የቀድሞ የየመን ፕሬዚዳንት አሊ አብደላ ሳላህ በሰነዓ ቤታቸው ላይ በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት እንደተገደሉ አልጀዚራ የሁቲ ሬዲዮን ጠቅሶ ዘገበ፡፡
በሰነዓ በሚገኘው የሳላህ ቤት አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች ቤታቸው በሁቲ አማጽያን የቦምብ አደጋ እንደተፈጸመባቸው መናገራቸውንም አልጀዚራ ዘግቧል፡፡
ነገር ግን የሳላህ ጄኔራል ፒፕልስ ኮንግረስ ፓርቲ ፕሬዚዳንቱ ሞተዋል ተብሎ የተሰራጨውን ዘገባ አጣጥሎታል፡፡