው በኋላ (ሔኖክ መደብር)

*******

ሁሉም ውብ ነው!

‹‹ከንቱ! ከንቱ! ሁሉም ከንቱ!

የከንቱ ከንቱ ነው! ከንቱ!››

ነበር ያለው ይኼ ከንቱ?

ምን ነካው ሊቀ ሰሎሞን፣ ምን ሆኗል ታላቁ ንጉሥ?

ስንቱን ጥበብ የሚፈታ እንቆቅልሽ የሚመልስ

የሰው ንግሥት ሆድ እሚያርስ

ቅኔ እንደ ውኃ የሚያፈልቅ የጣፈጠ ንግግሩ

‹‹የከንቱ ከንቱ ነው!›› ብሎ ምነው ፍጡር ማሸበሩ?

‹‹ከንቱ! ከንቱ! ሁሉም ከንቱ?››

ነበር ያለው ይኼ ከንቱ?

ቢራቢሮን ተመልከታት

ውቧ አደይን ቀርበህ እያት

ሕፃን ልጅህን ‹‹ዳዴ›› በላት

ከጥጆች ጋር ቦርቅ – ጨፍር

ከወፎች ጋር አብረህ ዘምር

ውደድ፣ ጥላ፣ አልቅስ፣ አፍቅር

ሜዳ፣ አቀበት፣ ሸለቆውም

ሰውና አዝርዕት፣ እንስሳቱም

ምሽት፣ንጋት፣ ሰማይ፣ ምድሩም

ሁሉም ውብ ነው ሁሉም ግሩም

‹‹ተመስገን!›› በል ፈጣሪህን

ሕይወት፣ ውበት የሰጠህን

ሁሉም ውብ ነው የምን ከንቱ?

‹‹ከንቱ!›› ማለት ብቻ ከንቱ!!

  • ሰሎሞን ሞገስ፣ ‹‹ከፀሐይ በታች›› (2004)

*******

‹‹የአገሬ ንቅሳት››

በሙሉዓለም ተገኘወርቅ የተጻፈው ‹‹የአገሬ ንቅሳት›› የተሰኘው የግጥም መድበል ለንባብ በቅቷል፡፡ ጸሐፊው ከዚህ ቀደም ‹‹ኡኡ›› የተሰኘ የግጥም መድበልና ‹‹የአመዳ ገጾች›› የተባለ የግጥም ሲዲ አሳትሟል፡፡ ‹‹የአገሬ ንቅሳት›› 119 ገጽ ያለው ሲሆን፣ በ50 ብር እየተሸጠ ነው፡፡

********

ሽንት ቤት ለሚጠቀሙ አሽከርካሪዎች የተዘጋጀው ፓርኪንግ

እያሽከረከሩ ሽንት ቤት መጠቀም ቢፈልጉ ምን ያደርጋሉ? ከተጨናነቀ ትራፊክ ወጥተው ሽንት ቤት ለመጠቀም መኪና ፓርክ ማድረግ ቢፈልጉስ? ቻይና የብዙ አሽከርካዎች ፈተና የሆነውን ይህን ችግር ለመቅረፍ አሽከርካሪዎች ሽንት ቤት መጠቀም ሲፈልጉ መኪና ፓርክ የሚያደርጉበት ቦታ ማዘጋጀቷን በቅርቡ አስታውቃለች፡፡ ፓርኪንጉ የተዘጋጀው በማዕከላዊ ቻይና ሲሆን፣ ወደ 50 በሚደርሱ የሕዝብ መፀዳጃ ቤቶች አቅራቢያ የፓርኪንግ ቦታ ተዘጋጅቷል፡፡ የቻይናውን ሁአ ሻንግ ባኦ ጠቅሶ ቢቢሲ እንደዘገው፣ አንድ አሽከርካሪ ለፓርኪንግ በተሰጠው ቦታ ከ15 ደቂቃ በላይ መቆየት አይችልም፡፡ ሽንት ቤት ለመጠቀም ለሚፈልጉ አሽከርካሪዎች የፓርኪንግ ቦታው እንዲበቃ የሰዓት ገደብ መጣሉንም የአገሪቷ የትራፊክ ፖሊስ ኃላፊዎች ገልጸዋል፡፡ አንድ አሽከርካሪ ከ15 ደቂቃ በላይ በፓርኪንጉ ከቆየ በአካባቢው ያሉ ሌሎች አሽከርካሪዎች ጥቆማ እንዲያደርጉም ጠይቀዋል፡፡ በፓርኪንግ አገልግሎቱ መደሰታቸውን የቻይና አሽከርካሪዎች የገለጹ ሲሆን፣ በሌሎች የሕዝብ መፀዳጃ ቤቶች አቅራቢያ ፓርኪንግ እንደሚዘጋጅ የትራፊክ ፖሊስ ኃላፊዎች አሳውቀዋል፡፡

************

በአደጋ ጊዜ የደረሰው ፒዛ

ጣልያን ከምትታወቅባቸው ምግቦች መካከል ፒዛ ግንባር ቀደሙ ነው፡፡ ፒዛ ከአገሪቱ አልፎ በመላው ዓለም ተወዳጅነትን አትርፏና ፒዛ ቤት የሌለበት አገር አለ ለማለት ያስቸግራል፡፡ ጣልያን ውስጥ ያሉትን ፒዛ ቤቶች ደግሞ ለመቁጠርም ያዳግታል፡፡ ከፒዛ ቤቶቹ የአንዱ ባለቤት የሆነው ሲሞኔ ዲ ማርያ ከሌሎች በተለየ የዓለምን ትረኩት የሳበው ባለፈው ሳምንት ነበር፡፡ አመሻሽ ላይ ሰሜን ጣልያን የሚገኝ ተራራማ አካባቢ እሳት ይነሳና መንገድ ይዘጋል፡፡ ቀኑን ሙሉ ሠርተው የደከሙ ግለሰቦች ወደ ቤታቸው ለመሄድ ተቸግረውም ለሰዓታት ቆሙ፡፡ ሁኔታው በፍጥነት የመገናኛ ብዙኃንን ትኩረት ሳበና በሚዲያ ይተላለፍ ጀመር፡፡ ይህንን የተመለከተው ሲሞኔ ሠራተኞቹ በአፋጣኝ ፒዛና ውኃ ይዘው መንገድ ለተዘጋባቸው ግለሰቦች እንዲሰጡ አዘዘ፡፡ የፒዛ ቤቱ ሠራተኞችም በነፃ በአካባቢ የነበሩ ሰዎችን ይመግቡ ጀመር፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው፣ ሲሞኔ ይህንን በሚያደርግበት ወቅት እሳቱ መኖሪያ ቤቱን ሊያቃጥል የ100 ሜትሮች ርቀት ብቻ ቀርቶት ነበር፡፡ በእሳት አደጋ ሠራተኞች ርብርብ እሳቱ ስለቆመ ግን ቤቱ ሳይቃጠል ቀርቷል፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች ሲሞኔን ሲያመሰግኑ እሱ ደግሞ ‹‹መመስገን የሚገባቸው እሳት አደጋ ተከላካዮቹ ናቸው፤›› ነበር ያለው፡፡

*******

በዶናልድ ትራምፕ የተሰየመው ዝርያ

ሙት የሚባለው ቢራቢሮ ዝርያ ውስጥ የምትመደብ ነፍሳት በዶናልድ ትራምፕ ተሰይማለች፡፡ ነፍሳቷ ወደ ቢጫ የሚያደላና ነጭ ራስ ያላት ሲሆን፣ ይህ ደግሞ ከትራምፕ ፀጉር አሠራር ጋር ተመሳሳይ ስለሆነ ስያሜው እንደተሰጣት ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ባለፈው ሳምንት ሥርዓተ ሲመታቸው የተከናወነውን የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ትራምፕ መጠሪያ የወሰደችው ነፍሳት ሙሉ ስም ኒዎፓልፓ ዶናልድትራምፒ ሲሆን፣ መኖሪያዋ በደቡብ ካሊፎርኒያና ሜክሲኮ አቅራቢያ ነው፡፡ ስያሜውን የሰጣት ባዮሎጂስት ቫዝሪክ ናዘሪ እንደገለጸው፣ ልዩ ልዩ ዝርያዎች የሚኖሩባቸው አካባቢዎች ጥበቃ እንዲደረግላቸው ለማሳሰብ ነፍሳቷ በትራምፕ ተሰይማለች፡፡ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ለዓሳ ዝርያዎች ጥበቃ ላደረጉት ጥረት ዕውቅና ለመስጠት በስማቸው አንድ ዓሳ እንደተሰየመላቸው ይታወሳል፡፡

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች