Thursday, September 21, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናለማዳበሪያና ለስኳር ፋብሪካ ፕሮጀክቶች መጓተት ሕጋዊ ተጠያቂነት ማስፈን ያልተቻለበት ምክንያት ተገለጸ

ለማዳበሪያና ለስኳር ፋብሪካ ፕሮጀክቶች መጓተት ሕጋዊ ተጠያቂነት ማስፈን ያልተቻለበት ምክንያት ተገለጸ

ቀን:

2007 ዓ.ም. በፊት ተጠናቀው ማምረት በመጀመር ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት የውጭ ምንዛሪ ወጪን ይቀንሳሉ ተብሎ የሚገነቡት ግዙፍ የስኳርና የማዳበሪያ ፋብሪካዎች፣ ሕጋዊ ተጠያቂነት ማስፈን ያልተቻለበት ምክንያት ተገለጸ፡፡ ፕሮጀክቶቹ ከተያዘላቸው ጊዜእጥፍ ዘግይተው እስካሁን ባለመጠናቀቃቸው የሚመለከታቸው አካላትን ሕጋዊ ተጠያቂ ማድረግ ተገቢ ቢሆንም፣ ይኼንን ለማድረግ አለመቻሉን የመንግሥት ልማት ድርጀቶች ሚኒስትሩ አቶ ግርማ አስረድተዋል።

የፕሮጀክቶቹ ባለቤቶች የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽንና የኢትዮጵያ ኬሚካል ኮርፖሬሽን፣ ፋብሪካዎቹን ገንብቶ እንዲያስረክብ ከተመረጠው የኢትዮጵያ ብረታ ብረትና የኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ጋር የተፈራረሙት ውል ሕጋዊ ተጠያቂነትን ለማስፈን እንደማያስችል ሚኒስትሩ አስታውቀዋል። ሚኒስትሩ ይኼንን የገለጹት፣ ለፓርላማው የመንግሥት ልማት ድርጀቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ነው፡፡

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ሚኒስቴሩ በበላይነት በሚከታተላቸው ሜጋ ፕሮጀክቶች መጓተትና ተጓዳኝ ችግሮች ላይ ሕጋዊ ተጠያቂነትን በተመለከተ ዕርምጃ እንዲወስድ በፓርላማው አቅጣጫ ተሰጥቶት፣ እስካሁን ድረስ ምንም ዓይነት ተጠያቂነት ለምን እንዳልኖረ ማብራርያ ተጠይቀዋል።  አቶ ግርማ በሰጡት ምላሽ ቋሚ ኮሚቴው ሕጋዊ ተጠያቂነት እንዲሰፍንና የአገሪቱ ሀብት ያለብክነት ሥራ ላይ እንዲውል የሚያደርገውን ጥረት በማድነቅ፣ በግዙፎቹ የስኳርና የያዩ ማዳበሪያ ፋብሪካ ፕሮጀክቶች ያለቅጥ መጓተትና ሌሎች ተያያዥ ችግሮችን አስመልክቶ ተጠያቂነትን ማስፈን ያልተቻለው፣ ግንባታዎቹን ለማከናወን ከኮንትራክተሩ ጋር የተገባው ውል የማይፈቅድ በመሆኑ ነው ብለዋል።

የፕሮጀክቶቹ ባለቤት የሆኑት የመንግሥት ልማት ድርጅቶቹ ከኮንትራክተሩሜቴክ ጋር በፈጸሙት ውል ከፕሮጀክቶቹ ግንባታ ሒደት ጋር በተያያዘ የሚነሱ ችግሮችን እንደ መንግሥት ተቋማት በጋራ በመነጋገርና በመደጋገፍ ያስወግዳሉ፣ አለመግባባቶችንም በዚህ አግባብ ይፈታሉ የሚል በመሆኑ ሕጋዊ ተጠያቂነትን በየትኛውም ወገን ላይ መጣል እንዳልተቻለ አስረድተዋል። መፍትሔውም ጥብቅ የኮንትራት ውል ማሰር የሚቻልበትን አሠራር መፍጠር እንደሆነ ተናግረዋል።

ይኸው ቋሚ ኮሚቴ ከሁለት ሳምንት በፊት የፕሮጀክቶቹን ባለቤቶችና ኮንትራክተሩን ጠርቶ ስለማነጋገሩ መዘገባችን ይታወሳል። የያዩ ማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ ከተጀመረ በርካታ ዓመታትን ቢያስቆጥርምግንባታው 50 በመቶ በታች ነው። የዚህ ፕሮጀክት ዋነኛ ችግር የውጭ ምንዛሪ ማግኘት አለመቻልና ከካሳ ክፍያ ጋር የተያያዘ ቅሬታ በአካባቢው ማኅበረሰብ መነሳቱ፣ እንዲሁም የመሬት መንሸራተት ችግር መሆኑን የፕሮጀክቱ ባለቤት ኬሚካል ኮርፖሬሽንና ኮንትራክተሩ ገልጸው ነበር።

የማዳበሪያ ፋብሪካውን ገንብቶ ለማስረከብ 11 ቢሊዮን ብር እንደሚፈጅ ታስቦ የተጀመረ ቢሆንም፣ በአሁኑ ወቅት ግንባታውን ለማጠናቀቅ የሚያስፈልገው ወጪ 21 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሚሆን ተገምቷል። የያዩ ማዳበሪያ ፋብሪካ መቼ እንደሚጠናቀቅ ሜቴክ እቅጩን መናገር አለመቻሉ የፕሮጀክቱን ባለቤት በእጅጉ ያሳሰበው መሆኑን፣ የኬሚካል ኮርፖሬሽን የሥራ ኃላፊ አቶ ፍቃዱ አመንቴ በወቅቱ ተናግረው ነበር።

ፕሮጀክቱ በመዘግየቱ ኬሚካል ኮርፖሬሽን በአሁኑ ወቅት በየወሩ 70 ሚሊዮን ብር የባንክ ወለድ እየከፈለ እንደሚገኝ መናገራቸውን መዘገባችን አይዘነጋም። ‹‹ከውጭ ስለሚገባው ማዳበሪያ እንተውና ፋብሪካው ቢጠናቀቅስኢኮኖሚካሊአዋጭ ይሆናል ወይ የሚለው ጉዳይ ሥጋታችን ነው፤›› ማለታቸውንም እንዲሁ።

በአሁኑ ወቅት በሜቴክ እጅ የሚገኙት ሁለት ስኳር ፋብሪካዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህም ውስጥኦሞ ኩራዝ ቁጥር አንድ ፋብሪካን ግማሽ የማምረት አቅም አጠናቆ በታኅሳስ 2010 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ እንደሚያስረክብ ኮንትራክተሩ መግለጹን፣ በእጁ የሚገኘውን ሌላውን ፋብሪካ በለስ ቁጥር አንድንም በዘንድሮ በጀት ዓመት አገባዶ ለማስረከብ ማቀዱን፣ ነገር ግን በዕቅዱ መሠረት ለመፈጸም የውጭ ምንዛሪና የኃይል አቅርቦት ማግኘት እንደሚገባው ለቋሚ ኮሚቴው መግለጹን ከሁለት ሳምንት በፊት መዘገባችን ይታወሳል።

 

 

 

 

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...