Sunday, June 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ፍሬከናፍርፍሬ ከናፍር

ፍሬ ከናፍር

ቀን:

‹‹ሰላሳ ዘጠኝ ንፁኃንን ከጨፈጨፍ አረመኔ ጋር በአንድ ሕንፃ ውስጥ መኖሬ በጣም አበሳጭቶኛል››

ዓሊ ሃይደር ደሚር የተባለ ቱርካዊ ከተናገረው የተወሰደ፡፡ ደሚር ይኼንን ያለው በአውሮፓውያኑ አዲስ ዓመት ዋዜማ በኢስታንቡል የምሽት ክለብ 39 የተለያዩ አገር ሰዎችን በጦር መሣሪያ በመጨፍጨፍ የተጠረጠረው ግለሰብ፣ እሱ የሚኖርበት የአፓርታማ ሕንፃ ላይ ማክሰኞ ጥር 9 ቀን 2009 ዓ.ም. ፖሊስ በፈጸመው ድንገተኛ ወረራ ሲያዝ ነው፡፡ ደሚር ሰውየው በከፍተኛ ሁኔታ በተጠናከረ የፖሊስ ኃይል በቀጥጥር ሥር ሲውል በነበረው ሁካታ ተደናግጦ በሩን ሲከፍት፣ ፈጽሞ  ያላመነውን ነገር ያያል፡፡ እነዚያን ንፁኃንን የፈጀ የተባለው ግለሰብ ሰላማዊ ዜጋ ይመስለው ስለነበር፣ የአሸባሪው አይኤስ አባል በመሆን ንፁኃንን መፍጀቱ አንጀቱን እንዳቃጠለው ለጋዜጠኞች ተናግሯል፡፡ ሌላው የአፓርታማ ነዋሪ ሴዘር አራስ ደግሞ ግለሰቡ ለአፓርታማው ነዋሪዎች በጣም ቅርባቸው ቢሆንም ምንም ዓይነት መረጃ እንደሌላቸው ተናግሯል፡፡ የ39 ንፁኃን ሕይወት አጥፍቷል የተባለው ተጠርጣሪ ማንነቱ ባይገለጽም፣ በምሥሉ ላይ በቁጥጥር ሥር ውሎ ይታያል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አወዛጋቢው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ጉዳይ

በኢትዮጵያ የሕገ መንግሥት ማሻሻል ጉዳይ ከፍተኛ የፖለቲካ ውዝግብ የሚቀሰቀስበት...

 መፍትሔ  ያላዘለው  የጎዳና  መደብሮችን  ማፍረስ

በአበበ ፍቅር ያለፉት ስድስት ዓመታት በርካቶች በግጭቶችና በመፈናቀሎች በከፍተኛ ሁኔታ...

የተናደው ከቀደምቱ አንዱ የነበረው የአዲስ አበባ ታሪካዊ ሕንፃ

ዳግማዊ አፄ ምኒልክ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ መናገሻ ከተማቸውን...

የአከርካሪ አጥንት ሕክምናን ከፍ ያደረገው ‘ካይሮፕራክቲክ’

በአፍሪካ ከጀርባ ሕመም ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች ለከፍተኛ የአካል...