Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅዕፀ በለስ እንደ ገና ዛፍ

ዕፀ በለስ እንደ ገና ዛፍ

ቀን:

የገና በዓል መገለጫ ከሆኑት አንዱ ዛፍ ነው፡፡ ቀደም ሲል ጥድ እየተቆረጠ በልዩ ልዩ ማሸብረቂያዎች ይዋብ ነበር፡፡ አሁን አሁን አርቲፊሻል ዛፎች በየቦታው ነግሰው ይታያሉ፡፡ በዘንድሮው ገናም በተለያዩ ከተሞች በየአደባባዩ በየመደብሩ ደጃፍ ተተክለው እየታዩ ነው፡፡ ከሕፃን እስከ አዋቂ ፎቶ ሲነሱበትም ነበር፡፡ በመቐለ ከተማ ጅብሩክ አካባቢ በሚገኘው ወዲ መሸሻ ሕንፃ የቆመው አንዱ ነው፡፡ በድረ ገጽ ውስጥ የተገኘው የገና ዛፍ ደግሞ በበለስ ዛፍና ፍሬው የተዋበ ነው፡፡ በሥነ ቃል የሚባለውን ‹‹ዕፀ በለስ በልቶ ሔዋን ከንፈርሽ፣ መድኃኔ ዓለም ልቤ ተሰቀለልሽ››ን ያስታውሳል፡፡

(በሔኖክ ያሬድ)

**********

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

እራሴን ታዘብኩት

ነፍሴን ጭንቅ አላት

መውጪያ መግቢያ ጠፍቷል፡፡

ባልታሰበ ውጊያ

በዓይን ለዓይን ግልቢያ፡፡

ልቤን ለማስረከብ

ለደስታ ስዋከብ፡፡

እምቶነው ጠፍቷል

ነፍሴ አስጨነኳት፡፡

አልፋኝ ልትሄድ ጉብል

በእጄ ብጠራት በዓይኔ ባባብል፡፡

ለሷ ከቶ ምኗ

የኔ ጉስቁልና፡፡

ነፍሴ መራኮቷ

ከላይ ታች ማለቷ፡፡

ጂማ ዩኒቨርሲቲ ኪነ ጥበባት ክበብ፣(1993)

                  ****************************

ሊጠፉ የደረሱ ቢራቢሮዎችን በመግደል ፍርድ ቤት የቀረበ

ጉዳዩ የተፈጸመው በእንግሊዝ ብሪስቶል ነው፡፡ የ57 ዓመቱ ፍሊፕ ኩለን፣ በእንግሊዝ ሊጠፉ የተቃረቡ ሰማያዊ ቢራቢሮዎች (ማኩሊና ኦሪዮን) ገድሏል በሚል በስድስት ጥፋት ተከሶ ፍርድ ቤት ቀርቧል፡፡ ኩለን ድርጊቱን አልፈጸምኩም ቢልም፣ በ2015 ከሰመርሴትና ከግሎስቲሸር ሁለት ቢራቢሮዎችን ይዞ ወደ ቤቱ መውሰዱንና የሞቱ ቢራቢሮዎችም በቤቱ መገኘታቸው በፍርድ ቤት ተሰምቷል፡፡ ኩለን የዋስ መብቱ የተጠበቀለት ሲሆን፣ ለውሳኔም ለመጋቢት 2009 ዓ.ም. ተቀጥሯል፡፡ እንዲህ ዓይነት ክስ በእንግሊዝ ሲቀርብ የመጀመሪያ መሆኑን ቢቢሲ አስፍሯል፡፡

                  ****************************

የዶናልድ ትራምፕ በዓለ ሲመት ግብዣን ያልተቀበሉ እንግሊዛውያን ዘፋኞች

እንግሊዛውያኑ ዘፋኞች ቻርሎቴ ቸርችና ሬቤካ ፈርጉሰን በአሜሪካው ተመራጭ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዓለ ሲመት እንዲገኙ የቀረበላቸውን ጥሪ አንቀበልም አሉ፡፡

በክላሲካል ዘፈኖቿ የምትታወቀው ቸርች፣ የ2016ን የትራምፕ ምረጡኝ ቅስቀሳ ስትነቅፍ እንደነበርና ከቅርብ ዓመታት ወዲህም የግራ ዘመም ፖለቲካዊ አመለካከቷን በትዊተር ገጿ ማስፈር መጀመሯን ሮይተርስ አስታውሷል፡፡

በ‹‹ዘ ኤክስ ፋክተር›› ቴቪ ታለንት ሾው ዕውቅና ያተረፈችው ፈርጉሰን በትራምፕ በዓለ ሲመት ላለመገኘት የወሰነችው ‹‹ስትሬት ፍሩት›› የተባለውን ዘፈኗን በመድረክ ለመጫወት በመከልከሏ መሆኑንም ታውቋል፡፡ የትራምፕን በዓለ ሲመት ዝግጅት የሚመራው የሪል ስቴትና የኮሎኒ ካፒታል መሥራች ቶማስ ባራክ ከሳምንት በኋላ በሚኖረው የትራምፕ በዓለ ሲመት የኮከቦች ዕጥረት ሊገጥም እንደሚችል ጠቁሞ፣ ግብዣውን ባጣጣሉት ቸርችና ፈርጉሰን ላይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል፡፡

             ****************************

የዘራፊዎች ሲሳይ የሆነው የሊዮኔል ሜሲ ሐውልት

ከመዳብ የተሠራው የአርጀንቲናው ኮከብ እግር ኳስ ተጫዋች ሊዮኔል ሜሲ ሐውልት ለዘራፊዎች ሲሳይ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በቦነስ አይረስ በሰኔ 2008 ዓ.ም. የቆመው የሜሲ ሐውልት፣ ግማሹ የተሰበረ ሲሆን፣ ጭንቅላቱ፣ ክንዱና የፊት ለፊቱ የሰውነት ክፍል ተሰርቋል፡፡

የቦነስ አይረስ ከተማ አስተዳደር፣ የሜሲን ሐውልት ለመስረቅና ለማፈራረስ ለምን እንደተፈለገ ግልጽ እንዳልሆነለት ገልጾ፣ ሐውልቱ መልሶ እንደሚጠገን አስታውቋል፡፡

**********

      ‹‹ጀፎረ››

ጀፎረ በጉራጌ ማኅበረሰብ መኖሪያ አካባቢ አንዱን መንደር ከሌላው መንደር የሚያገናኝ ሰፊ ጎዳና ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ መንደሮቹ የሚሠሩት የምሥራቅና የምዕራብ አቅጣጫን በመከተል ነው፡፡ ይህም የሚሆንበት ምክንያት ጠቅላላው የጉራጌ መሬት አቀማመጥ ከምሥራቅ ወደ ምዕራብ ዘንበል ስለሚል፣ ወንዞቹም የሚፈሱት በዚሁ አቅጣጫ ስለሆነና ቤቶቹ ከወንዝ በሚዋሰነው መሬት ራስጌ ስለሚሠሩ ነው፡፡

አንድ መንገደኛ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ በሚጓጓዝበት ጊዜ ከአንድ መንደር ጀፎረ እየተሸጋገረ ከአካባቢው አንድ ዳርቻ ወደ ሌላው ዳርቻ ሊደርስ ይችላል፡፡ ጀፎረ የመንደሩ ውበት ስለሆነ በእንክብካቤ እየተጠበቀ ሁልጊዜ በድንክ ለስላሳ ሳር የተሸፈነ ሆኖ ዳርና ዳሩ አልፎ አልፎ እንደ ዝግባ በመሳሰሉ ትላልቅ ዛፎች አጊጦ ይታያል፡፡ ያገሬው ነዋሪ በጋራ ጉዳይ ለመመካከር ስብሰባ የሚያደርገው በጀፎረ መገናኛ አደባባይ ላይ ነው፡፡ እንደመስቀል የመሳሰሉ ታላላቅ በዓላት በሚከበሩበት ጊዜ የበዓሉ ሥነ ሥርዓት የሚካሄደውና ደመራውም የሚቃጠለው በዚሁ አደባባይ ነው፡፡ የጀፎረ ስፋት ትንሹ 24 ሜትር ትልቁ 48 ሜትር ነው፡፡ በዚህ አኳኋን ከጥንት ጀምሮ በስፋት ተከብሮ የሚጠበቀው ጀፎረና በግራና ቀኙ በተርታ የተሠሩት ቤቶች አካባቢውን በዘመናዊ ቅያስ የተሠራ ስለሚያስመስለው ለኅበረተሰቡ ባህል ከፍ ያለ ግምት የሚያሰጥ ነው፡፡

የጉራጌ መንገዶች ሥራ ድርጅት፣ (1980)

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...