Saturday, June 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርትየቴክኒክ ኮሚቴ ያወጣውን የብሔራዊ አሠልጣኝ መሥፈርት ፌዴሬሽኑ አልተቀበለውም

የቴክኒክ ኮሚቴ ያወጣውን የብሔራዊ አሠልጣኝ መሥፈርት ፌዴሬሽኑ አልተቀበለውም

ቀን:

–  የ2019 የአፍሪካ ዋንጫ ምድብ ማጣሪያ የቀረው ከሦስት ወር ያነሰ ጊዜ ነው

እ.ኤ.አ. በ2019 የሚካሄደው 32ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ የሚጀመርበት ጊዜ ከሦስት ወራት ያነሰ ነው፡፡ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ እስካሁን ባለው የዝግጅት ምዕራፍ አንድ አካል የሆነውን ብሔራዊ አሠልጣኝ ምርጫ አላደረገም፡፡ ጥር 9 ቀን 2009 ዓ.ም. ቴክኒክ ኮሚቴ ያቀረበው የመምረጫ መሥፈርት ፌዴሬሽኑ በአብዛኛው ውድቅ ተደርጓል፡፡ በመሥፈርትነት ከተጠቀሱ መካከል፣ ‹‹በዜግነት ኢትዮጵያዊ የሆነ፣ ፆታ ወንድና ደመወዝ በስምምነት›› የሚሉት ተጠቃሾች ናቸው፡፡

ብዙዎቹ የአፍሪካ አገሮች ለመጀመርያው ምድብ ማጣሪያ ከወዲሁ አሠልጣኞቻቸውና ብሔራዊ ቡድናቸውን እያቀናጁ በሚገኙበት በዚሁ ወቅት፣ የኢትዮጵያ ሁኔታ ግን ግራ እያጋባ እንደሚገኝ የሚናገሩ አሉ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን  (ካፍ) ባወጣው ድልድል መሠረት ጋና፣ ኬንያና ሌሴቶ በሚገኙበት ምድብ ውስጥ ኢትዮጵያ ተደልድላለች፡፡ ይሁንና ከኢትዮጵያ በኩል እየታየ ያለው እንቅስቃሴ ሥጋትን ከወዲሁ የሚያጭር መሆኑን ጭምር የዘርፉ ሙያተኞች ይናገራሉ፡፡

- Advertisement -

ሰሞኑን መሥፈርቱን አዘጋጅቶ ለፌዴሬሽን ያቀረበው ቴክኒክ ኮሚቴ በመካሄድ ለሚገኘው 31ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ወቅት ከብሔራዊ ቡድኑ የቀድሞ ዋና አሠልጣኝ አቶ ዮሐንስ ሳሕሌ ጋር አብሮ እንዲሰናበት ተደርጎ የነበረ መሆኑ አይዘነጋም፡፡ ፌዴሬሽኑ ኮሚቴውን እንደገና ወደ ኃላፊነት ያመጣበት መንገድ እንዴትና በምን አግባብ እንደሆነ ሳያሳውቅ፣ አሁን ደግሞ ያንኑ ኮሚቴ ‹‹እንድታዘጋጅልኝ የፈለግኩት ይህን ዓይነት መሥፈርት አይደለም፤›› በሚል ኮሚቴው ያቀረበውን መሥፈርት ውድቅ ማድረጉ የተቋሙን ግምታዊ አካሄድ እንደሚያመላክት ጭምር ነው ሙያተኞቹ የሚናገሩት፡፡

በመሥፈርትነት ከቀረቡትና ቀደም ሲል ከተጠቀሱት በተጨማሪ ዕጩው አሠልጣኝ ከዓለም አቀፍ ቋንቋዎች ማለትም ከእንግሊዝኛ፣ ከፈረንሣይኛና ከዓረብኛ አንዱን መናገር ይጠበቅበታል፡፡ ሌላው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዕውቅና በሰጠው የካፍና የፊፋ ኮርሶችን ወስዶ ‹‹ኤ›› የሙያ ፈቃድ (ላይሰንስ) ያለው፣ በአገሪቱ ሊጎች በከፍተኛና ፕሪሚየር ሊግ ቢያንስ አሥር ዓመት ያሠለጠነ የሚለው ይገኝበታል፡፡

የተቋሙን አካሄድና የአሠራር ሥርዓት አስመልክቶ ሙያተኞቹ፣ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የተቋሙን ቴክኒካዊ እንቅስቃሴ የሚከታተል በፕሮፌሽናሎች የሚመራ ቴክኒክ ዲፓርትመንት እያለው የበጎ ፈቃድ (አማተር) የቴክኒክ ሙያተኞች ለምን እንዳስፈለጉት ይጠይቃሉ፡፡ ምክንያቱም ፊፋ እንደ ኢትዮጵያ ለመሰሉ እግር ኳሳቸው በማደግ ላይ ለሚገኙ አባል ፌዴሬሽኖች በየዓመቱ እስከ 500 ሺሕ ዶላር የሚሰጠው ፌዴሬሽኖቹ ከአማተር አሠራር ወጥተው ወደ ዘመናዊ አደረጃጀት እንዲገቡና በሙያተኞች እንዲመሩ በማሰብ እንደሆነም ይናገራሉ፡፡ ስለሆነም ፌዴሬሽኑ ቢያንስ ከኮሚቴያዊ አሠራር ወጥቶ ቴክኒክ ዲፓርትመንቱ አቅም ከሌለው አቅም ባላቸው ሙያተኞች ተክቶና ተደራጅቶ የአገሪቱን እግር ኳስ ወደ ሚፈለገው አቅጣጫ ማምጣት እንደሚጠበቅበት ጭምር ያስረዳሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...